ኦህዴድና ብአዴን በህወሀት ላይ በፈጠሩት ተፅእኖ ፓርቲው ከገባበት አጣብቂኝ አልተላቀቀም ። ዋናው ስቃዩ የሚጀምረው ደግሞ ከዚ በኋላ ነው ። የቀድሞዎቹ መለስና ፀጋዬ ብልጠት ከተንኮል ጋር አጣምረው ማእከላዊነቱን ጠብቀው የያዙት ህወሀት አባይ ወልዱ ጋር ሲደርስ በሙስና በጠገቡና እርስ በርስ በሚራገጡ ወያኔዎች ህወሀትን ሰንገው ሲይዟት ሀገራችንን ቀውስ ውስጥ እንድትከርም ተገዳለች ።
አንድ ቀን የረጋ ናፍጣ በሙቀት ፈሳሽ ነዳጅ አድርጎ ስላሳየን ሳይንቲስታችን ነው ። እያሉ ወያኔያውያን የሚመፃደቁበት በንግግር ችሎታውና ግብረገብነቱም በደካማነት የሚጠቀሰው የአሁኑ የህወሀት አለቃ ደብረፂዮን ህወሀትን ከድጡ ወደ ማጡ እንደሚከታት ይታመናል ። ከስድብና ማሸማቀቅ መለስ ይህ ነው የሚባል የረባ ሀሳብ የሌለው ደብሬ ተናቅን የበላይነታችንን ልናጣ ነው የሚል ምጥ ውስጥ ላሉት የታያቸው ብቸኛ ሠዋቸው ነው ። ነገር ግን በቦርድ አባልነት የሚመራው ኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኞችን በተለያዪ ወቅታዊ ጉዳዮች በፕላዝማ ቲቪ ለማወያየት በጠራቸው ስብሰባዎች ሁሉ ውይይቱ የሚበተነው በደብሬ ማስፈራሪያ እና ያዙኝ ልቀቁኝ ነው ። የተለየ ሀሳብ እንደስድብ ይነዝረዋል ይላሉ ቴሌዎች ። ታዲያ ለዚህ ነው ቀውሱ /እብዱ./ የሚል የቴሌ ሠራተኞችን መጠሪያ ያተረፈው ።
ህወሀት ይበድም ይቀውስም ደብሬ እንዲያከርማት ትፈልጋለች ። ከጌታቸው አሰፋ ጋር ያለውን የከረመ ፍቅር ተጠቅሞ ብአዴን እና ኦህዴድ የፈጠሩትን ግንባር ከተቻለ ንዶ ማፍረስ ካልሆነ እራሱ ኢህአዴግን ማፍረስ ግድ ሆኗል ።
የመጀመሪያዎቹ ሙከራዎች አሁን የተጀመሩ ይመስላል ። በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባላይ ህወሀት ዛቻ፣ ፍረጃ፣ ማስፈራራትን የመሳሰሉ አርጩሜ በሁለቱ ፓርቲ አመራሮች ጀርባ ላይ ብታሳርፍም ጠብ ያለ ነገር አልተገኘም ። ትንቅንቁ አይሎባታል ። ወደ ግድያ እና አፈና ደብሬ ያደረገው ጉዞ በለማ ጠባቂ ፖሊሶች እክል ገጥሞታል ። አሁን ዙሩ እየከረረ ነው ። ሁሉንም ከሸገር ሳይወጡ ለማፈን ህወሀት ልቧ ተመኝቷል ። ነገር ግን ከጀርባ ሚልዮኖች እፍርቷን ለማየት እስከመጨረሻው ሊቀብሯት አሉ ።
ግን የህዝብ ብሶት የወለደው የተባለለት ኢህአዴግ ባለፉት 27 አመታት እዚች ሀገር ላይ ስንት ብሶት ስንት ምሬት አስወለደን ? ህወሀት ዘራፊ መሪዎችዋን ከህግና ከህዝብ ተጠያቂነት ለማዳን በቅርቡ ሌላ እልቂት ፈፅማ ህጋዊ ትለናለች። ግን ለውጡ አይቀሬ ነው ። ዝርፊያ ንጥቂያ ግድያና ሀገራዊ ውንብድና ላይ የተሰማራው የደብሬ ህወሀት የማታ ማታ ራሱን የሚያይበት የታሪክ መስታወት የህዝብ ጩኸት እና ሽሽት ብቻ ነው ።