>

ክቡር ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳን ይተዋወቁ! (ዳንኤል ረጋሳ)

ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ኦህዴድን የተቀላቀሉት የደርግ ስርዓት ከመውደቁ ከጥቂት ወራት በፊት ገና በለጋ የወጣትነት እድሜያቸው በ1983ዓ.ም ነበር፡፡
~ ከመነሻው የፖለቲካ ፍላጎታቸው እና እውቀታቸው ከፍተኛ የነበረው አቶ ለማ መገርሳ እንደ ድርጅት ምርጥ ካድሬነት ወጥቷቿል፡፡
~ ክቡር አቶ ለማ መገርሳ በተለያዩ ድርጅታዊ የካድሬ መዋቅር ውስጥ የተለያዩ ግዳጆችን በብቃትና በታማኝነት ተወጥቷል፡፡
~ ታጋይ ለማ መገርሳ ከሽግግር ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በተለያዩ ክልላዊ የፀጥታ እና ደህንነት መዋቅር ውስጥ በተለያዩ ደረጃዎች ላይ ከፍተኛ ልምድ አካብቷል፡፡
~ አቶ ለማ መገርሳ ኦህዴድ በክልሉ ህዝባዊ መሰረቱን እንዲያሰፋ የተለያዩ ፀረ-ህዝብ ድርጅቶችን በመዋጋቱ ረገድ እጅግ ውጤታማ ስራን በሰፊው ሰርቷል፡፡
~ ተጋይ ለማ መገርሳ በድርጅት ደረጃ ከተራ ታጋይ እስከ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና ስራ አስፈፃሚ አልፎም የድርጅቱ ሊቀመንበር እስከመሆን ደረጃ ደርሷል፡፡

በመንግስት_መዋቅር_ደረጃ
~ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ሰርቷል፡፡
~ የኦሮሚያ የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሰርቷል፡፡
~ የኦሮሚያ ንግድ ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሰርቷል፡:፡
~ የጨፌ ኦሮሚያ ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ሆነው የሰሩ ሲሆን
~ በ2009 ዓ/ም መጀመሪያ አከባቢ ኦህዴድ ባካሄደዉ የጥልቅ ታህድሶ ክቡር አቶ ለማ መገርሳ የኦህዴድ ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ለመሆን በቁ።

የትምህርት_ደረጃቸውን_በተመለከ
~ በPolitical Science & International Relations የመጀመሪያ ዲግሪ ከAddis Ababa University አግኝቷል፡፡
~ በInternational Relations የማሰተርስ ዲግሪ ከAddis Ababa University ከፍተኛ ውጤት በማስገብ አግኝቷል፡፡
~ በPeace & Security የPh.D Doctorate Degreeያቸውን ከጥቂት ወራት ቡኃላ ያጠናቅቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአመራር_ጥበባቸውን_በተመለከተ
~ ክቡር አቶ ለማ መገርሳ እጅግ የተረጋጉ፤ ችግሮችን የሚጋፈጡ፤ ለውድቀት የማይንበረከኩ፡ ሁሌም በህዝብ ውስጥ የሚኖሩ፡ ቆራጥ የውሳኔ ሰው ናቸው፡፡
~ ታጋይ ለማ መገርሳ በአመራር ጥበባቸው እጅጉን አሳታፊ፤ እጅጉን ዴሞክራት፤ እጅጉን ታታሪ እና ምርጥ አዳማጭ ናቸው፡፡
~ ታጋይ አቶ ለማ መገርሳ ሲናገሩም የሚናገሩለት አውዲየንስ የሚመጥን ቃላት የሚጠቀሙ፤ ከሰው ጋራ ለመግባባት የማይከብዳቸው፡ ነገሮችን ከተለያዩ አቅጣጫ መቃኘት እና ማሰላሰል የሚችሉ፤ በውጥረት ውስጥ የሚደምቁ፡ በችግር ውስጥ የሚጠነክሩ ብቃታቸው በስራቸውና በስራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም በትግል አጋሮቻቸው የተመሰረከላቸው ብቁ አቢዮታዊ ዴሞክራት አመራር ናቸው፡፡
~ ክቡር አቶ ለማ መገርሳ በኦሮሞ ወጣቶች ዘንድ እጅጉን የሚወደዱ፤ በሙሉ የካድሬ መዋቅር ውስጥ በውሳኔ ሰጪነታቸው እና በዴሞክራት ብሔርተኝነታቸው የሚወደዱ፤ የሚከበሩ እና የሚደነቁ ዴሞክራት መሪ ናቸው፡፡
~ ድህነት በእውቀት ጥይት እንጂ ሊሸነፍ እንደማይችል ፅኑ እምነት ያላቸው ታጋይ ለማ መገርሳ ለእውቀት ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ፡፡ ለራሳቸውም ጥሩ አንባቢ ናቸው፡፡ ከሁሉ በላይ ግን አቶ ለማ መገርሳን ካዩ በእጃቸው መጽሓፍት እንደማያጡ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ለኦሮሚያ ብቻም ሳይሆን ለሀገራችን ኢትዮጵያም ጭምር ተስፋ የሆነ ህዝባዊ መሪ ናቸዉ።
እድሜና ጤና ለፕሬዝዳንት ለማ!

Filed in: Amharic