>
5:13 pm - Wednesday April 20, 5504

የኢህአዴግ ፓርላማ በይፋ ተከፋፈለ!

ሃብታሙ አያሌው እና ያሬድ ጥበቡ

የኦህዴድና የብአዴን ፓርላማ ተቀማጮች ሃይለማሪያምን ሃገሪቱ የገባችበትን ትርምስ በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጥ አዘዙት!

የኦህዴድና ብአዴን የፓርላማ ተቀማጮች ከድርጅቶቻቸው ጋር ስብሰባ ተቀምጠው አቋም ይዘዋል። የለማና የነገዱ ቡድን የፓርቲወቻቸውን ሙሉ ድጋፍ እንዳገኙ ይህ ይፋ አድርጎታል።

ለጥያቄያቸው መልስ ሳያገኙ መደበኛ ስብሰባ አናደርግም ብለዋል! የፓርቲወቻቸው ትእዛዝ ወርዶላቸዋል።

ህወሃት እና ገሚሱ ደህዴን በአንድ በኩል ብአዴንና ኦህዴድ በሌላ በኩል የሞት ሽረት እሽቅድምድም ገብተዋል። ብአዴንና ኦህዴድ የፓርላማ አብላጫ መቀመጫ ስላላቸው ወያኔ ትልቅ ስጋት ውስጥ ገብቷል።

ይህ ክንውን የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ፍጥጫ የተሞላበት ስብሰባ ጎን ለጎን እያደረገ በሚገኝበት ወቅት በመሆኑ ትርምሱን አባብሶታል!

የሪፖርተር ጋዜጣ ይህን ትርምስ ይፋ አድርጎታል። በኢህአዴግ ዘመን እንዲህ ያለ ክስተት ታይቶ አይታወቅም። አዲስ አበባ የለውጥ ማእበል እየናጣት ነው።

——

የኦህዴድና ብአዴን የፓርላማ ተወካዮች የሥራ ማቆም አድማ መምታታቸው የሚመሰገን ነው ። በዚህ ባገኙት የተግባር አንድነት ላይ ተመሥርተው በአፋጣኝ ወደሥራቸው በመመለስ ሌሎች ሃገራዊና አንገብጋቢ እርምጃዎችን ማድረግ ይችላሉ ፣ ይጠበቅባቸዋልም ። ለምሳሌ የሃገር ደህንነት ሃላፊው ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አመራር አባልነት ነፃ የሆነና ሁሉን የፖለቲካ ተዋናዮች በእኩልነት የሚያይ እንዲሆን መወሰን ይችላሉ ። ሌላው ፓርላማው ሊያደርግ የሚችለው ነገር፣ ያለ ፓርላማው ውሳኔ የመከላከያውና አጋዚ ሃይሉ የህዝብ ተቃውሞን ለማረጋጋት በሚል በክልሎች የሚያደርገውን ስምሪት መከልከል ይችላል ። በሶስተኛ ደረጃ፣ የመከላከያ ሠራዊቱ ከፍተኛ መኮንኖች የሃገሪቱን የብሄረሰብ ተዋፅኦ የተከተለና ከፖለቲካ አባልነትና ቲፎዞነት የፀዳ እንዲሆን መወሰን ይችላል ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖለቲካ እስረኞችን እንዲፈታ መመሪያ መስጠት ይችላል ። ስለሆነም፣ ባለፉት ሁለት ሳምንታት የፓርላማ አባላት የሥራ ማቆም አድማ እርምጃ ህዝባዊና የሚደገፍ ሆኖ ሳለ፣ በሥራ ማቆም አድማው መቀጠል ግን የሚጠቅመው የወያኔ አምባገነንነት በመሆኑ በአፋጣኝ ወደሥራቸው ተመልሰው ህዝቡ የሚጠብቃቸውን ወቅታዊ አጀንዳዎች መወሰን መጀመር አለባቸው።

Filed in: Amharic