>
5:13 pm - Thursday April 19, 2925

ትናንት አምቦ ውስጥም የሆነው ደም የጠማው ቫምፓየር የፈፀመው የተለመደ ድርጊት ነው (ቬሮኒካ መላኩ)

አለም ከቃየል ጀምሮ ብዙ ደም የሚያፈሱ ሰዎችንና ፣ ቡድኖችንና መንግስታትን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በተመለከተ ከፍጥረቷ ጀምሮ እንደ ወያኔ ያለ ጄስታፖ ገጥሟት አያውቅም። ወያኔ ማለት ፋሽዝምና ናዚዝም ሲደመሩ የመገኘው ውጤት ነው። ትናንት አምቦ ውስጥም የሆነው ደም የጠማው ቫምፓየር የፈፀመው የተለመደ ድርጊት ነው። ይሄን ስርአት ነዳጅ ሆኖ የሚያንቀሳቅሰው የሰው ደም ነው።

የአምቦ ህዝብ ሁሌም የሚገርመኝ ህዝብ ነው ። የአምቦ ህዝብ ወያኔ ገና በ 1983 አገር ተቆጣጥሮ አላማውን ከመግለፁ በፊት ቀድሞ ባህሪያቸውን ተረድቶ አንቅሮ የተፋ ህዝብ ነው። የህውሃት በረባሶ ጫማ የመሀል አገሩን ለም አፈርና ለምለም ጨፌ ገና እንደረገጠ ሀይለኛ ሬዚዝተንስ የገጠመው ከአምቦ ህዝብ ነው። ይሄው የአምቦ ህዝብ አንገት ለአንገት ከወያኔ ጋር ከተናነቀ 25 አመታት ሆነው። በፊት በፊት ” አምቦ ” የሚል ስሰማ ለእኔ ወድያውኑኑ በአእምሮዬ የሚመጣው ስእል ” የጥይት ፋብሪካ” እና “አምቦ ውሃ ” ነው።

አምቦ ከእነዚህ እግረ ደረቆች ይልቅ መንግስቱ ሀይለማሪያም ባለውለታዋ ነው። መንግስቱ በአራቱም መአዘን በጦርነት በተወጠረበትና በአገሪቱ ብዙም ፋብሪካ በሌለበት ወቅት ለአምቦ የጥይት ማምረቻ ፋብሪካና የመአድን ውሃ ፋብሪካ ከፍቷል። የአምቦ ጥይት ፋብሪካ በታሪክ ከምናውቀው የዝነኛው ጋፋት የመድፍ ፋብሪካ ቀጥሎ ስመጥር ነው። ህዝቡም ራሱ ጥይት ነው ። አምቦ ከደርግ እነዚህን የልማት ትሩፋቶች ስታገኝ ከወያኔ ግን ያገኘችው ደም ማፍሰስ ነው።

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የአማራና የኦሮሞ ህዝብ በዚህ አናሳ ቡድን ከመገዛት ይልቅ ለመሞት ቆርጦ የተነሳ ህዝብ ነው። ከመገዛት ይልቅ ሞትን የመረጠ ህዝብን በስልጣን መንበር ላይ ቁጭ ብየ እገዛለሁ ማለት ዘበት ነው። የወያኔ የባንቱስታናይዜሽን የመጫዎቻ አመታት ከባከነ ሰአቱ ጭምር ጋር አጠናቋል ። ያላቸው አማራጭ አንድና አንድ ብቻ ነው ዳግም ላይመለሱ ወደመጡበት መመለስ ብቻ ።

Filed in: Amharic