>

የህውሃት የሰሞኑ ሽኩቻ በስርዓቱ ላይ ያለው እንድምታ፥ (ጥሩነህ ይርጋ)

በወያኔ ጓዳ ፍርሃት ነግሷል፥ በአባዱላ ጀምሮ፣ በረከትን ከሃዲዱ ድንገት ያስወጣው ንፋስ፥ ሸክ መሃመድ ሁሴን ዓላሙዲን አሽከርክሮ ደብልቆታል፥ የአገዛዙ ቁንጮዎችና ተባባሪዎቻቸው እያንዳንዱ ምርኩዛቸው ውልቅ እያለ መውደቅ ሽብር ለቆባቸዋል፥ ወያኔዎች የሚመኩበት የተውሶ ጭንቅላትና የዝርፊያ ሃብት ሁሉም ብን ብሎ መጥፋቱን እያሰቡ ጭንቀት ይዟቸዋል። የኦሮሞውና የአማራው አንለያይም ማለት፥ የኦህዴድና የብአዴን ካድሬዎች ጡንቻ ማውጣት እንቅልፍ ነስቷቸዋል።

እሄን ተከትሎ በኢትዮጵያ ሰማይ የደራ የለውጥ ጊዜ ይታያል፥
ግን አሁን ሳይዘገይ በተቀናጀ መንገድ፣ በትላልቅ ከተሞች፣ በዓንድ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍና፥ መሬት አንቀጥቅጥ የሆነ ህዝባዊ ነውጥ ማድረግ ያስፈልጋል፥ እሄ ጊዚያዊ ጉዳት ቢኖረውም ብዙ የስቃይና የመከራ ጉዞዎችን ይቀንሳል።

የወያኔ የበላይ ተቆጣጣሪዎችና ዋና አመራሮች መቀሌ ላይ ወሩን ሙሉ በር ዘግተው በስድብ ሲጠዛጠዙ የከረሙት ግም ለግም ተያይዞ ይገማልና በሃገር ጉዳይ ሳይሆን፥ ሰርቀው በሰበሰቡት ገንዘብና ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዘርፈው ባካበቱት ንብረት የተነሳ እየደረሰባቸው ያለውን የፖከቲካ ኪሳራና ሊያቃኑት ያልቻሉትን የጊዜ ጎባጣ እያነሱ፥ የተግማማውን ማንነታቸውን እየገለጡ አንች ነሽ፥ አንተ ነህ፥ በመባባል ግምገማ እንደነበረ ተሰምቷል።

ከዚህ በዘለለ አዜብ ስብሰባ እረግጣ ወጣች ለሎችም ተከትለዋት ወጡ በሚል ዜና መቀሌ በጭንቀት ተወጥራለች፥ እንደ ትልቅ ነገር ተወርቷል፥ ወያኔ ሊፈረካከስ ነው እያሉ ወሬውን ሲያናፍሱ ሰንብተዋል።
እንደተባለው ስርዓት አልባ ሌቦች ናቸውና ተቧድነው ሽጉጥ ሊማዘዙና ሊገዳደሉ ይችላሉ በዚህ ግን ለውጥ ይመጣል ብሎ ማሰብ ቂልነት ነው።

አዜብ መስፍን የተባለች አንዲት ጋለሞታ ጥቂት ውሽሞቿን አስከትላ ስብሰባ እረግጣ መውጣት አይደለም፥ ከእኔ በላይ ጀግና የሚለው ስዬ አብርሃ የተባለ ወደል ወያኔ ስብሰባውን እረግጦ ወጥቶ እንኳን እንደ ጠጅ ቤት ጣሳ ከኢህአዴግ ጓሮ ወድቆ ነው የቀረ፥
ዛሬም አዜብን ተከትለው ስብሰባ እየረገጡ የወጡ ባልቴት ወያኔዎች የእነ ስዬ አብርሃ እጣ ይደርሳቸዋል ወይም እንደለመዱት ጫማ ልሰው ይመለሳሉ፥ የእነሱ ዛቻ ጥርስ ማፋጨትና መዘላለፍ እንደ ሜዳው አህያ የእርስበርስ እርግጫ የሚቆጠር ነው።
በህወሃት ውስጥ ሽኩቻ እና መጠላለፍ አዲስ አይደለም፥ ሆኖም ግን እሄን የወያኔ ፍጥጫ ለተጠቀመበት የደራ የለውጥ ጊዜ ነው።

ልብ ያለው ልብ ይበል።

Filed in: Amharic