>

ደብረፂዮን እንደ ሳኒ አባቻ - አብዲ ኢሌ እንደ አሊ ሶሊህ (ቬሮኒካ መላኩ)

ትናንትና ዛሬ የወጡት ዜናዎች አስገራሚና አስቂኝም ናቸው። ትናትና የወጣው አስገራሚ ዜና  ምንጩ  የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ይጠቀምበታል ተብሎ  የሚገመተውና  የአባይ ወልዱ ግሩፕን የሚደግፈው Zharina በሚል ስም የሚጠራው የፌስቡክ ገፅ ነው።
በዚህ ዜና መሰረት
“የህውሃት ሊቀመንበር የሆነው  ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል  ከ75 % በላይ ሰአቱን የሴክስ ፊልም ( Porno) ሲከሰክስ  እንደሚውልና  ሌላም  ሌላም ብዙ ስለሰውየው ጉድ  ፅፎ  አስነብቧል።
..
ዛሬ የወጣው ዜና ደሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት  አብዲ ኢሌ ጅጅጋን ስጋ በስጋ በሽ በሽ  አድርጎታል የሚል ነው ።
አብዲ ኢሌ ብዛት ያላቸው ግመሎችን በማሳረድ  የጎሳ መሪዎችና ሽማግሌዎች   ለማ መገርሳ  በአስቸኳይ እንድሞትለት  የመርገም እና የፀሎት ስነስርአት እንድፈፅሙ ባዘዘው መሰረት የእርግማን ስነስርአቱ እንደተከናወነ ታውቋል  :)።

የኒዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ የነበረው  ዴቪድ ላምብ  በ1970ዎቹ ስለነበሩት ስለአፍሪካ መሪዎች የፃፈው አስደናቂ እውነታ  ከአብዲ ኤሌና ከደብረፂዮን ጋር ተመሳሰለብኝ ።

የኮሞሮሱ ፕሬዚደንት አሊ ሶሊህ እንደ አብዲ ኢሌ ጠሽ ነበር ። ዴቪዲ ላምብ እንደፃፈው  የኮሞሮሱ ፕሬዚደንት  አሊ ሶሊህ ከእለታት በአንዱ ቀን በህልሙ  አንድ ሰውና አንድ ውሻ ሊገድለው  ሲያሳድደው ይታየዋል። በህልሙ ከውሻ ጋር ሲሯሯጥ ያደረው አሊ ሶሊህ በሚቀጥለው ቀን በመላው ኮሞሮስ  የሚተገበር አዋጅ አወጣ ። ይሄውም በኮሞሮስ የሚገኙ ውሾች ሁሉ አንድም ሳይቀር እንድገደሉ ያዛሉ ። በዚም መሰረት የአገሪቱ ጦር  ግዳጅ ተሰጥቶት በኮሞሮስ ያሉትን ውሾች ሁሉ በሳምንት ውስጥ ድምጥማጣቸውን አጥፍተው ኮሞሮስን ውሻ አልባ አገር አደረጓት ።

ሌላው ከደብረፂዮን ጋር የሚመሳሰለው የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዚደንት ሳኒ አባቻ  ነው። ሳኒ አባቻ Sexual perversion (ጤነኛ ያልሆነ የወሲብ ስሜት)  ተጠቂ ስለነበር ብዙውን ሰአቱን የወሲብ ፊልም ሲመለከት ነበር የሚውለው ። በመጨረሻ  ሳኒ አባቻ  ከህንድና ከስሪላንካ ካስመጡዋቸው ሴተኛ አዳሪዎች ጋር ቪያግራ ውጦ ሲዳራ ልቡ ቀጥ  ቆሞ ሞተ።፣ ዛሬም ድረስ  የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ሳኒ አባቻ የሚታወሰው ሬሳው አጠገብ በተገኘው ቪያግራና ባንክ  አካውንቱ ውስጥ በተገኘው  አምስት ቢሊዮን ዶላር  ነው።

Filed in: Amharic