>
5:13 pm - Wednesday April 20, 5644

ጠላት ምን ማለት ነው? (አብርሀ በላይ)

ጠላት ምን ማለት ነው?
አብርሀ በላይ
* ህወሀት ማለት በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት መላ ሀገሪቱ ላይ የተጠመጠመ ድራጎን ነው መስሎ የሚታየኝ።
ዛሬ ላይ ይችን ቀን ለማየት ሲሉ ህይወት እስከማጣት አካል እስከመጉደል ዋጋ በከፈሉ የህዝብ ልጆች መስዋእትነት ድራጎኑ አናቱን ቢመታም ዛሬም አፈር ልሶ ለመነሳት እያጣጣረ ነው!
ረዘም ላለ ጊዜ በኢትዮሚድያ በእንግሊዝኛ ስጽፍ፣ መለስ ዜናዊ በታሪካችን ተወዳዳሪ ያልተገኘለት የኢትዮጵያ ጠላት ብዬ ነበር የምገልጸው (መለስ ዜናዊ ስል በሱ ዙርያ ተኮልኩለው የኖሩት አውሬዎችንም ያጠቃልላል)። ታድያ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ፣ ለምን መለስ እና የህወሃት ሰዎች “ጠላት” ትላቸዋለህ የሚሉኝ ሰዎች ነበሩ። መለስ እና 100% እንደየግሉ ድርጅት ሲቆጣጠረው የነበረውን ህወሃት ያለምንም ጥርጥር ጠላት ብሎ መግለጽ ሲያንሰው ነው።
ጠላት ምን ማለት ነው?
የአንድ ሀገር ታሪክና ህዝቧን የሚያዋርድ ሰንደቅ አላማዋን የሚያንቋሽሽ ሀገርን ወደብ አልባ አድርጎ የትናንሽ ሀገሮች ጥገኛ እንድትሆን የታገለ – ህዝቡ አንድነት እንዳይኖረው በዘር የሚከፋፍል፣ እርስ በርሱ እንዲጋጭ ብዙ ሴራ ሲሸርብ የሚኖር የወጣቱ ሀገራዊ ስሜት የሚገድል አማራው፣ ኦሮሞው፣ ትግራዩ ወዘተ በየክልላቸው የተለያዩ፣ አንዱ ካንዱ ክልል ጋር የሚያጋድል “ታሪክ” ብሎ ጥላቻን በትምህርት ስም እንዲሰጥ የሚያደርግ፣
የድሃን ህዝብ ሀብት በወረራ መልክ የሚዘርፍ፣ አገር ስጋዋን በልቶ አጥንቷንም የሚግጥ ወጣቱ ተምሮም ስራ እንዳያገኝ አውቆ ተስፋ ቆርጦ ወደ ስደት አለም እንዲጠፋ የሚያደርግ – ወጣቱ ፖለቲካዊ ብስለት ኖሮት ለመብቱ እንዳይነሳ የልዩ ልዩ አደንዛዥ ዕፅ ሰለባ እንዲሆን የሚያመቻች ታሳሪዎችን በቁማቸው የሚያሰቃይ፣ አሰቃይቶም የሚገድል፣ ካልገደለም አካለጎደሎ ወይም የአ እምሮ በሽተኛ እንዲሆኑ የሚያደርግ –
በታሪክ ያልተሰሙ ዘግናኝ ወንጀሎችን የሚፈጽም – ለምሳሌ በታሳሪዎች መሀል ግብረሰዶምን ማስፋፋት የሚሰራ…. በአጭሩ ትውልድ ገዳይ ነው።
ህወሃት (ትህነግ) ኢትዮጵያን ለ27 አመታት ሲገዛ ለአንድ አፍታም ቢሆን ኢትዮጵያ በኢትዮጵያዊ እጅ ነች ያለችው ብዬ አስቤውም አላውቅ።
እንደውም ህወሀት ማለት በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት መላ ሀገሪቱ ላይ የተጠመጠመ ድራጎን ነው መስሎ የሚታየኝ።
ዛሬ ላይ ይችን ቀን ለማየት ሲሉ ህይወት እስከማጣት አካል እስከመጉደል ዋጋ በከፈሉ የህዝብ ልጆች መስዋእትነት ድራጎኑ አናቱን ቢመታም ዛሬም አፈር ልሶ ለመነሳት እያጣጣረ ከመሆኑም በላይ በየ ቤቱ (በየክልሉ) የጣለው እንቁላልም እየተፈለፈለ ቀድመው የተፈለፈሉትም የደም ግብራቸውን ለማስገባት፣ የማይጠረቃ ሆዳቸውን ለመሙላት፣ ቢሳካም ያጡትን ስልጣን ለማስመለስ፣ ያም ካልሆኑ አገሪቱን እና ህዝቧ ላይ የማያባራ የመከራ እሳት እያነደዱ ዳር ሆነው ለመሞቅ ያለሙ ፋሽስቶች እንኳንስ ለተቀረው ህዝብ ወጥተንበታል ለሚሉት ዛሬም በጨነቃቸው ሰአት መሸሸጊያ ላደረገት ህዝብ የማይራሩ ክፉ ጠላቶች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ህዝብ ለ27 አመታት በዘለቀ የከፋፍለህ ግዛ ፋሽስታዊ አስተዳደራቸው እንኳን ያለነውን መጭውን ትውልድ ገዳይ መሆናቸውን ያየውና የሚመሰክረው ሀቅ ነው።
 አሁን ያለው ጉዳይ ጠላት ያዋረዳትን ሀገር እንዴት ክብሯን እናስመልስ የሚል ይሆናል። ይህ ደግሞ ቀጣዩ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ፣ ምንም ቢሆን “የናቴ መቀነት አደናቀፈኝ” ሳንል፣ ጠ/ሚ አብይ አህመድ የጀመሩትን ጉዞ በጽኑ ሀገራዊ ፍቅርና እምነት ደግፎ መጓዝ ነው የሚል ሙሉ እምነት አለኝ።
Filed in: Amharic