>

መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ እድሜልክ እስራት ተፈረዳባቸው

ዘሄግ (14 dec. 17) ዛሬ ዲሴምበር 15 ቀን 2017 ከቀትር በኋላ በሆላንድ ዘሄግ ከተማ የዋለው ችሎት በመቶ አለቃ በእሸቱ አለሙ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው የጦር ወንጀል ክስ  እድሜልክ እስራት በይኖባቸዋል። በተጠቀሳባቸው ክስ በሙሉ ጥፋተኛ ተብለዋል። ከሁለተኛው አለም ጦርነት በህዋላ እንዲህ አይነት ፍርድ በሆላንድ ሃገር ሲሰጥ የመጀመርያው መሆኑን አቃቤ ህግ ተናግረዋል። በሃገሪቱ ህግ የእድሜ ልክ እስራት አመክሮ የለውም።

አቶ እሸቱ አለሙ በውሳኔው ሰዓት ችሎቱ ላይ መገኘት አልፈለጉም።

              በአራት ዳኞች በተሰየመው በዚህ International Crime Chamber የተሰኘ  ችሎት የመሃል ዳኛዋ ማርየት ሬከንስ የፍርድ ውሳኔውን ባሰሙበት ወቅት አቃቢያን ህጎቹ እና የተበዳይ ጠበቆች በውሳኔው የደስታ ስሜት ታይቶባቸዋል።

              29 ኦክቶበር 2017 ጀምሮ ሲታይ የነበረው ይህ የፍርድ ሂደት የከሳሽ አቃቤ ህግንና የተከሳሽ ጠበቆችን ክርክክር ለወር ያህል ሲያዳምጥ ቆይቶ  ውሳኔ ለመስጠት ሳምንት በኋ  ቀጠሮ  ይዞ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ከሁለት አመት በላይ የፈጀው ይህ በአይነቱ ለየት የሚለው፣ የአቶ እሸቱ አለሙ የምርመራ እና የክስ ሂደት አለም አቀፍ ትኩረትን ስቦ ነበር። ፍርዱ በተሰጠበት በዛሬው እለትም በርካታ የሃገርውስጥ እና የውጭ ሃገራት ጋዜጠኞች ወደ ችሎቱ ታድመዋል።

63 ዓመቱ እሸቱ አለሙ  120 የደርግ አባላት አንዱ ሲሆኑ፣  1970ዎቹ ቀይ ሽብር ዘመን ደርግን ወክለው የጎጃም ክፍለ ሃገር አስተዳዳሪ  እንደነበሩ በችሎቱ ፊት ቢመሰክሩምየተመሰረተባቸውን የጦር ወንጀል ክስ ግን ሲቃወሙ ነበር።  

አስራ ሁለት ዓመት ፈጅቶ የነበረው የኢትዮጵያው የቀይ ሽብር ወንጀል ችሎት .. 2006 አቶ እሸቱ አለሙ ላይ በሌሉበት የሞት ፍርድ መወሰኑ አይዘነጋም።

1991 ኢህአዴግ ሃገሪቱን ሲቆጣጠር አቶ እሸቱ አለሙ ከነበሩበት ከቡልጋርያ ወደ ሆላንድ በመምጣት የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ  1992 የሆላንድ መኖርያ ወረቀት ያገኙ ሲሆን አመት በኋላም የሃገሪቱ ዜጋ ሆነዋል። ግለሰቡ   2015 ክመኖርያ ቤታቸው ባላሰቡበት መንገድ ተይዘው ታሰሩ።  ኦክቶበር 29, 2017 – በታሰሩ  2 ዓመት በኋላ – ጉዳዩ በሄግ ችሎት መታየትጀመረ።

በሆላንድ አቃቤ ህግ የቀረበባቸው ክስ በነሃሴ ወር 1978  75 ወጣቶች ግድያ (በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ውስጥ ተገድለው በጅምላ የተቀበሩ)  በዘጠኝ ዜጎች ላይ የተደረገ ድብደባእና የማሰቃየት ወንጀል እና  321 ሰዎች ላይ በደረሰ ህገወጥ እስራት የሚል ነው።

ለክሶቹ 3000 ገጽ ያላነሰ የጽሁፍ ማስረጃዎች  ፎቶ እና ተንቀሳቃሽ ምስልሎች፣  ከኢትዮጵያ፣ ከአሜሪካ፣ ከካናዳ እና ከእንግሊዝ የተገኙ  30 በላይ የአይን ምስክሮች ( ከነዚህ ውስትስምንቱ ምስክሮች ከካናዳ እና ከአሜሪካ ተጉዘው በሄግ ችሎት በመገኘት  ምስክርነታቸውን የሰጡ ሲሆን፣  በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ሶስት ባለሙያዎች  (/ ጃን አቢንክ  / ካሳ እና ክፉሉ ታደሰበማስረጃነት ቀርበዋል።

የሆላንድ ፍትህ ሚንስትር በአቶ እሸቱ ላይ ክሱን ለመመስረት መነሻ የሆነው፤   ..1998 ‘ፍራይ ኔደርላንድ‘ (ነጻ ኔዜርላንድበሚል መጽሄት ስለ ተከሳሹ የወጣ ወንጀል ነክ ጽሁፍነው።  የሆላንድ አለም ዓቀፍ የወንጀል ምርመራ ቡድን ይህንን ጽሁፍ እንደተመለከተ 2009  ጀምሮ የአቶ እሸቱን ስልክ በመጥለፍ መከታተል እንደጀመረ አቃቤ ህግዋ ሚስ ኒኮል ፎገለንዛግተናግረዋል። 

ይህ ቡድን 2012  ወደ ኢትዮጵያ በመጓዝ የኢዮጵያን መንግስት መረጃ ቢጠይቅም ከመንግስት በኩል ትብብር እንደተነፈገውም አቃቤ ህግዋ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩአልተባበርም ለማለቱ የሰጠው ምክንያት ጉዳዩ በሃገር ውስጥ በቀይ ሽብር የወንጀል ችሎት ስላለቀ መቶ አለቃ እሸቱን አሳልፋችሁ ስጡን በሚል ሰበብ ነው።  በሆላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል የወንጀለኛልውውጥ ስምምነት ባለመኖሩ እና በኢትዮጵያ የሞት ፍርድ መሰጠቱ ተጠርጣሪውን የማስረከቡ ጥያቄ ውድቅ ሊሆን ችሏል። 

አቶ እሸቱ አለሙ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ በተደመጠበት ወቅት “የተሳሳተ ሰው ነው የያዛችሁት”  ብለው ነበር።ማስረጃዎች ሲቀርቡና የምስክሮች ቃል መሰማት ሲጀምር በወቅቱ አስከፊነገር እንደተፈጸመ ተናግረው  ለተፈጠረው ነገር ሁሉ  ይቅርታ ጠይቀዋል። ይሁን እንጂ  እሳቸው በወቅቱ  በፕሮፓጋንዳ ስራ እንደተሰማሩና አንድም  ሰው እንዳልገደሉ፣ ሰው እንዲገደልም ሆነእንዲታሰር ትዕዛዝ እንዳልሰጡም ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ  የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዳደርግ ፍርድ ቤቱ እድል ስለሰጠኝ አመሰግናለሁ።  120 የደርግ አባላት  ውስጥ አንዱ ሆኜ ስለተሰራው ወንጀል አዝናለሁ። ግንየቀረቡብኝ ክሶች በሙሉ አልቀበልም።” ብለዋል።

ሺህ አመት  ታሪክ ያላት ሃገራችን እንዳትፈራርስ አሜሪካንን እርዳታ ብንጠይቅ እንቢ ስላሉን ነው ወደ ሶቭየት ለመሄድ የተገደድነው።  በወቅቱ የተደራጀው ሃይል ደርግ ብቻ ነው።ኢህአፓ ሃገሪቱን ሊያፈርስ በእብደት የተነሳ ሃይል ነበር። አቶ ክፍሉ ታደሰ የኢህአፓ አመራር የነበሩ በመሆናቸው ሃሳባቸው ነጻና ገለልተኛ ሊሆን አይችልም።” ሲሉም ኢህአፓን በፍርድ ቤት ውሎኮንነዋል።

/ ሳንደር አርት፤ የአቶ እሸቱ ጠበቃ የስም መደባለቅን  እንደ  ለመከራከርያ አቅርበው ነበር። ወንጀሉን የፈጸሙት ተከሳሹ እሸቱ አለሙ ሳይሆኑ ሌላ እሸቱ ናቸው ሲሉ ተከራክረዋል።

የግድያውን ትዕዛዝ የያዙ ፊርማዎች የሱ ሳይሆኑ የሌላ እሸቱ ናቸው።   ምስክሮቹም የተናገሩት የሚያሳምን አይደለም። የፍርዱ ሂደት ፍትሃዊ አይደለም። አቶ እሸቱ አለሙ 2015 ከቤታቸው ተወስደው ሲታሰሩ ወንጀለኝነታቸው አስቀድሞ እንደተረጋገጠ ይተቁማል።” የሚል ነበር የመከራከርያቸው ጭብጥ።

ሌላው የጠበውቃው መከራከርያ ነጥብ ደግሞ 1978 ጎጃም ውስጥ የርስበርስ ውግያ ባለመካሄዱ ጉዳዩ የጦር ወንጀል ሊሆን አይችልም። ተራ ወንጀል ደግሞ በዚህ ችሎት መታየትአይችልም።” የሚል ሲሆን፣  ቀደም ሲል አቶ እሸቱ አለሙ በጎጃም ኢህአፓ በተደራጀ መልክ ጦርነት ከፍቶ እንደነበር ለፍርድ ቤቱ የተናገሩት ቃል ይህንን መከራከርያ ነጥብ አፍርሶታል።

የተበዳዮች ጠበቃ የሆኑት ሚስ ባርባራ ፋን ስትራተን – ለእያንዳንዱ ተበዳይ 200 ካሳ ኤሮ እንዲከፈል ፍርድ ቤቱን  ጠይቀዋል። ይህ ካሳ  ምንም እንኳን መጠኑ ዝቅተኛ ቢሆንም ጥፋቱንለማስረገጥ የተደረግ ተምሳሌታዊ (ሲምቦሊክነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ሁለት የሩዋንዳ እና  አንድ የኢራቅ ተወላጆች ላይ ተመሳሳይ ክስ ተመስርቶ እንዳንዳቸው በ 16 17 አመት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል። 

በሆላንድ የእድሜ ልክ እስራት የሚበየነው  እጅግ አስከፊ ለሆነ ወንጀል ስለሆነ  የተመክሮ መብትም የለውም።  በሃገሪቱ እድሜልክ የተፈረደባቸው ሰዎች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው።

አቶ እሸቱ አለሙ ባለትዳር እና የሁለት ልጆች የነበሩ ሲሆን ባለቤታቸው እና ልጆቻቸው በውል በማይታወቅ ምክንያት ከአመታት በፊት ጥለዋቸው ወደ አሜሪካ በመሄድ ኑሯቸውን እዚያአድርገዋል። 2015 ከመታሰራቸው በፊት ሆላንዳዊት የትዳር ጓደኛቸው ጋር ይኖሩ ነበር።

የአቶ እሸቱ መያዝ እና መታሰር የዚህን ትውልድ  ትኩረት ባይስብም አሁን በሃገሪቱ እየተፈጸመ ላለው ተመሳሳይ ወንጀል አይን ከፋች ነው።በሰብአዊነት ላይ ወንጀል ሰርቶ ከሃገር መውጣትእና መደበቅ እንደማይቻል ትምህርት ይሆናል።  የሆላንድ ፍትህ ሚኒስቴር ያሉትም ይህንኑ ነው። “ሃገራችን ዜጋቸውን ጨፍጭፈው ለሚመጡ ወንጀለኞች የመደበቅያ ገነት መሆን የለባትም!”

እሸቱን ያየህ ተቀጣ!

EMF

Filed in: Amharic