>

ኳሱ በእጃቸው ቢሆንም በፈለጉ ጊዜ አተንፍሰው አልጫወትም፣ሲፈልጉ ነፍትው እንጫወት ማለት ብዙ ርቀት አይወሰድም (ግርማ ሰይፉ ማሩ)

ወዳጃችን ዶክተር መረራ መፈታቱ ደሰ አሰኝቶናል። መታሰሩን እንደ ብስራት ሲያናፉ የነበሩ ጋዜጠኛ ተብዬ የመንግሰትና የፓረቲ ጥገኞች ደግሞ አንደ ቢንቢ ከበው ማዋከባቸው ሳይሆን ዶክተር መረራ የሰጣቸው መልስ አርክተኛል። “በዚህች አገር በሰላም አብረን እንኖር ዘንድ ሌሎችም መፈታት አለባቸው። ኳሱ ደግሞ ኢህአዴግ እጅ ነች።” ነው ያላቸው። ቆርጠው የሚቀጥሉት ነገር አላገኙም። ሌሎችም ተፈቺዎች በተመሳሳይ አሰደስተውኘሰል። ኢህአዴጎች ኳሱ በእጃቸው ቢሆንም በፈለጉ ጊዜ አተንፍሰው አልጫወትም፣ ሲፈልጉ ነፍትወ እንጫወት ግን ብዙ ርቀት አይወሰድም። ይህን ምክር ቢሰሙ ጥሩ ነው። እነዚህ በመንግስት ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች የሚሰሙት የፌስ ቡክ ላይ የሚሰድባቸውን፣ እልህ የሚጋቡትም ከእነዚሁ ጋር ነው። ለአገር ሰላም አሰፈላጊ የሆነውን ከቂም በቀል የፀዳውን መንገድ ለማየት አይፈልጉም። ዛሬም በሰሩተትና በሚሰሩት ሰህተት ጫካ ውስጥ ተደብቀው አለን አለን እያሉ ነው። አሁንም ደግመን ደጋግመን የምንለው፣ ከጀብደኝነት ወጥት የእኛ መንገድ ብቻ ከሚሉት በሸታ ተላቀው፣ የጋራ አገራችንን ለመታደግ በጋራ እንድንቆም የፐለቲካ ምዕዳሩን ነፃ ያድርገት። እሰረኞችን ለመፍታት የአጭር ጊዜ እቀድ ብለው ያሰቀመጠት ሁለት ወር ሞት ጠሪ ነው። ሁለት ቀን በቂ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር አሁን የፍትሃብሔርና የሰነሰርዓርት ህጎች ማሻሻል አይደለም። የነፃነት ጥያቄ ላይ ነው። በቀለነ ገርባን አሰሮ መረራን በመፍረታት የሚሰፋ የፖለቲካ ምዕዳር የለም። አንዱዓለምን፣ እሰክንድርን፣ ናትናኤልን በግፍና በግል ቂም ጭምር አጉሮ ሰለ ፖለቲካ ምዕዳር መሰፋት ማውራት የቀልዶች ሁሉ ቀልድ ይሆናል። የአገራችን ሰላም ያገባናል፣ የሰለም መሰረት በጋራ እንጣል ማለት ያስከብራል። ሸክሙ ከአቅማችሁ በላይ ነው። ሁላችንም ያገባናል፣ አገራዊ የሰላም ጥሪ ለሁሉም የአትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል ለሚል ይደረግ። ሰላም፣ ሰላም፣ ብሎ በሚዲያ በመዘመር አይመጣም። ተጨባጭ እርምጃ ያስፈልጋል። ታሳሪዎች ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ፣ የግፍ እሰር ሲባቃ ያኔ ማዕከላዊ ሙዚየም ይሆናል።
Filed in: Amharic