>
5:13 pm - Monday April 20, 2939

የሕወሐት፣ የኦነግ እና ጀሌዎቻቸው የአማራ ዘር ማፅዳት ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል!!! (ኢ/ር ይልቃል ጌትነት)

በአለፉት 40 ዓመታት በኢትዮጵያ በሕወሐት፣ኦነግና ጀሌዎቻቸው ፀረ አማራ ሁለ ገብ እንቅስቃሴ ዋነኛ የትግል አጀንዳቸው አድርገው በሰሩት የአመለካከት ስርፀት ስራ ፍሬ አፍርቶ በአለፉት 26 ዓመታት የአማራ ጅምላ ግድያ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይ በጨለንቆ፣አርባጉጉ፣በደኖ፣ጉራ ፋርዳ፣ጋምቤላ፣ቤንሻንጉል አረመኒያዊ በሆነ ሁኔታ ሲፈፀም መቆየቱ ሁላችንም የምናውቀው ሀቅ ነው፡፡ በአለፈው ሳምንት በኢሉባቦር የተፈፀመውን ዘግናኝ የአማራ ጭፍጨፋ ሰምተን ሳናበቃ ትላንት ጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ.ም በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ካማሽ ዞን ይህ ፀረ አማራ እንቅስቃሴ አድማሱን አስፍቶ አማሮች ተገለዋል፣ቤት ንብረታቸው በቃጠሎ ወድሟል፡፡ አሁን ከቦታው ደውዬ ባገኘሁት መረጃ መሰረት ከ30 እስከ 40 ሰዎች ተገለዋል፣ከ200 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል የሞቱትን ሰዎች አስከሬን ለማንሳትም ሆነ የሟቾቹን ቁጥር በትክክል ለማወቅ የፀጥታው ሁኔታ ለህወታቸው እጅግ አደገኛ መሆኑን ገልፀውልኛል፡፡ በድርጊቱም የአካባቢው ባለስልጣናትና የአካባቢው የፀጥታ ሀይሎች እንዳሉበት መረጃውን የሰጡኝ ሰዎች አረጋግጠውልኛል፡፡ በአካባቢው የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ ቢገኝም ድርጊቱን መረጃውን እስካገኘሁበት ሰዓት ድረስ መቆጣጠር አልቻለም፡፡ ቁጥራቸው በግምት 1000 አካባቢ የሚጠጋ አማሮች ለአቤቱታ በወረዳው ጽ/ቤት እንደሚገኙም ገልፀውልኛል፡፡
በካማሽ ዞን የተፈፀመውን የአማራ ጭፍጨፋ በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ
ከወረዳው ከተማ ጅብ ከሚበላቸው በሚል አስከሬናቸውን ለመልቀም በጫካ ውስጥ ሲያፈላልጉ ከነበሩ ግለሰቦች እንዳረጋገጥኩት ግለሰቡ እስከ ቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ 20 አስከሬን ማየታቸውን የተገደሉትም በገጀራ፣በቀስት፣በቃጠሎ እና በጩቤ እንደሆነ ገልፀውልኛ። የሶስትና የአራት አመት ህፃናት በጩቤ ተወግተው በወረዳው ክሊኒክ እንደሚገኙና በርካታ ህፃናትና እናቶች ከጭፍጨፋው ለማምለጥ ሸሽተው በከተማው በሚገኝ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ተጠልለው እንደሚገኙ ገልፀውልኛል። የተጠቀሰው አሀዝ ግለሰቡ በአይናቸው ያዩት ብቻ ሲሆን በጥቃቱ የተገደሉት ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ ለማወቅ ችያለሁ።
Filed in: Amharic