>

አረና ለቅዳሜ የተራው ሰልፍ በደብዳቤ ተከለከለ (ዮናስ ሃጎስ)

ደብዳቤው ባጭሩ ሲተነተን ‹በኦሮሚያ በሌሎች ብሔር ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለው በደል እንዲቆም የትግራይ ክልል ከፌደራሉ መንግስትና ከኦሮሚያ ክልል ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሆነና በቅርቡ መሻሻል እንደሚታይ እንዲሁም የሮማናት አደባባይ ቅዳሜ ሌላ ፕሮግራም ስለተያዘለት በተጠየቀው መሰረት ወደ አደባባዩ በሚወስዱ መንገዶች ላይ የመኪና ፍሰቱን ማቆም ስለማይቻል› መከልከሉን ነው የሚገልፀው።
***
አረና አሁን ከባድ ፈተና ከፊቱ ተደቅኗል። የትግራይ ሕዝብ ድምፅ ስለመሆኑ፤ በትግራይ ውስጥ ሕወሐትን ለመተካት
ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀህ ተፈቅዶ የሚያውቅባቸው አጋጣሚዎች ውሱን ከመሆናቸው የተነሳ በአንድ እጅህ ጣት መቁጠር ትችላለህ። ካሁን በፊት እነ ሰማያዊ፣ አንድነት፣ ኦፌኮና የመሳሰሉ ድርጅቶች በመስተዳድሩ ሰልፉ ቢከለከልም ከፖሊስ ጋር እየታገሉ መስቀል አደባባይ ድረስ መሪዎቹ ከፊት ሆነው የሕዝብን ጩኸት ሲያሰሙና ለእንግልት ሲዳረጉ ተመልክተናል።

አረናም የትግራይ ሕዝብ በደብዳቤው ላቀረበው ጥያቄ እንኳን ድምፁን ማሰማት የማይችል የታፈነ ሕዝብ እንደሆነ ለማስመስከር ቅዳሜ በጠሩት ሰልፍ ላይ ቃላቸውን አክብረው በመገኘት ሰልፉን ከፊት መምራትና ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

ሲጀመር የሰልፉ ምክንያት ነቀምት ላይ ሞቱ ስለተባለው ሶስት የትግራይ ጎሳ አባላት ብቻ ከሆነ ሕወሃት ሰልፋን ቢፈቅድ የተሻለ ፍላጎቱ የሚሳካና በሰልፉ የራሱ መልህክቱ የሚተላለፍ ይመስለኛል አለመፍቀዱ ምን ይጎዳዋል ብዬ ሳስብ እንደእስትራቴጂ ምንም ነገር የለም ነገር ግን ለአረና ትግራይ ፖርቲ የህዝቡ ምላሽ መስጠትና ሰልፋ ላይ መገኘት በራሱ እንደ ኪሳራ ሊታይ ይችላል።ነገር ግን ሰልፉ በኦሮሚያ፣በአማራ፣በሶማሌ፣በደቡብ፣በቤንሻንጉል በአጠቃላይ በአገራችን ስተፈጠረው ትርምስ፣መፈናቀልና ግድያ ከሆነ እውነትም እንደተባለው የሮማናትን አደባባይ ብቻ ሳይሆን የህወሃት መሪዎችን የሚያንቀጠቅጥ ይሆናል።ለህወሃት ስለ አንድነት ከመስማት በላይ ምን የሚያንዘፈዝፍ ፣የሚሰነጣጥቅ ይመጣል !
የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ለወገኖቹ ግድ እንደሚለው የሚገልጥበት አጋጣሚ የኦሮሞው/የአማራው/የደቡብ ደም የኔ ነው የሚልበት መድረክ ለፊቱ አለ።ከዚህ ማጥ ውስጥ የዘፈቀንን ዘረኝነትን የምናወግዝበት በተለያየ አጋጣሚ በዘረኞች በግፍ ያለቁ ወገኖቻችንን የምናወግዝበት ቢሆን መልካም ነው።
ይህ የቅዳሜው ሰልፍ በከፊል እንኳን ቢሳካ፤ አሊያም ተሞኩሮ እንኳን ቢከሽፍ አረና ባለፉት አራት ዓመታት ያልተጎናፀፈውን ድል እና ስኬት ሊያጣጥም የሚችልበትና ለትግራይ ሕዝብ ደግሞ ዓይን መግለጭጫ የሚሆነው እንቅስቃሴ ይሆናል።
Filed in: Amharic