>

33 የፖለቲካ እስረኞች ከ15 እስከ 18 አመት ተፈረደባቸው

በጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በእነ ሚፍታህ ሸህ ሱሩር ክስ መዝገብ በግንቦት 7 የተከሰሱ 33 ግለሰቦች ላይ የፍርድ ውሳኔ ሰጥቷል። በክስ መዝገቡ 77ተከሳሾች ክስ የቀረበባቸው ሲሆን 33ቱ አምነው ሲከራከሩ ቆይተዋል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጥር 3/2010 ከሰዓት በኋላ በነበረው የችሎቱ የስራ ሰዓት በተከሳሾቹ ላይ ከ15 እስከ 18 አመት ቅጣት ወስኖባቸዋል። ቀሪዎቹ ተከሳሾች ክደው የተከራከሩ በመሆኑ የመከላከያ ምስክር ለማቅረብ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል።

Filed in: Amharic