>
5:14 pm - Thursday April 20, 9426

የህወሓቱ መስራች አረጋዊ በርሄ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ጠየቁ!!!  (ዘመድኩን በቀለ)

የህወሓቱ መስራች አረጋዊ በርሄ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ጠየቁ!!!
ዘመድኩን በቀለ
★ የትግል ጓዶቻቸውና በመቐለ አክሱም እስር ቤት የሚገኙት እነ አቦይ ስብሐት ነጋ፣ ዓባይ ጠሐየ፣ ይህን ሲሰሙ ምን አሉ ይሆን?
#ETHIOPIA | ~ አዲስ አበባ ። በተለየ መልኩ ደግሞ ዐማራውን በግሉ ይቅርታ ሊጠይቁት ይገባል ባይ ነኝ። እሳቸው የጻፋት ፀረ ዐማራ የህወሓት ማኒፌስቶ ነው ዛሬ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ሆኖ ዐማራውን ከትግሬና ከኦሮሞ ያባላው።
•••
“ ውድ ኢትዮጵያውያን የተዘጋጀሁበትን ንግግር ከማቅረቤ በፊት አንድ አጭር መልእክት አለኝ። እሱም ምንድነው ከአዲስ አበባ ለ43 ዓመታታት ጠፍቼ ነበር። ብዙ ጊዜ ስለሆነ ብዙዎቻችሁ አታውቁኝም። ማነው ይሄሰው? ልትሉም ትችላላችሁ። ስለዚህ ትንሽ እኔም ራሴን ማስተዋወቅ ስለፈለኩ አንድ አጭር መልእክት መጀመሪያ ላቅርብ።
•••
7 የትግል ጓዶች ሆነን አዲስ አበባ ፒያሳ ካፌ ተቀምጠን በ967 ዓም መጀመሪያ የነደፍነው ስትራቴጂ የብሔሮችን እኩልነት የምታስተናግድ  ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትኖር መታገል ነበር።
•••
ይህን ስትራቴጂ የትግራይ ህዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን የሚያስችለው ዲሞክራሲያዊ መብትም ለማጎናፀፍ የሚያስችለው ያለመ ትግል ነበር። ስትራቴጂው ተቀለበሰና እኔና መሰሎቼ እንደ ኢንጅነር ግደይ የመሳሰልነው በ1980 ዓም ለስደት ተዳረግን። ከ43 ዓመት በኋላ ነው የምመለሰው አዲስ አበባ። እስከዚህ ጊዜ ለነበረው ትግሉ ያስከተለው ጥፋትም ደግም ሥራ አለሁበት። የተጠያቂነቱን ድርሻዬንም አነሳለሁ። ለነበሩት ጥፋቶችም ተጠያቂ ነኝ። ከዚህ የተነሳም ይቅርታ እጠይቃለሁ”። ብለዋል ህወሓትን አዲስ አበባ ሻይ ቤት ቁጭ ብለው ጠፍጥፈው የሠሯት አረጋዊ በርሄ።
•••
ከጳጳሱ በላይ ጳጳስ ለመሆን መከራቸውን የሚበሉት ጀማሪ ካድሬዎች ግን የሚሰሟቸው አይመስልም። ለማንኛውም አረጋዊ በርሄን በተመለከተ ወንድማችን ዘ አዲስ የሚከተለውን ዘገባ አቅርቧል። ይቅርታ ብናደርግላችሁም የዚያ ዘመን አረጋውያን ተፋቱን ብሎም ይጠይቃል። ሌንጮ ለታ፣ ዳውድ ኢብሳ፣ በየነ ጴጥሮስ ወዘተ ሰምታችኋል እንደማለት ያለ ነው።
•••
ከህወሓት መስራች አባላት አንዱ የሆኑትና በትጥቅ ትግሉ መጀመርያ ዓመታት ድርጅቱን በበላይነት ሲመሩ ከነበሩት ሰዎች አንዱ የነበሩት ዶክተር አረጋዊ በርሄ የኢትዮጵያን ሕዝብ ህወሀት ላደረስችው በደል ሁሉ በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል።
•••
አረጋዊ በርሄ ህወሓት ባካሄደችው የተለያዩ የወታደራዊ ዘመቻዎች ላይ ተሳታፊ ከመሆናቸውም ባሻገር ፟ የውጭ ዜጎች ጠለፋ ላይ ዋንኛ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ https://www.ethiopianreview.com/index/11519
•••
በ 1968 ዓ.ም በአክሱምና በአድዋ አካባቢ ሲዘግብ የነበረውን እንግሊዛዊ ጋዜጠኛ ጆንን የጠለፉት እና ኤርትራ በረሃ አግተው መደራደርያ ያደረጉት እሳቸው ነበሩ። የህወሓትን ማኒፌስቶ በመጻፍም ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን በተለይ በተለይ ከወታደራዊው ክንፍ ጋር ባላቸው ሚና ይታወቃሉ።
•••
አረጋዊ ትግሉ ላይ የነበሩ በርካታ የትግራይ ተወላጆችን በመግደልም የሚወቅስዋቸው አሉ፡፡ አረጋዊ በርሄን የመለስ የስብሃትና የአባይ ፀሓዬ ቡድን በ1980 መፈንቅለ ሥልጣን አድርጎባቸው ከድርጅቱ ያባረራቸው ሲሆን እሳቸው ስደት ወጥተው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል::
“When, after building up a secret power base of loyalists within the TPLF, Meles Zenawi seized control of it in an internal coup, Aregawi finally split from the movement he had helped to build. He had enough friends to be able to escape with his life, first to Sudan and then to Holland.”
•••
እስካሁንም አረጋዊና ስብሃት ነጋ እንደ ጠላት እንደሚተያዩ ከውስጠ አዋቂዎች የሚነበበው ጽሐፍ ይገልጻል፡፡
•••
ከብዙ ዓመታት በኃላ አረጋዊ ጠልፈውት የነበረውን እንግሊዛዊ ጋዜጠኛ ራሳቸው ቤት አስጠርተው ይቅርታ የጠየቁት ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ህወሓት ያካሄደችው ውጊያ ትክክል እንዳልነበር ጠቅሰውለትም ነበር።
ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡
•••
እኔም ይቅርታ ይደረግልኝና፤ ያ የዚያ ትውልድ ፖለቲከኛ ጠርቶ አይጠራም። አንዴ ጭንቅላቱ የተወጋ ነው፡፡ ይቅርታው እንዳለ ሆኖ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ራሳቸውን ቢያገሉ ምኞቴ ነው።
We need new blood politicians. Please you the so called 1960s politicians,  you  were directly and indirectly responsible for the mess created in the country, it is time for you guys to give up, please retire from Ethiopian politics. We had enough of your venom.Leave the spot to new blood  young politicians.
 ምንጭ-  ዘ አዲስ
ሻሎም!  ሰላም!
Filed in: Amharic