>
5:13 pm - Tuesday April 20, 6923

የወያኔ የእርቅ ጥያቄና የሻቢያ አስቂኝ ምላሽ፥ (ኰከብ ተድላ)

በአንድ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ ከመሞቱ በፊት፡ በምክር ቤት ቀርቦ፥ ከአንድ የምክር ቤት አባል፥በኢዮጵያና በኤርትራ መሀከል በወቅቱ የነበረውንና ለወደፊት ሊሰራ የታሰበውን ተጠይቆ፥የሰጠው ምላሽ እንዲህ የሚል ነበር:-
“እንታረቅ ብለን የሻቢያን በር 70 ጊዜ አንኳኩተናል ይሁን እንጅ ከኤርትራ በኩል ፈቃደኝነት የለም፥ለወደፊትም ሌላ 70 ጊዜ የኤርትራን በር እናኳኳአልን”ሲል ነበር የመለሰ።  ከዚያ ወዲህ ወያኔ የሻቢያን በር ስንቴ እንዳአንኳኩ ባይነግሩንም የሰሞኑ የወያኔ የእርቅ ጥያቄና፡አቶ የኢሳያስ አፈወርቄ የሰጡት መልስ ግን በጣም በጣም ያስቃል።
ሁላችንም እንደምናስታውሰው፡ ድሮ የወያኔ የእርቅ ጥያቄ “በቅድሚያ ተገናኝተን እንነጋገር” የሚል ቅድመ ሁኔታ ነበረበት። በሻቢያ በኩል ደግሞ ሲሰጥ የቆየው መልስ “መጀመሪያ ከባድሜና አካባቢው ጥርግ ብላችሁ ለቃችሁ ውጡና፡ ከዚያ በኋላ አስፈላጊ ከሆነ፥ መነጋገር እንችላለን”የሚል ነበር። ይህ የሁለቱ ፓርቲወች ግትር አቋም ላለመታረቅ እንደ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል።ሻቢያ የጊዜ ጉዳይ እንጅ የተፈረደለትን መሬት በሆነ ቀን ሊያገኘው እንደሚችል እርግጠኛ ነበር።ለወያኔ ደግሞ የስልጣን ጉዳይ ነው።ሁሉም ነገር ከወያኔ ስልጣን ጋር የተያያዘ ነው።ባድሜ፡ የህዳሴው ግድብ፡ኦርቶዶክስ፡ እስልምና፡ኢሪቻ—ወዘተ።
አሁን ግን ወያኔ ስልጣኑ ከእጁ እያመለጠው መሆኑን ሲያውቅ፡ ከሻቢያ ጋር ለመታረቅ፡ ጥያቄውን ማሻሻል ብቻ ሳይሆን የሻቢያን ጫማ ስሞ፡ ያለምንም ቅድመሁኔታ ቢቀርብም፥ ከሻቢያ በኩል የተሰጠው መልስ ግን፡ በበኩኩሌ ለአንድ መንግስት ነኝ ለሚል ቀርቶ፣አንድ ንፍጡን ለሚልስ ህጻን እያለቃቀሰ ሲያስቸግረን ዝም ለማስባል ልንሸውደው ብንሞክር እንኳ ህጻኑ ነቄ ከሆነ አይመጥነውም። የሻቢያ ምላሽ እንዲህ የሚል ነው፥ “ከአዲስ አበባና ከመላው የኢትዮጵያ ክልል ተባራችሁ፡ወደ ትግራይ ስትመለሱ ያኔ እንነጋገራለን፡አትቸኩሉ የቆያችሁትን ያህል አትቆዩም” የሚል አስደንጋጭና የወያኔን ወሽመጥ ሚቆርጥ መርዶ ነበር።
“አዳም አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ”(ወያኔ የሻቢያ ባሪያ ነበህና ተመልሰህ የሻቢያ ባሪያ ትሆናለህ) ብሎ የረገማቸው ማን ነው?
Filed in: Amharic