>

የማፍያ ቡድኑ መስራችና መሪ ማን ነው? የት ነው?  (ስዩም ተሾመ)

የማፍያ ቡድኑ መስራችና መሪ ማን ነው? የት ነው? 
ስዩም ተሾመ
በራሱ ጥሮ-ግሮ በላቡ ሃብታም የሆነ አንድ የትግራይ ተወላጅ በሆነ ግዜና ቦታ ለሆኑ ሰዎች የተናገረውን ነገር ከማስገረም አልፎ በጣም ያስቃል። ይህ ባለሃብት ከጓደኞቹ ጋር ከአንድ ካፌ ሰብሰብ ብለው እየተጫወቱ ሳለ የባንክ ባለሞያ የሆነው ጓደኛቸው የባንኩ ዘርፍ እንዴት ያለ አዋጪ እንደሆነ በመጥቀስ በዚያ ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ይወተውታቸዋል። በመጨረሻ ተሳካለት አንድ ላይ የተሰበሰቡት ሃብታሞች እያንዳንዳቸው የ10 ሚሊዮን ብር ቼክ በመስጠት አዲስ ባንክ ለማቋቋም ይስማማሉ። የባንኩ መጠሪያ ስም “አንበሳ ባንክ” እንዲሆን እዚያው ይወስናሉ። የተጠቀሰው የባንክ ባለሞያ ተሯሩጦ ሁሉን ነገር ይጨርሳል። ከተጠበቀው በላይ አክሲዮን በመሸጥ የዛሬው አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ይመሰረታል። ባለሞያውም የባንኩ ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን መስራት ጀመረ። ባንኩም ትርፋማ እየሆነ መጣ፣ ካፒታሉ ብዙ መቶ ሚሊዮኖች ደረሰ። ታዲያ አንድ ቀን የባንኩ ዋና ስራ አስኪያጅ መጀመሪያ ላይ ከተጠቀሰው ጓደኛው ጋር በመምጣት “በቃኝ…. በቃኝ … ሃላፊነቱን ውሰዱልኝ። ከዚህ በኋላ በኃላፊነት መስራት አልፈልግም” እያለ መወትወት ይጀምራል። “ምክንያትህ ምንድነው?” ቢባል ለመናገር አሻፈረኝ አለ። ቢባል-ቢሰራ አልናገርም ካለ በኋላ ጓደኛው በብዙ ጥረት ካግባባው በኋላ ምክንያቱን ይናገራል። የመሰረተውን ባንክ ለቅቆ ለመውጣት ያስገደደው #ህወሓት የተባለው ማፍያ ቡድን ዋና መሪ ያለ #ብድር ማስያዣ 300 ሚሊዮን ብር ከአንበሳ ባንክ ተበድረው መውሰዱ ነው። ከብዙ ልመና እና ሽምግልና በኋላ  አጎቴ ለወሰደው ብድር ማስያዣ እንዲያቀርብ ይደረጋል። ቅድም ያልኳችሁ ባለሃብትም በ10 ሚሊዮን ብር የገዛውን አክሲዮን ለመሸጥ እንደሚፈልግ ሲናገር የሰማው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ልክ #በሲዲኒ_ኦሎምፒክ በሮጠበት ፍጥነት አክሲዮኑን በ20 ሚሊዮን ብር ላፍ ያደርገዋል። ታታሪ ያልኳችሁ ባለሃብት ቀስ ብሎ ራሱን ከማፊያ ቡድኑ አራቀ፡፡ ነገር ግን የዚህ ማፊያ ቡድን መስራችና መሪ ማን ነው? በህወሓት የትጥቅ ትግል እና በኢትዮጵያ ፖሊቲካ ውስጥ የሚጫወተው ሚና እና የሚፈጥረው ተፅዕኖ ምንድነው? እነዚህን እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ነገ በሰፊው እንመለከታለን።
Filed in: Amharic