>

በአውሬ መሃል ያለመከላከያ «እምብዛም ዝምታ ለበግም አልበጃት፣አስራ ሁለት ሆና አንድ ነብር ፈጃት» 

ኣቻምየለህ ታምሩ

ያለ አንዳች መከላከያ በጫካ ውስጥ በአውሬ መሃል የሚኖር ሰው አደጋ ቢደርስበት የሚታዘንበት እንጂ የሚታዘንለት ሊሆን አይችልም። አማራን ለማጥቃት በሰለጠኑ የተከዘ ማዶ ጨካኝ አውሬዎች መካከል እየተኖረ ለምን ተገደልን ማለት በሲኦል ውስጥ እየኖሩ በምህረት ወደ መንግሥተ ሰማያት ለምን አንገባም እያሉ የመቃናጣት ያህል ነው።

እንስሳት እንኳ ቀድመውን የአውሬ መለካከያ አበጅተው ራሳቸውን ከጥቃት እየተከላከሉ፤ እኛ ሰዎች እኛን ለማጥቃት በሰለጠኑ አውሬዎች ስንታደን እየዋልን የአውሬ መከላከያ አሽክላ እንኳ አለማበጀታችን ጥፋቱ የኛ በአውሬ መካከል ያለመከላከያ እየተበላን የምንኖረው እንጂ የሚያሳድዱን አውሬዎች ሊሆን አይችልም።

ትልቁ ጥፋተኛ እኛን ለማጥቃት በሰለጠኑ ተኩላዎች መካከል እየኖርን ዛሬም ድረስ ዝቅተኛ ህልያት [እንስሳትና እፀዋት] ራሳቸውን ለማስተዳደር ካስቀመጧቸው ህግጋት እንኳ መማር ሳንችል፤ እኛን ሊያጠፉ የተፈጠሩ አውሬዎችን ቀንበርን ለመሸከም ዝግጁ ሆነን፤ ተበልተን ሳናልቅ የአውሬ መከላከያ መሳሪያ ሳናበጅ፡ የአውሬ መጫዎቻ የሆነው እኛ ነን።

አያቶቻችን በጫካ ውስጥ ሲኖሩ ራሳቸውን ከአውሬ ጥቃት ለመከላከል ተናካሽ ውሻ ከማሳደግ ጀምሮ እሳትና ልዩ ልዩ መከላከያዎችን በመጠቀም ራሳቸውን ከአውሬ ሲከላከሉ ኖረዋል። ዛሬ ግን ጫካው ተመንጥሮ አልቆ ከአውሬ የከፉ አማራን ለማጥቃት የሰለጠኑ የተከዘ ማዶ ጨካኝ አውሬዎች እየዘለዘሉ ሲበሉን እያየን ተበልተን ለማለቅ እንጂ ራሳችንን ለመከላከል ዝግጁዎች አይደለንም።

የፋሽስት ወያኔ ድርጅት ነውረኛ ብአዴን እንደራሴ የሆነበት ወያኔ የፈጠረው አማራ ክልልም ሆነ የትግራይ ክልል ዛሬ ላይ ለአማራ ልጆች እጅግ አደገኛ ሆኗል። ባሁኑ ሰዓት ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ የአማራ ተማሪዎች እየተደበደቡ፤ ለትግራይ ልጆች ግን በፖሊስ ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው።

ትናንትና የአማራ እናት የአይኔ ማረፊያ ይሆናል፤ አድጎ ይጦረኛል፤ አገሩን ያገለግላል ብላ አገር ያላት መስሏት አዲግራት እንዲማር የሸኘችው የስለት ልጇ አማራን ለማጥቃት በሰለጠኑ የትግራይ ተወላጆች በግፍ ተጨፍጭፎ ተገድሏል። የአማራ ልጆች በየተገኙበት እንፈ ፋሲካ ዶሮ መታረድ ጥፋቱ አማራን ለማጥቃት የሰለጠኑት አውሬዎች አይደለም። ጥፋቱ እሱን ለማጥቃት በሰለጠኑት መካከል እየኖረ ያለው አማራ የአማራው መታረጃ ቄራ በሆነችው የወያኔዋ ኢትዮጵያ ለራሱ መከላከያ የሚሆን መሳሪያ ሳያበጅ መኖሩ ላይ ነው። በአውሬ መካከል እየኖሩ ከአውሬ ጥቃት ራስን መከላከል ያባት ነው። ባውሬ መሃል እየኖሩ ያለመከላከያ መቀመጥ « እምብዛም ዝምታ ለበግም አልበጃት፣ አስራ ሁለት ሆና አንድ ነብር ፈጃት» አይነት ተረት የተነገረላትን በግ መሆን ነው።

አማራን ለማጥቃት በሰለጠኑ የተከዘ ማዶ ዘረኞች በግፍ የወደቀውን እንቦቀቅላውን ሐብታሙ ያለውን እግዚአብሔር ከቅዱሳን ጋር ከሰማዕታት ተርታ የቆመው ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን!

Filed in: Amharic