>

አኖሌን አፍርሱ!!! (መንግስቱ ዘገዬ)

የኦሮሞ ተወካዩች ባህርዳር መገኘታቸውን ወደነዋል።አብሮ ለመኖር እንደዚህ ያሉ ኩነቶች ቱርፋታቸው የሚናቅ አይደለም ። እሰየው ነው! ደስ ብሎናል!!!  ኢትዮጲያዊነትን ህያው ለማድረግ ብዙ ጀግና ኦሮሞዎችና አማሮች ከሌሎች ወንድሞቻቸው ጋር  እልፍ ሺህ መስዋእት ከፍለዋል ። ያ አሻራ በዚህ ትውልድ ደምቆ ማየት  አጥንት ያለመልማል ።

ግን ደግሞ እኛ አማሮች በወንድሞቻችን የኦሮሞ ምድር ላይ አኖሌ የተባለ የጋንጩሩ ተስፋየ ገብረአብ ተረት ተረትና  ልብወለድ ስጋ ለብሶ  ወደ እውነት ተለውጦ አኖሌ የተባለ የበቀል ሃውልት ቆሞ ማየት እስከ አጥንት ድረስ ሰርስሮ የሚገባ  ሃዘን ከፈጠረብን ዘመናት አለፉ ።
ይህንን የጋንጩር ልብወለድ ሃውልት አብዝሃኞቹ ኦሮሞ ወንድሞቻችን ተረት ተረትና ልብወለድ ነው ሲሉ  መስከረዋል ።
በዚሁ ልክ አኖሌን እውነተኛ ታሪክ አድርገው ቂም የቋጠሩ የኦሮሞ ልጆችም እንዳሉ አውቃለሁ ። አኖሌ ተረት ነው ሲሉ ያወጁ የኦሮሞ ልጆች እወጃቸው  አይበቃም ።
ይህንን የቂም ሰንደቅ ገንድሶ መጣል ግድ ይላቸዋል ።
ኦሮሞዎች ይህንን በቀያቸው ላይ የተደነጎረውን የክፋት ልብወለድ ሃውልት አፍርሰው የጣሉ ቀን መተማመን ከቤታችን ይገባል ባይ ነኝ።
እነ ለማ መገርሳ የጀመሩትን የፍቅር መንገድ ዳር ይደርስ ዘንድ በነካ እጃቸው አኖሌን ያፍርሱ! !!! ያኔ መሰሪዎችና ተንኮለኞች አንገታቸውን ሰብረው ወደ ጉረኗቸው ይገባሉና! !!!! እንዲህም ያለ ነገር በሆነ ጊዜ ኦሮሞ ኬኛ አማራ ኬኛ የሚለው መዝሙር የትውልዱ ድምጽ ይሆናል! !!!

Filed in: Amharic