>
5:13 pm - Tuesday April 19, 4968

በኢትዮጵያ ነፃ አውጭ እንጂ  መንግሥት አለ?!? (እሸቱ ቶኩማ)

እነዚህ ሰዎች እውን ኢትዮጵያዊ ናቸውን ?
ከሁሉ በላይ ሁሌም የሚያስቀይ ከተቃዋሚ ሚዲያና ከታላላቅ ሰዎች ሲነገር የምሰማው አንድ ነገር አለ። ” የኢትዮጵያ መንግሥት “ዕውን የኢትዮጵያ መንግሥት አላት?ሕውሓት ምንድን ነው?
ሕውሓት ማነው? ብለን ራሳችን ጠይቀናል? 

ሕውሓት ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነት እና የሥም አጠራሩ ምንን ያመለክታል?
ለምንድን ነው ኢትዮጵያን ለ25 ዓመት ወይም ለሩብ ምዕተ ዓመት ሙሉ በሙሉ ሁሉን ተቆጣሮ እየገዛ  በመንግሥት ሥም ነገር ግን “የትግራይ ነፃ አውጭ”
ትግራይን ከማን ነው ነፃ የሚያወጣት ?
* ከኢትዮጵያ ከሆነ እነሆ ኢትዮጵያ በመዳፉ ሥር ከወደቀች ዓመታትን አስቆጠረች ።
★ታዲያ የሕውሓት ሥህተቱ የት ላይ ነው ?  እውነቱ እየነገረን እኮ ነው ።
— እኛ ሕውሓትን ለምን አናምነውም ?  የትግራይ ነፃ አውጭ ነኝ ሲለን ፣ አይደለም ?  አንተ የኢትዮጵያ ነህ ። በግድም  መንግሥት ነህ እንለዋለን ።
የኢትዮጵያ መንግሥት አለመሆኑንም በተግባር ቢያሳየንም አሁንም  ኧረ በጭራሽ   !
አንተማ መንግሥታችን ነህ!
— ”አንቀበልም” ብንለውም  በተግባር ኢትዮጵያዊ አለመሆኑን  ለማሳየት  ከዚህ የሚከተለውን አድርጓል እያደረገም ነው ።።
1ኛ/ የሚገዛትን ሀገር ሀብት መሻማትና መዝረፍ ብቻ ሳይሆን ሌሎችን አካባቢ ወደ ትግራይ መጠቅለልና መከለል  ምን አመጣው?
2ኛ/ የኢትዮጵያን መሬት ከራሱ የተረፈውን  ለጎረቤት ሀገር በነፃ ማደል።
3ኛ/ ሁሉን  ምርጥ ምርጡ ለራሱ ሌላው ነሀገሩ ባይተዋር አድርጎ እሱ እየበላ ሌላውን የበይ ተመልካች ማድረጉ ።  በኢትዮጵያውያን ጭካኔ ሲፈፅም ምንም እንደ አንድ ሀገር ሰው የማይሰማው ።
4 ኛ/ ከወረራ በኋለም ከታላቋ ትግራይ ውጭ ያለነውን ሕብረተ ሰብ አብረን እንዳንኖር የሚያደርጉንን ሥራዎች ሁሉ በመፈፀም በማስፈፀም ብዙ የጥላቻና የተንኮል ተቋማትን ከመገንባትም ባሻገር ከመቶ ዓመታት በፊት ተፈፅሟል እያለ የሀሰት ሰነድና የውሸት ታሪክ እየፈበረከ  ሀውልትም ጭምር  አቁሟል ።
— ሥልጣንና የሀገሪቱን ንብረት በእጁ ስለሆኑ ፀረ ኢትዮጵያ ተግባሩን የሚፈፅሙለተፈን  የሌላ ጎሳ ወይም ብሔር አባላትን እየመለመለ እያሰለጠነ ያሰማራቸውል።  ሕውሓት አድርጉ ካላቸው ውጭ ምን ማለት የምይችሉ የደንቆሮዎችን ስብስብ በማቀፍ  አይሆንም  ቢሉም የዕለት ጉርስ የሚያገኙት ከሱ ነውና  የግድ አቤት ወዴት ብለው በናታቸውም ልጅ ላይ ይፈፅሙታል።
በኢትዮጵያ ካሉት ሕብረ ብሔር ሰዎች መካከል ሰዎችን ሲመለምል እና ሲሾማቸው የሰወችን ፕሮፊል በደንብ አጥንቶ ነው ።
በራሳቸው ሕሊና የማይመሩትን አድርባይ መሆን የሚችሉትን የፍርሀት መጠናቸው እጅግ ክፍ ያለውን ካልሆነም ኦቲዝም  (አዕምሮአቸው  የጫጫ) የተባሉትን ብቻ እንደማሚቶ ወይም እንደሮቦት  ግዑዝ አካል የመሰሉትን ነው ። ።
****ለዚህ መረጃ የሚሆነው መለስ ዜናዊ በሕይወት እያለ ፣ ከኢትዮጵያውያን ሁሉ መርጦ ምክትሉ ያደረገውን ሰው ልብ ይሏል ። ።
ይህ ሰው መለስ ከሞተም አመታትን ቢያስቆጥርም ነገር ግን   መለስ ገና አልሞተም  የተናገራቸውን ሳያሳስት እንደማሚቶ ያስተጋባል ችግሩ አንዳንዴማ  ቀኑንንም አመተ ምህረቱ ማለፉን የዘነጋው ይመስላል ።
ይህ መለሰን የተካው ግለሰብ አንዳንዴ ወደ አደባባይ ሲወጣ የሚናገራቸው በሙሉ መለስ በሕይወት እያለ ይናገር የነበረውን ነው ።
የሚናገረው ሀሳቡ የርሱ አለመሆኑና ከሰው የተወሰደ በመሆኑ አናዳንዴ ወቅቱ ያለፈበትንም  እርስ በርሱ የሚጣረስ መሆኑንም ልብ የማለት አቅሙን በውል የሚታይበት   ነው ።
ሀሰት እውነት የሌለበት ንግግር እያደረገም  ይገኛል ።
ችግሩ መለስ ታላቅ የተንኮል ሰው ነበረ ከመሞቱ በፊት እሱን እንዲተካ የወከለው ግለሰብ አሁን ላይ ላሉት የሕውሓት ሰዎችም እጅግ ጠቃሚ ገራም ፈረስ( በቅሎ) በመሆኑ ባለው እንዲቀጥልም ተስማምተዋል ።
በኔ ግምት በኢትዮጵያ ያለው መንግሥት በጠ/ ሚ  ኃይለ ማርያም  ደሳለኝ የሚመራው አይመስለኝም ።
ይህ ለአለም ሕብረተ ሰብ በሚመች በሞዴልነት የተቀመጠ ይመስለኛል
እውነተኛው መንግሥት  ስውሩ መንግሥት ነው ።
ልክ በፖለቲከኛው ኤርሚያስ ለገሰ በአዲስ አበባ “ባለቤት አላባዋ ከተማ” መጽሐፉ ላይ እንደገለፀው የሕውሓት  የካሳንችሱ ” ሥውሩመንግሥት ” ነው
5 ኛ/ ሕውሓት በ25 ዓመት የግዛት ዘመኑ ከሰራቸው የተሳኩለትና ያልተሳኩለትን ማየት እንችላለን
— ትግራይን ከሌላ ብሔር የፀዳች ቁጥር አንድ ክልልን ዕውን አድርጓል፣ ——ክልሏም በየዕለቱ እንደ አሜቫ ራሷን አያባዛች የምትገኝ አድርጓታል ፣
— ለትግራይ ታላቅ የኢኮኖሚ ሞኖፖል ኢፈርት የተባለ ግዙፍ ድርጅት መስርቷል፣ —በተቻለና አቅሙ በፈቀደው ያክል የኢንዱስትሪ ማዕከል ወደማድረጉ አሸጋግሯል ።
— በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኘውን ኡጋዴ ብሎ የከለለውን ከውጩ አለም በማግለል ራሱ ከሚመራው ፌዴራል ብሎ ያዋቀረው አካል ሳይቀር ስለኦጋን  ሚያውቀው አለመኖሩን ይታወቃል ኦጋዴን ላይ ምን እየተፈፀመ መሆኑን የሚያወቅ ከሕውሓት ሰዎች በስተቀር ማንም አያውቅም ።
ኢትዮጵያውያን የሚያውቁት ነገር አለመኖሩን የሚያመለክተው በኦጋዴን መንቀሳቀስም ሆነ መኖር የሚችሉት ከሕውሓት ጋር አብረው ይሰራሉ ተብለው የተገመቱት የኢትዮጵያ ሶማሌ የጎሳ አባላትና  እና የትግራይ ተወላጆች የሕውሓት አባል ብቻ ናቸው ።
በሱማልያ በጊዜው ስላጣን ላይ ያለው ፕሬዚዴንት በኦጋዴን በርካታ የዘር ማጥፋት ያካሄደ  ግለሰብ ነው ከዚህ ቀደም መረጃውን ለአለም መድረሱ ይታወሳል።
ኦጋዴንን ከኢትዮጵያ ሀገር ጋር ጋር ያላትን ግንኙነት በሙሉ በሚያሰኝ መልኩ ቢነጥሉም ለዛ ክልል ተብሎ ከፈተኛ ባጀት የሚመደበው ግን ከኢትዮጵያ ሕዝብ በግብር መልክ በሚሰበሰብ ገንዘብ ነው ።ኦጋዴን ከሕውሓቶች ውጭ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን  አይፈቀደም  ኦጋዴ ለኢትዮጵያ ባይተዋር ነች ።

በምስራቁ በኩል መረጋጋት እንዳይኖር  የሚጠቀምባቸውም በኦጋዴን የጎሳ አባላትን ነው ።
በክልሉ አማራ ሁነህ ከተገኘህ አማራ ሳይሆ ሀበሽ ተብለው እንደሚጠሩና ከፍተኛ ሰቆቃ የሚፈፀምባቸው እንደሆን ይነገራል ፣
ወደ ክልሉ  በምንም ዓይት መግባት አይፈቀድላቸውም ።
በምስራቁ የሀገራችን ክፍል በኦሮሞ ብሔሮችና በአፋሮችም ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት እየፈፀሙም ያሉበት ሁኔታም አንዱ ማሳያ ነው ።
አሁን ላይ የሚገኘውን የኦሮሞን ሕዝብ አመፅ ለማፈንም በሀረር በሚገኘው የኦሮሞ ሕዝብ ላይ ጭካኔ የሚፈፅሙት በሕውሓት በተደራጁ የሶማሌ ጎሳዎች አባል በሆኑ ልዩ ኃይል ተብለው የሚጠሩ ናቸው ።
የኦጋዴን ሶማሌዎች ራሳቸው ሳይወዱ በግድ ተይዘው የሚገኙ ሲሆን እለት ተዕለት የሚፀምባቸውን  ለውጩ ዓለም ዝግ ነው ማንም አያውቅም ።
በዚህ ሰዓት ከፍተኛ ረሀብ አለ ተበሎ ቢነገርም በኦጋዴን ያለውን ግን የዓለም ሕብረተ ሰብ ቀርቶ ለኢትዮጵያን ጀሮ  ወሬው  አይደርስም  ያሳዝናል።

6ኛ/   በጋንቤላ በኩል ምን እንደሚሰራ ማዩቱም ጣቃሚ ነው በጋንቤላ መስተዳድር በፕሬዚደንት ደረጃ የተሾሙት ሱዳናዊ ናቸው እውነተኛ ኢትዮጵያውያን አንጡራ ተወላጀች የአኟክና የመዠንገር ብሔር አባላት ተደጋጋሚ የዘር ማፅዳት ተካሂዶባቸዋል ይህንም በመፍራት አብዛኛዎቹ ተሰደዋል ።
ሕውሓት በሚመራው ቡድን የዘር ፍጅት የተፈፀመባቸው መሆኑ አስመልክቶ ከክልሉ ከመፈናቀል የተረፉት አካባቢውን ለቀው እንዲሰደዱ ተደርጓል ።
በሌሎችም የሱዳን ደንበር አካባቢ እየታየ ያለው ይህ ነው።
በጎንደር በኩል የሚታየው አዲስ ባለመሆኑ ደርግን ከስልጣን ከማስወገዳቸው በፊትም ይፈፅሙት የነበር በመሆኑ ለቀባሪ ማርዳት ነው።

Filed in: Amharic