>

ቴዲ አፍሮ፤ በመላው አለም ''ኢትዮጵያ ኮንሰርት'' በቅርብ ቀን

Image may contain: 1 person, standing and text

 

አለም ኋላ ቀር ናት ያላት ኢትዮጵያ በቴዲ አፍሮ ለአለም ሁሉ መልዕክቷን በቅርቡ ትልካለች። /በጥበብ ስራው የአልበም ሽያጩ የአለምን ሪከርድ እንደ ሰበረ ሁሉ…/ በዲክሽነሪዎች ሳይቀር ኢትዮጵያ የሚለው ስም ሲብራራ ድሃ እና እርሀብተኞች የሚል መተንተኛ የተሰጣት ሀገር ዛሬ ታላቅነቷን በቴዲ አፍሮ ልታስመሰክር ነው። /አፄ ቴውድሮስ የሚሉት ታላቅ ንጉስ እንደነበራት፣ባሮ ወንዝ፣የአክሱም ሀውልት፣ጥንታዊው የፍፁምነት መግለጫ “ቶ” መስቀል፣ ሶሪት የተባለ ውብ አበባ ወዘተ… ያላት ሀገር መሆኗን ለማስመስከር/

#ኢትዮጵያ_ኮንሰርት በሚል አለምን ለማመስ የተነሳው ብላቴና ከሶስት ወራቶች በላይ ባደረገው የመድረክ ልምምድ ከቀድሞው በተሻለ የመድረክ ላይ ብቃት /Performance/ አድናቂዎቹን ለማስደሰት ዝግጅቱን ጨርሷል። እንደየ ሁልጊዜው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ከፍ ብሎ የሚታይበት #ኢትዮጵያ_ኮንሰርት ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስን እና የሱን ራዕይ ይዞ የተነሳ መሆኑ ለዓለም በቂ ምላሽ ይሰጣል። አፄ ቴዎድሮስ ኢትዮጵያ የማንም ታናሽ ሀገር አይደለችም ብለው የሚያምኑ ንጉስ ናቸው። በመላው አለም ስፍር ቁጥር የሌለው ህዝብ ከቴዲ አፍሮ ጋር ኢትዮጵያ ብሎ በባዕድ ሀገር ስሟን ሲጠራ ማየት የሚያኮራ ነው።

እንደ ቴዲ አፍሮ ሀሳብ ቢሆን #ኢትዮጵያ_ኮንሰርት መጀመር ያለበት ከአዲስ አበባ እና የኢትዮጵያ ክልል በሆኑ በሌላ ሁለት ሀገሮች ላይ ነበር። ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ላይ ኮንሰርት አዘጋጃለሁ በሚል ተስፋ ብዙ ትላልቅ ኮንሰርቶችን የሰረዘ ሲሆን በብርም ደረጃ ጠቀም ያለ ገንዘብ ከማግኘት የተገታ መሆኑ የሚታወስ ነው። በአሁንም ቢሆን እስከ ቅርብ ጊዜ ባደረገው የፍቃድ ጥየቃ ጥረት አልሳካ በማለቱ ጉዞውን ከአሜሪካ ለመጀመር ተገዷል። ስለሆነም በቀጣዩ የነጮች ወር ዲሴምበር /December/ አሀዱ ብሎ #ኢትዮጵያ_ኮንሰርትን ይጀምራል።

በጥቁሉ በሚያደርገው #የኢትዮጵያ_ኮንሰርት ጉዞ ከአምስት እስከ ሰባት ወራቶች ሊፈጁበት እንደሚችሉ ይጠበቃል። እኛም ከወዲሁ መልካም ጉዞ #ኢትዮጵያዬ ብለናል። በተጨማሪም ልናሳስባቹ የምንወደው ነገር ቢኖር ስለ ኮንሰርቱ በቂ መረጃ ለማግኘት የቴዲ አፍሮን ኦፊሺያል ፔጅ እና በስሙ የተከፈቱ ቴዲ አፍሮ ፔጆችን ይከታተሉ። በወቅቱ የደረሱንን አጫጭር የመድረክ ቪዲዮዎችን በዚሁ ፔጅ የምናደርሳቹ ይሆናል።

Filed in: Amharic