>
5:13 pm - Monday April 18, 9036

ናዚዝም በጀርመን ፣ ፋሽዝም በጣሊያን ቢቀበሩም በኢትዮጵያ ትንሣኤ አግኝተዋል!! (ያሬድ በጋሻው)

– የትግሬ-ናዚዎች አዋጅ፦ «ዐማራን ከምድረ-ገፅ እናጠፋለን!»

– «ገረብ ገረብ ትግራይ፣ መቃብር ኣምሓራይ»  

ወያኔ የተመሠረተበት ዓላማ እና ተልዕኮ በድርጅቱ ማኒፌስቶ በግልፅ የሠፈረው አቋሙ ነው። ወያኔዎች ተዋጊዎቻቸውን ከሚቀሰቅሱባቸው መፈክሮች «ገረብ ገረብ ትግራይ፣ መቃብር ኣምሓራይ» የሚል ይገኝበታል፤ ትርጉሙም «የትግራይ ተራሮች የዐማራ መቀበሪያ ይሆናሉ» ማለት ነው። ስለዚህ ዛሬም ዐማሮችን በነገዳቸው ለይቶ መፍጀት ከዚህ የትግሬ-ወያኔዎች የትግል መግለጫ የመነጨ፣ ግቡም የዐማራን ነገድ ከምድረ-ገፅ ማጥፋት እንደሆነ ምንጊዜም ሊዘነጋ አይገባም።

ናዚዝም እና ፋሽዝም በሁለት የተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ተፈጥረው በሁለት የተለያዩ ሥያሜዎች ቢጠሩም መገለጫ ባህርይዎቻቸው ተመሣሣዮች ናቸው። ናዚዝምም ሆነ ፋሽዝም የፓርላማ ዲሞክራሲን አይቀበሉም። ለእነርሱ ብሔረተኝነት የሚገለፀው በዘር (በጎሣ ወይም በነገድ) ላይ በተመሠረተ መሥፈርት ላይ ስለሆነ የርዕዮታቸው መሠረት ሁሉ ዘረኝነት ነው። ለናዚዎች እና ለፋሽስቶች የቡድን ማለትም «የጎሣ ወይም የነገድ» መብት ከሁሉም መብቶች በላይ ስለሆነ የግለሰብ መብት ሥፍራ የለውም። በተለይ ደግሞ ናዚዎች «ምርጥ የሆነው የአርያን ዘር ነን» ብለው ስለሚያምኑ ዘራቸውን ከሌላው ዘር ሣያቀላቅሉ ማራባት መርሆዋቸው ነበር፣ ነውም። ናዚዎች ለፖለቲካ ግባቸው መቀስቀሻ ፀረ-አይሁዳዊነት ዋና መፈክራቸው ስለነበረ ከ6 ሚሊዮን የማያንሱ አይሁዶችን በአሠቃቂ ሁኔታ በግፍ ጨፍጭፈዋል። ለፋሽስት ጣሊያኖች ዋና ጠላታቸው «ኢትዮጵያዊ» በተለይም ደግሞ «ዐማራ» የሚባለው ዘር ስለነበረ ኢትዮጵያን በወረራ በያዙበት 5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን የማያንሱ ኢትዮጵያውያንን በመርዝ ጋዝ፤ በቦንብ፣ በመጥረቢያ፣ በእሣት በማጋዬት እና በሌሎችም አሠቃቂ መንገዶች ጨፍጭፈዋል። በታሪክ ተመዝግቦ እንደሚገኘው በፋሽስት ጣሊያኖች በብዛት የተጨፈጨፉት ዐማራዎች ነበሩ። ናዚዎች እና ፋሽዝቶች በነፃ ገበያ መርሆ የሚመራ የኢኮኖሚ ሥርዓት አይቀበሉም። ስለዚህ የመሠረቱት የኢኮኖሚ ሥርዓት በዘር ትሥሥር እና በሥውር ሤራ ላይ የተመሠረተ የፋይናንስ ካፒታሊዝምን የጀርባ አጥንት አድርጎ የሚንቀሣቀስ የማፍያ ካፒታሊዝም ነበር። በፖለቲካ አመለካከታቸውም ዜጎቻቸውን ለፍፁም አምባገነናዊ አመራር ታዛዥ የሚያደርግ ሥርዓትን ያራምዳሉ። ስለሆነም የሊበራል ዲሞክራሲንም ሆነ በተፃራሪ የቆመው የግራ ርዕዮተ-ዓለም «ኮሚኒዝምን» አምርረው የሚጠሉ እና የሚታገሉ ነበሩ፣ ናቸውም። ሁለቱም እኒህን የርዕዮተ-ዓለማቸውን ምሦሦዎች ያቆሙት «ውሽት ሲደጋገም ወደ እውነቱ ይጠጋል» በሚሉት የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ መሠረት ላይ ነበር። ከላይ የተዘረዘሩትን ለሚመለከት የትግሬ-ወያኔዎች ቀዳሚውን የርዕዮተ-ዓለም መሠረታቸውን ያገኙት ከጀርመን ናዚዎች እና ከጣሊያን ፋሽስቶች መሆኑን ለመገንዘብ ይችላል። ለትግሬ-ወያኔዎች ሁለተኛው የርዕዮተ-ዓለማቸው መሠረት ደግሞ የኮሚኒዝም አመለካከት ነው። አንድ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው «እንዴት ተደርጎ እኒህን ሁለት ፍፁም ተፃራሪ የሚመስሉ ርዕዮቶች አንድን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለመምራት በተጣመረ ሁኔታ መርሆ አድርጎ መቀበል ይቻላል?» ብሎ ሊጠይቅ ይችላል፣ ተገቢ ጥያቄም ይሆናል። መልሱ ደግሞ «የትግሬ-ወያኔዎች በሚሄዱበት አቅጣጫ ከተሄደ ይቻላል፤» ነው። ለዚህ እንዲረዳ የትግሬ-ወያኔዎችን የመጀመሪያውን የ1968 ዓ.ም. ማኒፌስቶ በከፊል መመልከቱ ይጠቅማል።

የትግሬ-ናዚ-ወያኔዎች ገና ከጥንስሣቸው ጀምሮ ለዐማራ ሕዝብ ያላቸውን ጥላቻ እና ያንንም የመረረ ጥላቻቸውን እስከ ዘር ማጥፋት በሚደርስ እርምጃ ከመግለፅ የቦዘኑበት ወቅት የለም። ይህ ያልተገለፀለት ሰው ቢኖር ከገሃዱ ዓለም ወጥቶ በተምኔታዊ የቅዠት ኅዋ ውስጥ ራሱን የደበቀ ብቻ ነው። የትግሬ-ወያኔዎች በዐማራ ሕዝብ ላይ ከፈፀሟቸው አያሌ ከሆኑት ናዚያዊ ተግባሮቻቸው መካከል ዋና ዋናዎቹን አለፍ አለፍ እያሉ መጥቀስ ለማስታወስም ያህል ይረዳል።

ገና ሲሽፍቱ በትግራይ ውስጥ ብቻ በሚነቀሣቀሱበት የመጀመሪያዎቹ ሦሥት ዓመታት እነርሱ ቀዳሚ የዘር ማፅዳት ሠለባ ያደረጓቸው እዚያው ትግራይ ውስጥ በሥራም ሆነ በሌላ ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ምክንያት ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች ነበር። እንዲያውም ከእነዚያ ዐማሮች መካከል አንዳንዶቹ ከትግሬዎች የተጋቡ እና የተዋለዱ ነበሩ። ለትግሬ-ወያኔዎች ግን እኒያ ሰዎች ዐማሮች ሰለሆኑ መወገድ ነበረባቸው። ስለዚህ አንድ በአንድ በወረንጦ እየለቀሙ ጨፈጨፏቸው።

ከ1971 ዓ.ም. ጀምሮ ወያኔ ከትግራይ ወደ ጎንደር የመስፋፋት ጦርነት አድማሱን ሲያሠፋ የመጀመሪያ እርምጃው በወልቃይት እና ጠገዴ የሚኖሩ የጎንደር ዐማሮችን በጅምላ መፍጀት ነበር። እስከዛሬ ምን ያህል የወልቃይት እና የጠገዴ ዐማሮችን እንደጨፈጨፉ በአሃዝ ለይቶ ለማስቀመጥ ቢከብድም በ20 ሺህዎች የሚቆጠሩትን ከምድረ ገፅ እንዳጠፉ፣ ከ70 ሺህ የማያንሱትን ደግሞ ከጥንት አባቶቻቸው ርስት አፈናቅለው ስደተኛ እንዳደረጓቸው ይታወቃል። ወያኔዎች የጎንደር ግዛት የሆነውን የወልቃይት ፣ የጠገዴ እና የፀለምት አካባቢዎችን «የትግራይ ክልል» ብለው ነጥቀዋል። በአካባቢውም ከተለያዩ የትግራይ አውራጃዎች ያመጧቸውን የራሣቸውን ዘር አሥፍረውበታል።

ሥልጣን ከያዙበት ከግንቦት 1983 ዓም ጀምሮ በመላ ኢትዮጵያ ዐማሮችን፦ «ነፍጠኞች፣ ትምክህተኞች፣ አድሃሪዎች፣ ጨቋኞች፣ የትግራይ ሕዝብ ደም መጣጮች፣ ወዘተርፈ» እያሉ ከአገራቸው አፈናቅለዋል፣ ጨፍጭፈዋል። በተለይም ከግብር አጋሮቻቸው ከሻቢያ ፣ ከኦነግ እና ከኦብነግ ጋር በመሆን በሐረርጌ (በበደኖ፣ በሐብሩ፣ እና ሌሎች ሥፍራዎች)፣ በአርሲ (በአርባ ጉጉ እና ጢቾ)፣ በወለጋ፣ በጅማ፣ በኢሉባቦር፣ በባሌ፣ በሲዳማ፣ በጌድኦ፣ በወላይታ፣ በከፋ፣ በጉራፈርዳ፣ በመተከል፣ በአሶሳ እና በሌሎችም አካባቢዎች በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዐማሮችን በአሠቃቂ ሁኔታ ፈጅተዋል።

ከ1984 ዓ.ም. ጀምሮ «ብረት ማስፈታት» በሚሉት ዘመቻ ዐማራው ሙሉ በሙሉ ትጥቁን እንዲፈታ ተደርጓል። በተለይም «የዐማራ ክልል» ብለው በሠየሙትና አብዛኞቹ የዐማራ ተወላጆች በሚኖሩበት አካባቢ ይህንን ዘመቻ በበላይነት የመራው ኤርትራዊው በረከት ስምዖን ነው። ዛሬ ዛሬ የዐማራ ተወላጅ እንኳን የጦር መሣሪያ ይቅርና የብረት ጅንፎ ያለው ዱላ መያዝ ጦር መሣሪያ እንደመታጠቅ ተቆጥሮበት ራሱን ከትንሽ አውሬ የሚከላከልበት ዱላ እንኳን መያዝ አይችልም።

ከ1985 እስከ 1987 ዓ.ም. ባካሄዱት «ሽፍታ ምንጠራ» ብለው በሠየሙት ዘመቻ ከዐማራው መካከል ንቃተ-ኅሊናቸው ከፍ ያሉትን እና «ለትግሬ-ናዚያዊ አገዛዝ አይንበረከኩም» ብለው የሚያስቧቸውን ዐማራዎች እየለቀሙ አሥረዋል፣ ደብዛቸውን አጥፍተዋል፣ ገድለዋል።

ከ1986 እስከ 1987 ዓ.ም. ዐማራውን በሦሥት መደቦች ከፋፍለው፦ የወያኔ ኮር አባል፣ ተራ ዜጋ እንዲሁም ቢሮክራት እና ፊውዳል ብለው መድበው መሬት አከፋፍለዋል። የመሬት ድልድል ሲያደርጉ በገጠሩ የዐማራ ማኅበረሰብ መካከል የመደብ ልዩነት በመፍጠር ዐማራው እርስ በእርሱ እንዲፋጅ ሲያደርጉ፣ በተለይም ደግሞ አብዛኛውን ዐማራ የኢኮኖሚ ዐቅሙ የተዳከመ እና ፍፁም በድነህት የሚማቅቅ ምስኪን አድርገውታል።

ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ በምሥራቅ ወለጋ ለዘመናት ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች «የጦር መሣሪያ ታጥቃችኋል፣ የኦሮሚያን መሬት ለግላችሁ አድርጋችኋል፣ የኦሮሚያ የቦታ ሥሞችን የዐማራ ስም አውጥታችሁላቸዋል፣ የከብት ዝርፊያ ትፈፅማላችሁ፣ ደን ትመነጥራላችሁ» እና የመሣሠሉትን ሠበቦች በመደርደር ከ12 ሺህ የማያንሱትን አፈናቅለዋቸዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩትን ዐማሮች ደግሞ የአካባቢው የወያኔ ሎሌ የሆኑት የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ታጣቂዎች ፆታ እና ዕድሜ ሣይለዩ በአሠቃቂ ሁኔታ ጨፍጭፈዋቸዋል። የተፈናቀሉት ዐማሮች ከነበሩበት ሥፍራ ተባርረው ጎጃም ክፍለሀገር አገው ምድር አውራጃ ውስጥ ጃዊ የሚባል እጅግ ሞቃታማ እና በወባ ወረርሽኝ በሚጠቃ ወረዳ እንዲሠፍሩ ተደርገው አብዛኞቹ በወባ ወረርሽኝ እንዲያልቁ ተደርገዋል።

ከሚያዝያ 16 ቀን 2001 ዓ.ም. ወዲህ ከአዲስ አበባ እና ከሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች “የግንቦት 7 ንቅናቄ አባሎች ናችሁ” ተብለው ከታሠሩት ከ37 በላይ የሲቪል ፣ የደህንነት ፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የወታደር እስረኞች መካከል አብዛኞቹ ዐማሮች ናቸው። በእኒህ እሥረኞች ላይ የወያኔ መርማሪ ፖሊሶች ካደረሱባቸው ዘግናኝ ግርፋት ዓይነቶች መካከል፦ የወንድ የዘር ብልት ማኮላሸት፣ በኤሌክትሪክ መጥበስ፣ ጥፍር መንቀል፣ ከባድ ድብደባ፣ በአስጨናቂ ሁኔታ በካቴና ጠፍሮ ማሠር እና ከጣሪያ ላይ ማንጠልጠል፤ እንቅልፍ መከልከል፣ በርሃብ እና በውኃ ጥም ማሠቃዬት፣ ጫካ ውስጥ ወስዶ ግድያ እንደሚፈፀምበትና ሬሣው ለአውሬ እንደሚጣል ማስፈራራት ይገኙባቸዋል። እኒህ እሥረኞች በአካል የተሠቃዩት ሣያንስ እጅግ ቅስም-ሠባሪ ዘለፋ ለመስማትም ተገድደዋል፦ ከወያኔዎቹ አረመኔ ገራፊዎች ከሚወጡት ቃላት ውስጥ፦ “ትምክህተኛ ዐማራ፣ ግም ዐማራ ፣ ብስብስ ዐማራ፣ ሽንታም ዐማራ፣ ፈሪ ዐማራ፣ በኤድስ ቫይረስ የተበከለ ደም እንወጋሃለን፣ ከሃምሣ ጋይንት አንድ አጋንንት ይሻላል አንተ ሆዳም ጋይንቴ፣ ዘር-ማንዘርህን ቀሚስ አልብሰን የወጥ-ቤት ሠራተኛ አድርገን እንገዛዋለን፣ አንተ ደም መጣጭ ጎጃሜ እናቃጥልሃለን፣ ዘረ-ቆሻሻ ዐማራ፣ ወዘተርፈ” የሚሉ ይገኝባቸዋል። እኒህ እሥረኞች በወያኔው የጨረባ ፍርድ ቤት እስከ ሞት የሚደርስ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

እነዚህ ሁሉ የትግሬ-ወያኔዎች የዐማራ ጭፍጨፋ ድርጊቶች ከራሣቸው አንደበት እና ዘገባ ማረጋገጥ የተቻሉ ናቸው። በተለይም በ1999 ዓ.ም. የትግሬ-ወያኔዎች ባካሄዱት የሕዝብ ቆጠራ «አረጋግጠናል» ብለው ለሕዝብ ይፋ ባደረጉት መረጃ መሠረት ከ1989 እስከ በ1999 ዓ.ም. በነበሩት 10 ዓመታት ብቻ 2 ሚሊዮን 500 ሺህ ዐማሮች የደረሱበት አልታወቀም ብለዋል። በእርግጥ ይህ የአሃዝ አገላለፅ ግራ የሚያጋባ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን በራሣቸው በወያኔዎች የታመነውን ጉዳይ ከማስተባበል ይልቅ ከጨፈጨፏቸው የዐማራ ነገድ ተወላጆች መካከል ከዚህ ቁጥር ውስጥ ያልተካተቱት ምን ያህል እንደሆኑ ማጣራቱ ይበልጥ ትርጉም ይኖረዋል።

ህወሀት አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ አማራ ብሔር ላይ የወረደው ጭፍጨፋ : እልቂትና ጥፋት ወደር ያለው አይመስልም:: ራሱ የኢትዮጵያ መንግስት እንዳመነው

https://www.youtube.com/watch?v=ikVl6auH83w ( fast forward it minute 7:10)

በሕዝብና ቤት ቆጠራ ውጤጥ እንደሚያሳየው 2.5 ሚሊዮን አማሮች የገቡበት አልታወቀም:: ምናልባትም ከ ጽዮናዊቷ እስራኤል ቀጥሎ ይሄን ያህል ቁጥር ያለው ሕዝብ የገባበት ሲጠፋ አማራ ሁለተኛው ሳይሆን አይቀርም::

በተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሚድያዮች እንደተዘገበውም ከወልቃይት እስከ ከፋ ድረስ ባለፉት 26 ዓመታት የአማራ ደም ያልፈሰሰበት : የአማራ ንብረት ያልወደመበት: አማራ በብሔሩ እየታደነ ” ወደ ሀገርህ: ተብሎ ያልተባረበበት ቦታና ዓመት የለም ማለት ይቻላል::

በቅርቡ የተፈጸመውን እንኳን ብናይ 2013 ላይ ጉራ ፈርዳ ላይ ከ 80 ሺህ በላይ አማሮችን – ባለስልጣናት አፈናቅለዋል:: ለዚህ መፈናቀል ምክንያት የሆነው ሽፈራሁ ሽጉጤም ታዥዤ ነው ማለቱን ኢሳት ዘግቧል:: 2014 ላይ ቤኒሻንጉል ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ አማሮች በግፍ ተፈናቅለዋል:: ተገድለዋል:: ደመቀ መኮንን በመግለጫቸው እንደገለጹትም ይሄ የተከናወነው በባለስልጣናት መሆኑን : ድርጊቱም ህገ ወጥና ወንጀል መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል:: 2015 ላይም የአማሮች ሰቆቃ አላለቀም:: ወንበራ ላይ እግጅ ዘግናኝ እልቂት መፈጸሙን አሁንማ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባንደበታቸው ገልጸዋል:: ራቅ ባሉትም አመታት በደኖ : ኢንቁፍቱ : ወተር : ላንጌ: እና መሰል ቦታዎች አማሮች ላይ የደረሰው ግፍ በባለስልጣኖች ሴራ እና ተንኮል እንጂ ባካባቢው ገበሬ አለመሆኑን ፕሮፌሰር አስራት በማያሻማ መልኩ አስቀምጠውት እንደነበር ይታወሳል::

በነዚህ ሁሉ እልቂቶች የአካባቢው ገበሬ እጅ የለበትም:: ያካባቢው ገበሬማ እስካሁን እኮ ከአማሮቹ ጋር ለብዙ ዘመናት ኖሯል::ጉራ ፈርዳ ላይ ያካባቢው ገበሬዎች ” አማሮቹን ለምን ታፈናቅላላችሁ ” በማለት ባለስልጣናትን ሲወቅሱ እንደነበር ቪ ኦ ኤ ዘግቧል:: በተለያዩ የኦሮሚያ ቦታዎች ላይም ያካባቢው አርሶ አደር ለተፈናቀሉት አርሶአደሮች እህልና ገንዘብ ለተፈናቃዮች እንዳዋጣ አሁንም ሚድያዎች ዘግበዋል::

ችግሩ ካርሶአደሮቹ ሳይሆን ” አማራ ጠላቴ ነው” በሚል ሰይጣናዊ እሳቤ ህሊውን ካሳመነው አካል ነው የዚህም ወደር የለሽ ጥላቻ መነሻው የጣልያን መርዝ ነው እንጂ : አማራ ለትግሬ ጠላቱ አልነበረም:: ትግሬም ላማራ ጠላቱ አይደለም:: ትግሬ ሲወረር አማሮቹ ደማቸውን ከትግሬው ጋር አፍሠዋል:: ጎንደርን ደርቡሽ ሲያጠቃት ትግሬው ለወገኑ ደሙን አፍሧል:: በኔ እነገስ እኔ እነግስ ሽኩቻ መኖሩ የማይካድ ታሪክ ቢሆንም ይሄን ያህል የመረረ ጥላቻንና በቀልን የሚያስቋጥር አይደለም:: አልነበረምም::

አማሮች ብቻ በመሆናቸው ንብረታቸው የተዘረፈው : ደማቸው የፈሰሰው አርሶአደሮች ደም እንደአቤል ደም ይጮሃል:: አንድ ቀንም የደማቸው ድምጽ የሰማይ አምላክ ዘንድ መድረሱ አይቀርም:; ደም አፍሳሹ ቃኤልም : ያለሀጥያቱ ደሙ የፈሰሰው አቤልም ፍርዳቸውን ያገኛሉ:: የአምላክም የተፈጥሮም ህግ ነውና ይህ መሆኑ አይቀርም:: የግፉ ጽዋም እየሞላ ይመስላል:: እስከዛው ግን “ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርማ ባይኖርም : ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም” እንዳለ ገጣሚ ;—– አረ ድሃን ማፈናቀል ማቅበዝበዝና መግደል ይብቃ:: ለነብስም : ለስጋም : ለልጅ ልጅም አይበጅም!!

Filed in: Amharic