>
5:13 pm - Friday April 19, 4701

"የዚምባበዌ ዜጋ የሆነው ኮለኔል መንግስቱ ሀይለማሪያም " (ቬሮኒካ መላኩ)

የሰሞኑ የዝምባብዌ መንግስት መፈነቅለ መንግስት አርክቴክትና መሀንድስ መንግስቱ ሀይለማሪያም እንደሆነ በተለያዩ አለምአቀፍ ፕሪንት ሚዲያ እየተገለፀ ነው። “የዚምባበዌ ዜጋ የሆነው ኮለኔል መንግስቱ ሀይለማሪያም ” በማለት እየፃፉ ነው። ከሁሉም የገረመኝ ጥሬ ስጋና ሚጥሚጣ መብላትና ሻይ በቡና ስፕሪስ መጠጣት በጣም የሚወደው ” ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ነብር ዝንጉርጉርነቱን አይለቅም ” የምትለውን አባባል በጣም የሚወደው መንጌ ዜግነቱን መቀየሩ በጣም አስደንቆኛል።
በተረፈ የዝምባበዌን የመፈንቅለ መንግስት ሂደቱን ከተመለከትነው የመንጌ ታክቲክ እንዳለበት ያስታውቃል።
ዝምባቤዎችና ደቡብ ሱዳኖች መንግስቱ ሀይለማሪያምን በጣም እንደሚወዱት የታወቀ ነው። ደቡብ ሱዳኖች ጁባ ላይ እኔ ነኝ ያለ ቪላ ሰርተው ሰጥተውታል ።መንግስቱ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚደንት ሳልቫ ኬርንም እንደሚያማክረው ይታወቃል። ወያኔ በዚህ ጉዳይ በአንድ ወቅት በመበሳጨት አዲስአበባ ያለውን የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ማብራሪያ እስከመጠየቅ ደርሳለች።
በተረፈ ዝምባቤዎች ቢበዛ ሙጋቤን ስልጣን አስለቅቀው በክብር ያስቀምጡታል እንጅ አንዳች ክፉ ነገር አያደርጉበትም። ጫፉን የሚነካው የለም። ሙጋቤ አምባገነን ቢሆንም ለነጭ ተበግሮ የማያውቅ ደምበኛ አፍሪካዊ መሪ ነው ። በአፍሪካዊነት ከቶማስ ሳንካራና ማንደላ ቀጥሎ የሊቢያው ጋዳፊንና ሮበርት ሙጋቤን የሚወዳደር የለም ። ለማንኛውም ሙጋቤ እድሜውም በጣም ስለገፋ ከስልጣን ዘወር ማድረጋቸው ትክክለኛ እርምጃ ነው።

Filed in: Amharic