>

በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የኦህዴድ ዉሳኔ ተደስቻለሁ (ተክሌ በቀለ)

ኦህዴድ ይህን በማድረጉ ስብእናቸዉ  ከፍ ባሉ ሰዎች እየተመራ ለመሆኑ ማሳያ ነዉ! 

– በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የኦህዴድ ዉሳኔ ተደስቻለሁ (እንደግለሰብ)

ኣንድነት ከመፍረሱ በፊት የወቅቱ ስራ ኣስፈፃሚ እንድ ታሪካዊ ዉሳኔ ወስኖ ነበር፡፡የፓርቲዉን ፕሬዝደንትነት ስልጣን እየተለመኑ ስልጣን ለለቀቁት ለዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቤት መኪና ገዝቶ ለመስጠት ኮሚቲ ኣዋቀረ፡፡ኮሚቲዉን እኔ እንድመራ ተደርጎ ኣቶ በላይ ፈቃዱን፤ግርማ ሰይፉን፤ዳንኤል ተፈራን፤ሰለሞን ስዩምን፤ኣስራት ኣብረሃምን በህዝብ ግንኙነት ስራ ተመድበዉ እንዲሰሩ ተደረገ፡፡የፋይናንስና የዉጪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቲ ሃላፊዎችም የኮሚቲዉ ኣባላት እንዲሆኑ ተደረገ፡፡እቅድ ወጥቶ ተሳታፊ ባለድርሻ አካላት ከተለዩ በኃላ ሁለት ነገሮች ተከሰቱ፡፡
ኣንደኛዉ ዶ/ር ነጋሶ ዉስጣቸዉ ያሰገደዳቸዉን ነገር ኣደባባይ ኣዋሉት፡፡የፓርቲዉ ፕሬዝደንት እያሉ ከሚያራምዷቸዉ ሃሳቦች በተለየ የኦሮሞን ብሶት ብቻ ኣንጸባረቁ፤ኣንድነትንም በኣንዳንድ ጉዳዮች ስላልተስማሙ የምመራዉን ፓርቲ ኣላዉቀዉም ነበር ማለት ነዉ ኣሉ ተብለዉ የዉስጥ ቅሬታ ተፈጠረ፡፡ደጋፊዉን ለማንቀሳቀስ ትንሽ መታገስ ያሰፈልግ ነበርና ግዜ ስንጠብቅ ሁለተኛዉ ሁኔታ ተከሰተ፡፡ፓርቲዉ እንዲፈርስና ለግለሰቦች ተሰጥቶ እንዲፈርስ በዛ ሰፈር ሰዎች ተወሰነ፡፡እንደግለሰብ ብቻሳይሆን እንደኣመራር ሲያንገበግበኝ የኖረ ያልተሳካ ዉጥን ነበር፡፡
ኦህዴድ ይህን በማድረጉ ስብእናቸዉ ከፍ ባሉ ሰዎች እየተመራ ለመሆኑ ማሳያ ነዉ፡፡የተከበረም የተቀደሰም ተግባር ነዉ፡፡የስዪ ኣብረሃ ህግና የዶ/ር ነጋሶ ህጎች የስርኣቱን ቁንጮ ሰዎች ምቀኝነት፤ክፋት፤ተንኮል፤ጨካኝነት፤ትንሽነት….ማሳያ ኣድረጌ ኣያቸዋለሁ፡፡ደግሞ እሳቸዉን በስሜትም ለመጉዳት ቀጣዩን ጡረተኛ ፕሬዝዳንት የተንከባከቡበት ሁኔታ በጣም ያስተዛዝባል፡፡
ኦህዴድ ይህን ኣርጎት ከሆነ (ተጠራጣሪ እንድንሆን ስርኣቱ የፈጠረብን ችግር ነዉ) ኣሁንም ከፍ ከፍ እንዲል እየተመኘሁ እንደግለሰብ ለዉሳኔዉ ከብር ኣለኝ፡፡ካለደረገዉም ያደርገዉ ዘንድ ልባዊ ጥሪየ ነዉ፡፡ኣስበን ያልተሳካን ነገር የኦህዴድ ወንድሞቻችን በመፈፀማቸዉ ቢያንስ ለምስጋና ንፉግ መሆን የለብንም!!
የዶ/ሩ ስራ ሁሌም የሚዘከር፤የሚከበር ተግባር ነዉ፡፡የህዝብ ልጅ፤የግል ከብርና ጥቅም ብሎ ያልፈጠረባቸዉ ናቸዉ፡፡

Filed in: Amharic