>
5:13 pm - Thursday April 19, 4187

“የአርቲስት ቴዲ አፍሮ “ኢትዮጵያ” የተሰኘው አልበም ከዓለማችን ምርጥ 100 ውስጥ አንዱ ነው” (በወንድወሰን ተክሉ)

የዳላሱ የሙዚቃ ባለማል ቴድ ጂዮያ 
 ኢትዮጵያ አልበም የ2017 የዓለም ምርጥ ሙዚቃ ውስጥ አንዱ ነው

በወንድወሰን ተክሉ
17-12-2017


የእውቁ ኢትዮጵያዊው አርቲስት ቴውድሮስ ካሳሁን [ቴዲ አፍሮ]የዘንድሮ “ኢትዮጵያ” የተሰኘው አልበም በ2017 ላይ በዓለም ከወጡት በርካታ አልበሞች ውስጥ ምርጥ 100 አልበሞች ውስጥ አንዱ ነው ተባለ።

ጃዝ ዶት ኮም [jazz.com ]እንደዘገበው በዓለማችን በ2017 ከወጡት 1034 አልበሞች ውስጥ ምርጥ 100ዎቹን አልበሞች ለመምረጥ በተደረገው ምርጫ የአርቲስት ቴዲ አፍሮ “ኢትዮጵያ” አልበም አንዱ ሆኖ መመረጡን ገልጻል።

የዓመቱን ምርጥ 100አልበሞችን በመምረጥ የሚታወቀው የዳላሱ የሙዚቃ ባለማል ቴድ ጂዮያ ባለፈው ሚያዚያ ውስጥ የተለቀቀውን እና በወቅቱ በዓለም የሙዚቃ ሽያጭ ቻርት [Billboard ]ላይ ለሳምንታት ያህል በአንደኝነት ደረጃ ላይ የሰፈረውን የቴዲ አፍሮን “ኢትዮጵያ” አልበም በዘንድሮው የዓመቱ ምርጥ አልበም ውስጥ መምረጥ እንደቻለ ማወቅ ተችላል።

ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነትን ያገኘው የአርቲስት ቴዲ አፍሮ የጥበብ ስራ በትውልድ ሀገሩ እስከዛሬ ድረስ በይፋ ለህዝብ በመድረክ እንዳይቀርብ በመንግስት ቢታገድም በዓለም የሙዚቃና የጥበብ መድረክ ላይ ተቀባይነትን እና እውቅናን ግን ከማግኘት እንዳላገደው መረዳት ይቻላል።

የቴዲ አፍሮ አልበም የአለማችን ሙዚቃ ቤተ መፃህፍት፣ የአለማችን ታላቁ የሙዚቃ ታሪክ አርታኢ እና በሙዚቃው አለም ታላቁ ተፅዕኖ ፈጣሪ በሚባለውና ባለ ዘርፈ ብዙው ሙያተኛው [የፍልስፍና፣ የምጣኔ ሃብትና ፓለቲካዊ ሳይንስ ምሩቁ) በቴድ ጂዮያ መራጭነት 100 የአለማችን ምርጥ አልበሞች ተርታ መሰለፉ ከአገራችንም አልፎ ለአህጉራችን አፍሪካ ታላቅ ስኬት ነው።

Filed in: Amharic