የእንቁዎቻችን ጥሪ፡ “LAMMII KOF NAN FIIGA” “ለወገኔ እሮጣለሁ” ትገኛላችሁ?
ለመሆኑ እነዚህ ኢትዮጲዉያን እንቁዎች እነማን ናቸዉ? በግል የተወዳደሩትን ትቼ ኢትዮጲያ በኦሎምፒክ መሳተፍ ከጀመረችበት አንስቶ ያለውን ብናይ የሚከተሉትን እናገኛለን።
Gold | Silver | Bronze | |
Rio, 2016 | Almaz Ayana (10000M) | Feyisa Lelisa (Marathon) | Mare Dibaba (Marathon) |
1G, 2S , 5B | Genzebe Dibaba (1500M) | Tirunesh Dibaba (10000M) | |
Tamirat Tola (10000M) | |||
Almaz Ayana (5000M) | |||
Hagos G/Hiwot(5000M) | |||
London, 2012 | Tiki Gelana (Marathon) | Dejene G/Meskel (5000 M) | Tariku Bekele (Marathon) |
3G, 2S, 2B | Tirunesh Dibaba (10000M) | Sofia Assefa (3000, Steeplchase) | Tirunesh Dibaba (5000M) |
Meseret Defar (5000M) | |||
Beijing, 2008 | Tirunesh Dibaba (10000M) | Sileshi Sihine (10000M) | Tsegaye Kebede (Marathon) |
4G, 1S, 2B | Kenenisa Bekele (10000M) | Meseret Defar (5000M) | |
Tirunesh Dibaba (5000M) | |||
Kenenisa Bekele (5000M) | |||
Athens, 2004 | Kenenisa Bekele (10000M) | Ejigayehu Dibaba (10000M) | Derartu Tulu (10000M) |
2G, 3S, 2B | Meseret Defar (5000M) | Sileshi Sihine (10000M) | Tirunesh Dibaba (5000M) |
Kenenisa Bekele (5000M) | |||
Sydney, 2000 | Gezahegn Abera (Marathon) | Gete Wami (10000M) | Tesfaye Tola (Marathon) |
4G, 1S, 3B | Derartu Tulu (10000M) | Assefa Mezgebu (10000M) | |
Haile G/Selassie (10000M) | Gete Wami (5000M) | ||
Million Wolde (5000M) | |||
Atlanta, 1996 | Fatuma Roba (Marathon) | Gete Wami (10000M) | |
2G, 1B | Haile G/Selassie (10000M) | ||
Barcelona, 1992 | Derartu Tulu (10000M) | Addis Abebe (10000M) | |
1G, 2B | Fita Bayisa (5000M) | ||
Moscow, 1980 | Mirus Yifter (10000M) | Mohammed Kedir (10000M) | |
2G, 2B | Mirus Yifter (5000M) | Eshetu Tura (3000 steeplechase) | |
Munich, 1972 | Mamo Wolde (Marathon) | ||
2B | Mirus Yifter (10000M) | ||
Mexico, 1968 | Mamo Wolde (Marathon) | Mamo Wolde (10000M) | |
1G, 1S | |||
Tokyo, 1964 | Abebe Bikila (Marathon) | ||
1G | |||
Rome, 1960 | Abebe Bikila (Marathon) | ||
1G |
Source: https://www.olympic.org/
እንቁዎቻችን የአገራቸው ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ እኛም ኮራ እንድንል በዓለም ዙሪያ የምንታወቅበት መጠሪያ፡ የረዥም ርቀት ሩጫ ባለቤቶች (ከረሐብና ጦርነት ውጪ) አድለውናል። ከግል ችሎታቸው ባሻገር የቡድን የአጋርነታቸው(All for one and One for all) ዓለምን ያስደመመ ነው። በ1980 ሞስኮ ኦሎምፒክ አጋርነታቸውና የቡድን ስሜታቸው ለድል እንዴት እንዳበቃቸው የዓለም ጋዜጣዎች በሰፊው ዘግበውታል። ይህ ሊንክ ሶስቱ እንቁዎቻችን፡ምሩፅ ይፍጠር መሐመድ ከድርና ቶለሣ ቆቱ የተፎካካሪያቸውን መንፈስና ጉልበት በግል ጥረትና በጋራ እንዴት አሸንፈው ለድል እንደበቁ ያሳያል። https://www.youtube.com/watch?v=C6eHUXDCKmQ
በ2004 የአቴንስ ኦሎምፒክ የቀነኒሳ ሐይሌና ስለሺ አጋርነት ቢያስደምመው እውቁ የሙዚቃ ሰው ቴዲ አፍሮ ቀነኒሳ አዲስ አበባ ሳይገባ አንበሳ፡ቀነኒሳ–ታሪክ ተሰራ የሚለውን ዜማ አበረከተለት። ይህንን ሊንክ ይመልከቱ https://www.youtube.com/watch?v=Ios9C1V3RCM
የኢትዮጲዉያን እንቁ የሆኑት አትሌቶቻችን በታሕሳስ 22 ከሶማሊያ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ማቛቛሚያ የሚውል የሩጫ ዝግጅት እኛው ለኛ በሚል መርህ አዘጋጅተው ለወገን ደራሽ ወገን ነው ብለው አድመውናል። በኦሎምፒክ ሜዳ ይሳዩንን አብሮነትና አጋርነት የመጀመሪያውን ሩጫ በአዲስ አበባ በማድረግ ገቢው ብቻ ሳይሆን አብሮነታችንና አጋርነታችን ለወገን ደራሽነታችን ይጠነክር ዘንድ እድል ሰጥተውናል። እንደታዋቂነታቸው ቢሆን London or New York or Washington DC ቢያደርጉ የሚሳተፉት እነማን እንደሆኑ መገመት ይቻላል። የሚገኘውም ገቢ እጥፍ ድርብ ይሆናል። ታዋቂነታችውንና የተቀረው ዓለም ስለእንቁዎቻችን የሚለውን ለማየት ይቺን ሊንክ ይመልከቱ። http://www.vogue.com/article/dibaba-family-ethiopian-distance-runners-olympics-2016-rio-de-janeiro
በአገር ውስጥ ያለን በሩጫው በመሳተፍ፣ መሮጥ የማንችል ለሚሮጡትና ራቅ ካለ ቦታ ለሚመጡት የመጓጓዧ አገልግሎት በመስጠት፣ ከአገር ውጭ ያለነው ሯጮችን ስፖንሰር በማድረግ አጋርነታችንን እናሳይ። እኛው ለኛ፡ለወገን ደራሽ ወገን ነው።
“LAMMII KOF NAN FIIGA” “ለወገኔ እሮጣለሁ” ትገኛላችሁ?