>
5:14 pm - Tuesday April 20, 0466

ለአንድ መንደር ጉጅሌ መገዛት ነውር ነው (ደረጀ ገረፋ ቱሉ)

የወያኔ ዘረኝነትና አድልኦ ናላው ዞሮ ትናንት ከተመረጡት ዘጠኝ የፖሊተቢሮ አባላት ስድስቱ ከአድዋ፣ ሁለቱ ደግሞ ባለቤቶቻቸው ከአድዋ መሆናቸውን የትግርኛ ሶሻል ሚዲያ ይፋ እያደረገ ነው ። ዝርዝሩን ተመልከቱ ። ብቸኛው ከአድዋ ውጪ የተገኘው ጌታቸው ረዳ ሲሆን፣ እርሱም የኦሮሞ አማራን ህብረት ለማቆሸሽና ለመስበር ይረዳል ተብሎ የተጨመረ ፀጉረ ልውጥ መሆኑ ግልፅ ነው ።

አድዋን ብቻ የሚወክል ወያኔ እንዴት አድርጎ ነው የኢህአዴግ ሥራአስፈፃሚ ውስጥ መሳተፍ የሚችለው ። እነ አቶ ለማና ገዱ በሚቀጥለው ሳምንት የሚደረገው የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ፣ ወያኔ ትግራይን የሚወክል የአመራር ተዋፅኦ ይዞ እስኪመጣ ድረስ ከኢህአዴግ አመራር ስብሰባዎች የታገደ መሆኑን ማሳወቅ ይኖርባቸው ይመስለኛል ። ይህ በማንቀላፋት ላይ ያለውን የትግራይ ወጣት ሊያነቃቃውና የለውጥ እንቅስቃሴውን እንዲቀላቀል ሊያበረታታው ይችላል ። ወያኔም ተስተካክሎ እስኪመለስ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት፣ የመከላከያውንና የደህንነቱን ከፍተኛ መዋቅሮች ብሄራዊ ተዋፅኦ ማስተካከል፣ ደኢህዴን ውስጥ አስተማማኝ ድጋፍ መኮትኮት፣ የኢህአዴግ አመራር ድርጅቶቹ ከሚወክሉት ህዝብ ብዛት አንፃር ልክ በተወካዮች ምክርቤት ያላቸውን ድልድልና ስሌት ተከትሎ እንዲደለደል ማድረግ ወዘተ ወዘተ ይችላሉ ። ለአንድ መንደር ጉጅሌ መገዛት ነውር ነው ። 

እሄ ነገር እንዴት ነው? እኛ እኮ ትግራይ ልክ እንደ ሸዋ እና ጎጃም አንድ ክፍለሀገር ነበር የሚመስለን። እናንተም ጋር በክፍለ ሀገር መካፋፈል አለ እንዴ?

፩) ደብረፅዮን…………… ዓድዋ
፪) ፈትለወርቅ…………… ዓድዋ
፫) ጌታቸው ኣሰፋ…………ዓድዋ
፬) ኣባይ ነብሶ……………ዓድዋ
፭) ኣብራሃም ተከስተ……… ዓድዋ
፮) ኣዲስ ኣለም ባሌማ……. ዓድዋ
:
:
፯) ኣለም ገብረዋህድ…… ባለቤቶቻቸው ከአድዋ 
፰) ኬርያ መሓመድ ………  ባለቤቶቻቸው ከአድዋ 
፱) ጌታቸው ረዳ ……… ብቸኛው ከአድዋ ውጪ የተገኘው  ሲሆን፣ እርሱም የኦሮሞ አማራን ህብረት ለማቆሸሽና ለመስበር ይረዳል ተብሎ የተጨመረ

Filed in: Amharic