>

አይዞሞርፊክ ሀብታሙ (አያሌው - ክፍል 2-)

አይዞሞርፊክ ክፍል 2
ሀብታሙ አያሌው
ህወሓት እንደ ኤሊ
———————–
ህወሓት ከኤሊ ጋርም የሚያመሳስለዉ ነገር አለ፤ ኤሊ በልዩ ሁኔታ የሚታወቅባቸው  ሦስት መለያዎች አሉት።
* አንዱና የመጀመሪያው ከውጭ
   በሚደርስ ጥቃት ለመስበር በጣም
    አታካች የሆነ ጠንካራ የሰውነት
    መሸፈኛ (ድንጋይ) ሲሆን፤
 * ፈፅሞ ከማንም ጋር እኩል
    መራመድ የማይችል ከራሱ በቀር
    ምንም አይነት ጓደኛ የሌለው፣
    ማንንም የማያምን፣ ኮሽ ባለ
    ቁጥር ድንጋዩን እየለበሰ
    የሚያደፍጥ መሆኑ፤
* ሦስተኛ መለያው የድንጋይ ክምችት
ባለበት ሁሉ ድምፁን አጥፍቶ ከድንጋዩ ጋር በመመሳሰል በአካባቢው መኖሩ እንዳይታወቅ የማድረግ ዘዴ የሚከተል መሆኑ በዋና ዋና መለያነት ሊጠቀስ ይችላል።
የህወሓት  ስሪትም  ከኤሊ ጋር በርካታ ተማስሎዎች አሉት። ህወሓትን እንደ ኤሊ ድንጋይ ለበስ አድርገውት የቆዩትም  በአንድ ብሔረሰብ አባላት የበላይነት ስር የወደቀው የመከላከያ፤ የደህንነት፤ የፌደራል ፖሊስ፤ የኢኮኖሚ ተቋማት፤ ክልሎችን ሁሉ የሚቆጣጠር የህቡ መዋቅር፤ የሚዲያ ተቋማ እና የመሳሰሉት መሆኑ ከውጭ በሚደረግ ጥቃት ብቻ በቶሎ ለጉዳት እንዳይጋለጥ አድርጎ መቆየቱ ተማስሎ አንድ ልንለው እንችላለን።
ተማስሎ ሁለት ከዘመኑ ጋር መራመድ የማይችል ቆሞቀር የፖለቲካ ኃይል በመሆኑ ታሪክ ላይ ተቸክሎ ጥላቻ እየሰበከ ከማዝገም በቀር ፈፅሞ ተራማጅ መሆን አለመቻሉ፤ ኮሽ ባለ ቁጥር ድንጋዩአን ለብሳ እንደምትደበቀው ኤሊ  ህወሓትም ኮሽ ባለ ቁጥር መሳሪያ ስር የሚደበቅ በሴራ ከመጥለፍ በቀር ፊትለፊት መጋፈጥ የማይችል ብሔር መደበቂያው የሆነ ድርጅት መሆኑ በተማስሎ ሁለት የሚታይ ነው።
ተማስሎ ሦስት  ከእውነት ጋር የተጣላ አስመሳይ ባህሪው ሲሆን ኤሊ በድንጋይ ክምችት ውስጥ ድንጋይ መስሎ የሚቀመጥ በተግባር ግን ህይወት ያለው ነገር እንደሆነ ሁሉ ህወሓትም  በተግባር ፀረ-ዴሞክራሲ ኃይል ሆኖ ሳለ  ዴሞክራሲያዊ  ለመምስለ  በራሱ አምሳል የፖለቲካ ፓርቲዎች ከማደራጀት ባሻገር የምርጫ ጫወታ  አዘጋጅቶ  ለማስመሰል እና ለመመሳሰል  ያልቆፈረው ጉድጓድ የለም።
ህወሓትን በተገቢው ደረጃ ለማጥቃትና እስከመጨረሻው ለማሸነፍ  ብትፈልግ እንደ ኤሊ አካል ውስጠኛውን ክፍል መነካካትና  ትግሉን ከመሃል እንብርቱ ላይ መጀመር  ተደብቆ የሚገኘዉን ጭንቅላትና ልቡን ማፍረስ  ይጠይቃል።   በእርግጥ የህወሓት ውጫዊ አካል በኤሊ የድንጋይ ሽፋን መመሰሉ  የድርጅታዊ ተክለ ቁመናው ጥንካሬ ማሳያ ነው ማለት እንዳልሆነ መገንዘብ ጠቃሚ ነው።  ንፅፅራዊ አመክንዮው  የህወሓት ውጫዊ አካል በኤሊ ተማስሎ የሚታየው ከአመለካከት እንፃር የ(presuiption) ጉዳይ  መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል።
ህወሓት ሰዎች እንዲፈሩትና ጠንካራ እንደሆነ አድርገው እንዲስሉት በርካታ ስራዎች ስርቷል፤  ነገር ግን ውስጡ ባዶና በተቃርኖ የተሞላ፤ በየጊዜው በውስጥ ችግር የሚታመስ፤  በሴራ ፖለቲካ የሚናጥ፤  ማህበራዊ መሰረቱ እጅግ ደካማ የሆነ፤  በሃሳብ የማያማኑ ልዩነትን የማያስተናግዱ ባንዳዎች የተጠራቀሙበት፤  እርስ በእርሳቸው የሚፈራሩበት የተፈረካከሰና አንድነት የጎደለዉ እብቅ ገለባ ድርጅት መሆኑን በሚገባ መገንዘብ በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡
ህወሓት እንደ ድርጅትም ሆነ የትግራይ ክልል እንደ ክልል የተቀባይነት እጦት ቀውስ ውስጥ በከተታቸው  ብቃትም ሆነ አቅም በሌላቸዉ አመራሮች እጅ መውደቃቸውን ለመረዳት የዋና ዋናዎቹን አመራሮች የስቦዕና ዝቅጠት በማሳያነት መጥቀስ ይቻላል።
ለምሳሌ:-   የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር የሆነው ዶ/ር  ደብረ ፅዮን  የትግራይን ህዝብ ፍላጎት ለማሳካት የሚሰራ ወይም ለአገር ህልውና የቆመ መሪ ሳይሆን በሴቶች ጭን ተደብቆ ውሎ የሚያድር ሴሰኛ ስለመሆኑ በርካታ አክቲቪስቶች በማስረጃ ሲሞግቱ ተመልክተናል፡፡  ምንም አይነት የፖለቲካ አቋም የሌለው አዲስ አበባ የተናገረውን መቀሌ ሲደርስ መድገም የማይችል ተራና የስልጣን ጥም ብኩን ያደረገው ግለሰብ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ።
ቀደም ሲል  የአገሪቷን የደህንነት ተቋም እንደፈለገ ሲዘውርና  ኤሎሄ በሚያሰኝ ስቃይ መራር ግፍ ሲፈፅም የነበረው  ነፍሰበላውን ጌታቸዉ አሰፋም ሌላው ተጠቃሽ ነው፡፡ ጌታቸው አሰፋ በባህሪው ለውይይት ራሱን አዘጋጅቶ የማያዉቅ፣ በምንም አይነት ማህበራዊ ተሳትፎ ውስጥ የሌለ፤  ከሰዎች ተነጥሎ በመኖር በብቸኝነት የሚሰቃይ  ለህዝብ ሳይሆን ለራሱ የሚኖር አገር ሻጭና ዘራፊ ነዉ፡፡
ሌላኛው ተጠቃሽ ልበ ስውሩ አስመላሽ ወ/ሥላሴ ሲሆን ይህ ሰው በእጅጉ ጨካኝ የሆነ፤ በዘረኝነት የተለከፈ፤ ፍፁም አምባገነን፣ የፍትህ ተቋማትን ለህወሓት አስገብሮ ስንቱን ዘብጥያ ሲያስወረውር የኖረ ሰብዓዊ ርህራሄ እና ሞራል የሌለው ሰው መሆኑ በአብዛኛው ማህበረሰብ የሚታወቅ ነው።
ሌላው ተጠቃሽ ጌታቸው ረዳ (ጌታቸው ቮድካ) የተሰኘው ምኩን ሰውም  ቀን ከሌት ቮድካ እንደ ጡጦ ካልተሰካለት መንቀሳቀስ የማይችል ምኩን ሰው ነው።  ጌታቸው ቮድካ ለራሱ ብቻ መኖር የሚፈልግ፤  ሰካራምና የሱስ ማገገምያ ጣብያ መሄድ የነበረበት ሴሰኛ ሆኖ ሳለ በትግራይ ህዝብ ህልውና ለመወሰን በድፍረት እራሱን ለጌታቸው አሰፋ በጥቅም የሸጠ  አሳፋሪ ሰው ነው፡፡
የዲሲው ምርኮኛ አዲስዓለም ባሌማም ያለውን ጊዜ ሁሉ በማጭበርበር እና  የህዝብ ሃብት በመዝረፍ የሚያሳልፍ እጁ በሙስና የተጨማለቀ ዘራፊ መሆኑን  ብዙዎች የሚመሰክሩበት ነው፡፡  ልጅ ያላቸው ሁሉ ልጆቻቸውን ከአገር ውጪ በዶላር ከፍለው ያስተምራሉ፤  የዘርዓይ አስገዶም ልጆች አሜሪካ  አትላንታ፤  የአስመላሽ ልጆች በርክሌ ለንደን፤ የጀነራል አብርሃ ልጆች አውስትራሊያ…
እንግዲህ የትግራይ ህዝብና ህወሓት የተሰኘው ድርጅት  እየተመሩ ያሉት እንዲህ ባሉ ሱሰኛ ዘራፊና ሞራል አልባ በሆኑ በመላው ኢትዮጵያ ተቀባይነት ባጡ  ነውረኛ አመራሮች ናቸዉ፡፡  የተደፈነ እሳተ ገሞራ የሆነችው ትግራይ …የተንቤን፣ የራያ፣ የወልቃይት፣ ዋጀራት፣ ኢሮብ፣ ኩናማ የማንነት ጥያቄዎች እስካሁን ድረስ ተዳፍነዉ ሲኖሩ የነበሩ ቀኑ ሲደርስ ግን ፈንድተው ትግራይን እንደ  ሰም የሚያቀልጧት ተጠባቂ ምፅዓቶች መሆናቸውን መገንዘብ እንኳን አልተቻላቸውም፡፡
የህወሓት መቀበሪያ እንደሚሆኑ የሚነገርላቸው ራያና ወልቃይት ከአገር አቀፋዊ ይዘት ተሻግረው ዓለም ዓቀፋዊ ትኩረት የተቸራቸው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ  ከላይ የተጠቀሱት ቀሪ የማንነት ጥያቄዎች በቅርቡ እንደታፈነ ውሃ በየፈርጁ አፈትልከው  ሲፈነዱ  የዓድዋ ልሂቃንና አመራሮችን ወደ መቃብር መክተታቸውን  አይቀሪ መሆኑን ለመንገር እመኑኝ ብዬ ዳግም ማሳሰብ አያስፈልገኝም ፡፡
ሁላችንም እንደምናውቀው ትግራይ ከአንድ ወረዳ የመጡ አመራሮች ሌሎችን ሲያስገብሩባት እና  ሲያስገብሯት የኖረች ክልል ነች። ትግራይ በአድዋ ቡድን የምትተዳደር፣ በአድዋ  ቡድን የመትዘረፍ፣ በአድዋው ቡድን መከራና እልቂት እየተደገሰላት  የምትገኝ የጭንቅ ገላጋይ ያጣች የፓለቲካ ነፍሰጡር ነች ማለት ይቻላል፡፡
—-
በእርግጥም ትግራይ በከባድ ምስቅልቅል ውስጥ ወድቃለች። ኢፈርት የተሰኘው ድርጅት የስብሃት ነጋ እና የቤተሰቦቹ የግል  ሃብት ከሆነ ሰንብቷል፡፡  የትግራይ ገጠራማ ክፍል ነዋሪዎች  በድህነት አየተመቱ፤   በችግርና በኑሮ ውድነት በእጅጉ እየተጎሳቆሉ፤  ንፁህ የመጠጥ ዉሃ ማግኘት እንኳን ምኞት ሆኖ በቀረበት በዚህ ወቅት  የአድዋ ጀሌዎች ግን  በዘረፉት ልክ የኑሮውን ከፍታ ዛሬም እንደተቆናጠጡት ነው።
የአድዋውን ቡድን የመደበቂያ ሸለፈት እንደ ኤሊዋ ድንጋይ በስር በኩል በዘዴ ሾልከህ  ውስጡን ብትመታው  ፍርስርሱ ይወጣል የምልህ ለዚህ ነው፤ ህወሓን ከውጭ መቆርቆር ትተህ ከውስጧ ነካ ብታደርጋት ድምጥማጧ ይጠፋል።  እነዚህን የማፍያ ቡድኖች ማሸነፍ የሚቻለው በውስጣቸው የተዳፈነው እሳተ ገሞራ ፈንድቶ መውጣት እንዲጀምር በተገቢው መንገድ መቆስቆስ ሲጀመር መሆኑን መረዳት ጠቃሚ ነው፡፡
—-
ህወሓት በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ጄኖሳይድ ፈፅሟል፤  አስሯል፣ ገድሏል፣ እናትን  ያለ ልጅ አስቀርቷል፤  አባትን በስተርጅና በሃዘን ፀጉር አስነጭቷሎ፣ እህትና ወንድሞችን ደም አስነብቷል፤  ከዚህ ሁሉ በኋላ ሃጢያቱን ተናዝዞ ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ ኤሊ በድንጋይ መካከል ተመሳስላ እንደምትደበቅ ህወሓትም መቀሌ መሽጎ በትግራይ ህዝብ  መካከል  በተማስሎ ተደብቋል።  መደበቅ ብቻም አይደል የኢትዮጵያ ህዝብ በዕልፍ መስዋዕትነት ያገኘውን ድል ለመቀልበስ ጦርነት እየደገሰ ይገኛል።
እናም ከዚህ በኋላ ፖለቲካዊ መሽኮርመማችንን ትተን የትግላችን የመቋጫ ምዕራፍ ሊሆን የሚገባው  ህወሓት በኢትዮጵያ ፓርላማ እና በዓለም አቀፍ መድረክ  በአሸባሪነት ተሰይሞ ውሳኔ እንዲተላለፍበትና በህግ እንዲፈርስ ለማድረግ  ያለመ መሆን ይኖርበታል፡፡  የኤሊውን (የህወሓትን ) የድንጋይ ሽፋን ሳይሆን ውስጡን መነካካቱን አጠናክረን እንቀጥል  !!
          
ኢትዮዮጵያ ለዘልዓለም ትኑር !!
Filed in: Amharic