>
5:13 pm - Tuesday April 18, 5082

«በዚምቧቤ ውስጥ ምንም ዓይነት የሚቀየር የመሬት ፖሊሲ የለም ...» ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ (አዞው)

በዮናስ ሃጎስ
«የዚምቧቤ አባት ሮበርት ጋብሬል ሙጋቤ ሀገሪቷን የመሰረተና ከጭቆና ነፃ ያወጣ ትልቅ መሪ ነው። ለኔ ሁሌም ቢሆን መሪዬና የሐገሪቷ ትልቅ ጀግና ነው። ቀሪ ዘመኑንም ለእንደርሱ ዓይነት ጀግና በሚገባው መልኩ እንዲያሳልፍ ሁላችንም የበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይኖርብናል።»
አዲሱ የዚምቧቤ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ (አዞው)
***
የሰውዬው ንግግር በእውነቱ የድሮ ስርዓት ናፋቂነቱን ያሳበቀ ነው። ምናልባት ይህንን ንግግሩን ስላልወደዱት ይሆናል የኛ መሪዎች በቦታው ያልተገኙት?
የበለጠ የሚገርመው ሰሞኑን በሙጋቤ መወገድ ደስታውን ሲገልፅ የነበረ ሕዝብ ይህንን የአዲሱን ፕሬዝዳንት ንግግር ሲሰማ በሆታና በሁካታ አደባባዩን ማድመቁ ነው። ሮበርት ጋብሬል ሙጋቤን ከዚምቧቤ ቤተ መንግስት ማስወገድ ይቻል ይሆናል። ከዚምቧቤያውያን ልብ ግን እንዲሁ በቀላሉ መፋቅ አይቻልም።
***
ባልተያያዘ ዜና እነ ቢቢሲ፣ ሲኤንኤን ዝግጅቱን በቀጥታ ስርጭት ማስተላለፋቸው አዲሱ ፕሬዝዳንት ዚምቧቤን ከምዕራቡ ዓለም ጋር ለማቀራረብ እንደሚሰሩ የተናገሩት ጋር ተደማምሮ ከነጮች ተነጥቆ ለጥቁሮች የተሰጠው መሬት ላይ ለውጥ ያመጣ ይሆን?
***
ይህንኑ እየፃፍኩኝ አዲሱ ፕሬዝዳንቱ ፅሁፌን ያዩ ይመስል በንግግራቸው ምላሽ ሰጡኝ።
***
«በዚምቧቤ ውስጥ ምንም ዓይነት የሚቀየር የመሬት ፖሊሲ የለም። በሮበርት ሙጋቤ የተፈፀመው የመሬት ፖሊሲ እንዳለ የሚቀጥል እና የዚህም ፖሊሲ ተጠቃሚዎች መሬታቸውን በአግባቡ በመጠቀም የዚምቧቤን ምርታማነት እንዲያስቀጥሉ ጥሪዬን አቀርባለሁኝ። በመሬት ፖሊሲው መሬታቸውን ያጡ ሰዎች ደግሞ በዚምቧቤ ሕግ መሰረት የመሬታቸው ካሳ እንዲያገኙ ይደረጋል…»
***
ምርጫን በተመለከተ በ2018 የታቀደው ምርጫ በታቀደለት ጊዜ እንደሚካሄድ አዲሱ ፕሬዝዳንት ቃል ገብተዋል።
Filed in: Amharic