>
5:13 pm - Friday April 20, 9201

ፍጻሜያችን ተቃርቧል ሁሉም ይንቃ! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

…. ይህ ፍጹም ኃላፊነት የጎደለው ልክና ቅጥ ያጣ አረመኔያዊ የግፍ ድርጊት ዓለማችን የዛሬ ሁለት ዐሥርት ዓመታት በሩዋንዳ በቱትሲና ለዘብተኛ የሁቱ ተወላጆች ላይ ካስተናገደችው አረመኔያዊ ግፍ በኋላ በድጋሜ ሲከሰት ይህ የመጀመሪያው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ደግሞ በአንድ ዘር ተወላጆች ላይ በዘራቸው ምክንያት ብቻ ጥቃት ሲፈጸም ይህ በአማራ ተወላጆች ላይ ወያኔ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ እየወሰደ ያለው መጠነ ሰፊ ጥቃት ከዮዲት ጉዲት 842ዓ.ም-882ዓ.ም. ለ40 ዓመታት ከፈጸመችው ጥቃት በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡ ይህ ሰሞኑን በዚህ አረመኔ አገዛዝ የተፈጸመው የግፍ ድርጊት የአንድ ዘር አባላት በመሆናቸው ብቻ 540 ያህል ወገኖቻችንን ከአንድ አካባቢ ብቻ ሲፈጁ የተቀሩትንም ሲያቆስሉና ሲያፈናቅሉ ባለፉት ጊዜያትም በሱማሌና በአኝዋክ ዜጎቻችን የተፈጸመው የጦር ወንጀልና የዘር ማጥፋት ለዚህች ሀገርና ሕዝብ ህልውና ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ በሚገባ የታወቀ ቢሆንም እጅግ በሚደንቅና ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተለይም የሰው ልጆች መብት ያንገበግበናል ከሚሉ ምዕራባውያን መንግሥታት አንድ የተባለ ነገር የለም ለምን? ለምን? እኮ ለምን?

ይህ የግፍ አገዛዝ የተማመነውን አላውቅም ሊያደርገው ካሰበው ሰይጣናዊ ድርጊት ዝግጅቱ የተነሣ ይሄንኛውን ጨምሮ ከዚህም ከቀም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ስለፈጸማቸው የግፍ ድርጊቶች ተከታታይ ክሶች ጉዳይ ፈጽሞ የሚያሳስበው ሆኖ አልተገኘም፡፡ ከንቱ የቁራ ጩኸት አድርጎ ነው እያየው ያለው፡፡ ነገሩን እያደረገው ያለው በዓላማ ነውና ከመታረም ከመስተካከል ይልቅ በተጠናከረ መልኩ መፈጸሙን የሙጥኝ ተያይዞታል፡፡
ከዚህ ቀደም በተጠናና በተቀናበረ መልኩ በተለያዩ ቦታዎች የተፈጸሙ ተመሳሳይ የግፍ ድርጊቶቹ ሊደብቀው ሊያስተባብለው የማይችለው ሲሆንበት ይሄንን የፈጸሙ ከአሥተዳደር መዋቅሩ የወረዳ የዞንና የክልል ባለሥልጣናት እንዳሉ ያምንና ለፍርድ እንደሚቀርቡም ይገልጻል፡፡ ይሁን እንጅ አስቀድሞም ይሄንን የሚለው ለማስመሰል ወይንም ለመልስ ያህል እንጅ ሊያደርገው ባለመሆኑ እስከ ዛሬ ድረስ “እነ እከሌ እነ እከሌ እንዲህ እንዲህ ዓይነት ወንጀል መፈጸማቸው በመረጋገጡ ሕጉ እንዲህ ዓይነት ቅጣት ጥሎባቸው ተቀጥተዋል!” ብሎ ለሕዝብ ሲገልጽና ሲያስቀጣ ታይቶ አይታወቅም፡፡

ከልምዱ እንደምንረዳው እንዲፈጽሙ ታዘው በሌላ ተመሳሳይ ወንጀል ላይ የሚገኙ አባላቱንም ወንጀሉ በሕዝብ ዕይታ ውስጥ ሲሆንና ሊታበል የማይችል ሲሆንበት ለይስሙላ እንደታሰሩ ይገለጽና ግን ወዲያውኑ ወደ ሌላ አካባቢ ተዛውረው እንዲሠሩ ያደርጋል እንጅ አገዛዙ በራሱ እዝ ስር ሆነው ወንጀል ከፈጸሙ አባላቱ ማንንም ተጠያቂ በማድረግ ታይቶ አይታወቅም፡፡ ይህም ጉዳይ ወንጀሉ እየተፈጸመ ያለው በሚገባ ታስቦበት በተጠናና በተቀናጀ መንገድ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

ይሄንን እውነት የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚገባ ያውቃል ይረዳል፡፡ ይህ መሆኑ ከታወቀ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ከመጀመሪያው ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ጥቃቱ ሲፈጸምበት የቆየውና በቀጥታ ያነጣጠረበት አማራው ምን እንደሚጠብቅ ፈጽሞ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ በፍጹም ያልተዘራ ነው የበቀለው “የእሳት ልጅ አመድ” እንዲሉ ያለ አባቱ ነው እየኖረ ያለው፡፡ ሕዝቡ ለመታረድ ተራውን እንደሚጠብቅ የቄራ የእርድ ከብት የረባ ተቃውሞ እንኳን ሳያሳይ በዝምታ እጅና እግሩን አጣምሮ ምንም እንዳልተፈጠረ ተራውን መጠበቁ ለሚያየው ሁሉ የማይታመንና ትንግርት ነው፡፡ ኧረ ምንድን ነው የሆንከው ወገኔ? ተራህን ነው ወይ የምትጠብቀው? እነዚህ በግፍ የተገደሉ ወገኖችህ እኮ ከአማራነታቸው በስተቀር አንድም በደል፣ አንድም ወንጀል የለባቸውም፡፡ ወንጀላቸው እኮ አማራነታቸው ብቻ ነው፡፡

ታዲያ እንዲህ ከሆነ እንዴት እኔን ይምረኛል ብለህ አሰብክ? ይህ ጭራቅ አገዛዝ እነሱን ብቻ በልቶ ይቀር ይመስልሀል? ይተወኛል፣ ያልፈኛል፣ ይምረኛል ብለህ ተስፋ የማይደረግ ነገር ተስፋ አድርገህ ከሆነ መበላትህ ነው ለዘር እንኳን ሳትተርፍ ማለቅህ ነው መፈጀትህ ነው፡፡ ቀን ያልፍ ይሆናል ብለህ እንጀራህን፣ ድርሻህን፣ የራስህን ማዕድ እየነጠቀ ሲበላብህና የበይ ተመልካች ሆነህ በችጋር እየተቆላህ እየተጠበስክ አኗኗሪ መሆንህንስ ችለኸው ኖርክ፡፡ ሲያቅትህም እግርህ ወዳመራህ እየተሰደድክ የበረሀ አውሬና የባሕር ዓሣ ሲሳይ ሆነህ እያለቅህም ከችጋርህ ጋር ቆየህ እንዲህ ተዋርደህ ተሰቃይተህ ያቆየሀት ነፍስህ ያልፋል ያልከው ቀን ሳያልፍ ተደፍታ የምትቀር ከሆነ ከዚህ በኋላ ያለህ ትዕግሥት ለምንህ ይሆናል?

ተው ሳይቀድምህ ቅደመው? ተው ተበላህ? ተው አለቀልህ? ኧረ ምን ጉድ ነው? ኧረ ተው ኧረ ተው? በምኖች እጅ እንዳለህ እኮ ፈጽሞ አላወከውም! እንዳንተ አስተዋይነት፣ እንዳንተ አርቆ አሳቢነት፣ እንዳንተ ኃላፊነት እንደሚሰማው ዜጋነትህ፣ እንዳንተ ትዕግሥት መስሎሀል እንዴ? ፈጽሞ አላወከውም አለማወቅህ ሊያስበላህ ነው፣ ቅንነትህ፣ ታጋሽነትህ፣ አሳቢነትህ ሊያስጨርስህ ነው፡፡ ተው በጊዜ ንቃ የሞት ሰው መሆንህ ካልቀረ ገለኸው ሙት የሚቀረው ልጅህ ቀን ይውጣለት፡፡ በደምህ ዘርህን ታደግ ትውልድህን ነጻ አውጣ፡፡ ቀንህን ጠብቀው መፍጀታቸው ካልቀረ ነፍስህ በከንቱ አትለፍ ሀገርንና ሕዝብን የሚታደግ ቁምነገር ሥራባት፡፡ ገለኸው ሙት ጉርቦውን እነቀው፡፡ ተው ተነሥ አለቀልህ! የቀኑ ቀን እማ የመጨረሻው ቀንማ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ያ ቀን እኮ ካንተ ይልቅ የሚመቸው ለሱ ነው፡፡ ያኔማ ምን መላወሻ አለህ? ተረፍርፈህ ከማለቅ በስተቀር ምን አማራጭ የሚኖርህ መሰለህ?
ወያኔ በሰነዱ አስፍሮት እንዳየኸው እንደሰማኸው “አያጅባጅቦ ሳታመሀኝ ብላኝ” እንዲሉ አብሮ ለመኖር፣ ተከባብሮ ለመኖር፣ እንግዳን ለማስተናገድ ያለህን በሃይማኖታዊ አስተምህሮ የታሸ የበሰለ ባሕል ሸምጥጠው በመካድ “አማራን ለጥቃት የሚዳርገው ትምክህተኛነቱ ነው! ይሄንን ትምክህት ይዞ ከሌላው ሕዝብ ጋር ሊኖር አይችልም!” ብለው ቆርጠውብሀል፡፡ አይተሀል ሰምተሀል፡፡ እውን አንተ እንደዚያ ሆነህ ነው? ወይስ ለማጥቂያ ምክንያት ሲፈለግልህ?

ደናቁርት የወያኔ ጭፍሮች ሆይ! ትምክህት መሠረት ካለው የሚያኮራ እንጅ እንዴት ነው የሚያሳፍር የማይፈለግ እንዲጠፋ የሚፈለግ ሊሆን የሚችለው? ይሄ ትምክህት ከየትም የመጣ ወድቆ የተገኘ ይመስላቹሀልን? ይህ ትምክህት ተፈልጎ የመጣ ሳይሆን ለሽዎች ዓመታት ከነበረን የሥልጣኔ፣ የነጻነት፣ የማንነት እሴቶችን ለመፍጠር በተደረገ ድካም፣ ውጣ ውረድና ታሪክ የተነሣ በራሱ ጊዜ የተፈጠረ የሥነልቡና ሀብት ነው፡፡
ደናቁርቱ ይህ የሕዝባችን ማንነት ምን ያህል እንደተደከመበት፣ ምን ያህል መሥዋዕትነት እንደተከፈለበት እያወቁ ለሀገራችን ታሪክ፣ ቅርስ፣ ማንነት ካላቸው ጠላትነት የተነሣ “ይሄንን ቅርስህን ታሪክህን ማንነትህን ጣልና ባዶ ሁን፣ ቀፎ ሁን፣ አልጫ ሁን!” እያሉ እየተጫኑት፣ እያስገደዱት እያዋከቡት ግራ እያጋቡት ይገኛሉ፡፡ ወያኔ “ትምክሕት” የማንነት ምስክራችን መሆኑን፣ ቅርሳችን መሆኑን፣ የቀረልን ሀብታችን መሆኑን፣ የወደፊት የመነቃቂያ ጉልበታችን መሆኑን፣ የወኔ ምንጫችን መሸነጫችን መሆኑን ጠንቅቆ ስለሚያውቅና ስለሚያሳስበው ትምክህታችንን ከልቦናችን፣ ከደማችን ላይ ነቅሎ ጥሎ ገልቱ፣ ስልብ፣ አልጫ፣ ጀሌው አድርጎን ሊቀር በርትቶ እየሠራበት ነው፡፡ ወያኔ በአማራ ላይ ስለሚያመር እንጅ ትምክህተኛ አማራ ብቻ ነው ያለው ማን ነው? በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለዚህች ሀገር ሥልጣኔ፣ ማንነትና ነጻነት ድርሻ የሌለው የለምና ይበላለጥ ካልሆነ በቀር በዚህች ሀገር ታሪክና ማንነት ትምክህት የማይሰማው ወይም ሊሰማው የማይገባው ብሔረሰብ ማን አለ? በግለሰብ ደረጃ ግን የዚህችን ሀገር ጥፋቷን የሚመኙ የጥፋት ልጆች አሉና ከዚህ ጠላትነታቸው የተነሣ እነሱ ማውደም፣ ማጥፋት በመቻላቸው በዚህ ሥራቸው እብሪትና ትዕቢት ይሰማቸው ካልሆነ በስተቀር በምንም ተአምር ትምክህት ሊሰማቸው እንደማይችል ለማንም ግልጽ ነው፡፡
እኔስ እኮራለሁ ፤ ቅርሴ ነው ትምክሕቴ
በደም የወረስኩት ፤ ከእናትና አባቴ
የትንሣኤየ አቅም ፤ መነሻ ጉልበቴ
ትምክሕቴ ነው ውርስ ፤ ቅርስ የታሪክ ሀብቴ፡፡
ትልቅ እንደነበርን ፤ ትልቅ እንሆናለን
ያለው እኮ ካሳ ፤ ተናግሮ ኃይለ ቃልን
ለማገናኘት ነው ፤ ትናንትና ነገን፡፡
የሀገርን ታሪክ ፤ ታሪኬ ካላሉት
ከወዴት ይገኛል ፤ ያ ቅርስ ትምክሕት?
አንተ ባንዳ ሆነህ ፤ ከነ ዘርማንዘርህ
ስታደማ የኖርክ ፤ ለሀገር ጠላት አድረህ
ታዲያ ትምክህቱ ፤ ከወዴት ይምጣልህ?
ተከናነብ እንጅ ፤ ውርደት እንደ አባትህ፡፡
ከጥንት ከመሠረት ፤ ሳይደከምበት
ከእናትና ከአባት ፤ ሳይወራረሱት
ግራ ቀኝ ቢያፈጡ ፤ ከየት ይገኛል ትምክሕት?

በውጪ በስደት ያላቹህ ወገኖቻችን ሆይ! ፡-
ይሄውላቹህ እንግዲህ የእኛ መጨረሻ ይሄው ሆኗል፡፡ የቀን ጉዳይ ነው እንጅ ሳንሞት ሞተናል፡፡ ነፍሳችን ሳይወጣ ሞተን ተቀብረናል፡፡ መቸም ይሄንን እየሰማህ ሥራው ይሠራልህ፣ መብሉም ይበላልህ አይመስለኝም፡፡ ከዚህ የከፋ ነገር የለህምና ሥራዬ ምኔ ሳትል ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከሃይማኖት መሪ እስከ ሕዝባዊ፣ ከምሁሩ እስከ ጨዋው ሁላቹህም የሚሰማህ፣ የሚረዳህ፣ የሚደርስልህ መንግሥት ባይኖርም አማራ ብቻ ሳትሆን ሌላውም የኢትዮጵያ ልጅ የሐበሻ ዘርም ቢሆን በወያኔ ያልተጎዳ ዘር የለምና ሁልህም በያለህበት ሀገር አንድላይ አደባባይ ወጥተህ ለእግዚአብሔርና ለታሪክ እሪ በል አሰምተህ ጩህ፡፡ መጨረሻችን ይሄውና እንዳለቅን እንደተፈጀን ቆጥረኸን አልቅስልን፣ ሙሾህን አውርድልን፣ እንባህን ተራጭልን፡፡ ይሄንን ባታደርግ ግን እርም እንደበላህ ቁጠረው፣ እንደሸጥከን፣ እንደከዳኸን ቁጠረው፣ ደማችንን ደመ ከልብ እንዳደረከው ቁጠረው፡፡

ወገኔ ሆይ! መንገድ ቢሠራ ሕንፃ ቢደረደር ግድብ ቢገነባ ምን ቢያደርግ ላንተ እንዳይመስልህ፡፡ እንዲህ እንዲህ እያደረገ በምታውቀውም በማታውቀውም ጥቃቱ መጦ ጨርሶህ ለራሱ ተዝመንምኖ ሊኖርበት እንጅ፡፡ ከአያያዙ ዕይና ተረዳ ላንተ አስቦ እንዳይመስልህ፡፡ ከድርጊቱ እወቅ፣ ከአስተሳሰቡ ገምተው፣ ከአፈጻጸሙ ንቃ፡፡ ለሕዝብ በማሰቡ ይመስልሀል እርስ በእርስህ አፋጅቶ ሊያጫርስህ የሚጥረው? የብሔረሰቦችን እኩልነት በማመኑ ይመስልሀል ጥቂትም የነበሩትን የሌላ ብሔረሰብ ተወላጆችን እየፈነገለ ሥልጣን የተባለውን ሁሉ በራሱ ዘር ብቻ እንዲያዝ ያደረገው? ላንተ ስላዘነ ይመስልሀል የሀገሪቱን ሀብት ሁሉ በፓርቲውና በግለሰቦቹ እጅ ጠቅልሎ የያዘው? ወገኔ ሆይ! ይሄ ይሄ ካላነቃህ ሌላ ምን ሊያነቃህ ይችላል?
የበረሀ አውሬ ፤ አለምዳለሁ ብሎ
ሰይጣንን መልአክ ፤ ሊያደረግ ተስፋ ጥሎ
ወገኔ አለቀ ፤ በየዕለት ተገሎ
ለሰይጣን አምልኮው ፤ መሥዋዕት ታድሎ
አፉን እንደዘጋ ፤ በአዚም ታጅሎ፡፡
ተበልተህ አትለቅ ፤ ተው ስማ ተው ስማ!
በሀገሩ ሰው ሳያልቅ ፤ ሳትሆን ውድማ፡፡
ወኔህ ተቀስቅሶ ፤ ዘራፍ ብትልማ
ማን ከፊትህ ሊቆም ፤ ምኑም አይሰማ፡፡
የሚገባበትም ፤ ድራሹ አይታወቅ
እንደዚህ መሆኑ ፤ ላንተም እስከሚደንቅ፡፡
እንዲህ ከብዶ የታየህ ፤ ቋጥኝ ተመስሎ
ገለጥ ብታደርገው ፤ ባገኘኸው ቀሎ፡፡
ገለባ ቢከመር ፤ ተራራ አክሎ
ያለ የሚመስለው ፤ እስኪነሣ ነው አውሎ፡፡
ለዘር ትረፍ ካለህ ፤ በሰይፍህ ተቀስፎ
መሆኑን ታያለህ ፤ ባዶ የንብ ቀፎ፡፡
ከቀየህ መብቀሉን ፤ ወገንነቱን ዐይተህ
ስምክን ይዟልና ፤ አንተን የሆነ መስሎህ
እጅግ ተዘናጋህ ፤ ባዕድ አልመጣ! ብለህ፡፡
ከጠላትም ጠላት ፤ ሆኖ እንደከፋብህ
እንድታውቅ አድርጎ ፤ ማን የት በነገረህ?
ጉዞህ ከአውሬ ጋራ ፤ መሆኑን ካወከው
መቅደምህ ብቻ ነው ፤ ነፍስህን የሚያተርፈው፡፡

ለወያኔ ተሰልፈህ እንደዜጋና እንደሰው ለምን? እንዴት? ሳትን የገዛ ወገንህን እየጨፈጨፍክ ያለህ የመከላከያ የፌዴራልና የፖሊስ ሠራዊት አባላት ሆይ! ፡-
ይሄንን ድርጊት በገዛ ወገንህ ላይ ምንም የሠራው ወንጀል እንደሌለ እያወክ ጨክነህ ስለፈጸምክ ወያኔ አንተን ይምርሀል እንዳይመስልህ፡፡ ከእሱ ጋር በድሎት የምትኖር እንዳይመስልህ፡፡ እንድትሠራለት የፈለገውን ሠርተህ ከጨረስክ በኋላ ቀጣዩ ኢላማው ከራሱ ዘር ውጪ የሆንከው የመከላከያ ሠራዊትና የጸጥታ ኃይሉ አባላት መሆንህን እወቀው፡፡ አእምሮ ካለህ፣ ማስተዋሉ ካለህ ይሄንን ጉዳይ ከወያኔ ታሪክ ትረዳለህ፡፡
የምትተርፍ እየመሰለህ ፤ ማንነትህን ብትከዳ
አማራ አይደለሁ እያልክ ፤ ብትገባም ሌላ ጓዳ
እሱ እንደሆን አይተውህ ፤ ይጨርስሀል ለቃቅሞ
ሱማሌነት አላዳነ ፤ አኝዋክ ነኝ ማለት ኦሮሞ፡፡

ወያኔን በታሪኩ እንደምታውቀው ወያኔ ማለት ለተራና ነውረኛ የፖለቲካ ትርፍ ሲል ሆን ብሎ ቀጥሮ ሀውዜን ላይ የገዛ ወገኖቹህ እንዲጨፈጨፉ ያደረገ አረመኔ ነው፣ ወያኔ ማለት ትግሬ ስላልሆኑና ስለፈራቸው ብቻ በሐሰት ክስ ወንጅሎ አብረውት ታግለው የገቡትን የሌላ ብሔረሰብ አባላትን የሚገል፣ የሚያስር፣ የሚያባር ወራዳ ውለታቢስ የአንድ ጎጥ የወንበዴ ቡድን ነው፣ ወያኔ ማለት በምርጫ 97ዓ.ም. ላይ “ስለገደሉ ገደልኩ” ለማለት ለተቃውሞ የወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞችን ለመምታት ከተሠማሩት ውስጥ ሰባት/ዘጠኝ የሚሆኑትን የገዛ ኃይሉን ከኋላ አዘጋጅቶ ባስቀመጣቸው መትቶ ከገደለ በኋላ 199 ሰላማዊ ሠልፈኞችን የገደለ ሌላም አንተ የምታውቀውን እኛ የማናውቀውን ብዙ ዓይነት ግፍ፣ ሸፍጥ፣ ሸር የፈጸመና እየፈጸመ ያለ አረመኔ አገዛዝ ነው፡፡
እናም ከትግሬ ውጭ ያለህ የመከላከያና የጸጥታ ኃይል አባላት ሆይ! ቀንህ እስኪደርስ ነው እንጅ ለአንተም ለእያንዳንድህ ቢሆን ይመለስልሀል እንዳይመስልህ፡፡ ቀንህን ነው የምትጠብቀው ልዩነት የለንም ቶሎ ነቅተህ ካልቀደምከው በስተቀር የቀን የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ አንተም እሬሳ ነህ፡፡ ብትቀድመው ነው የሚሻልህ ጊዜ የለህም ቶሎ ንቃ! ሕዝብ ላይ፣ ወገንህ ላይ፣ እናትህ ላይ፣ አባትህ ላይ፣ እኅትህ ላይ፣ ወንድምህ ላይ ያነጣጠርከውን አፈሙዝ መልሰህ አንሥተህ ከራሱ ግንባር ላይ አርከፍክፍበት፡፡ ሞትህን ገድለኸው በሞትህ ላይ ፎክርበት! እራስህን ነጻ አውጣ! ነፍስህን ከጭራቅ አትርፋት፡፡ ሀገር ሕዝብህን ታደግ፣ የሚያኮራህን ታሪክ ሥራ! ጊዜ የለህም ፍጠን የአፍታ ጊዜ ካባከንክ ያልቅልሀል መበላትህ ነው፡፡ አንተ ብቻ ትንሽ ድፈር በጣም ቀላል ነው ከቁርስ አያልፍም ፍጠን! ፍጠን! ወገን ፍጠን!
ቁረጥ ቁረጥ ስለው ፤ ገና ሲያመነታ
ድንገት ቆርጠው ጣሉት ፤ ከነእንቅልፉ ለአፍታ፡፡
መቅደም እንጅ ነበር ፤ የወንድነት ግብሩ
ነገን ዛሬ ላይ ዐይቶ ፤ በቁም ሳይቀበሩ፡፡
እስኪቀደሙማ ፤ ቆመው ካንቀላፉ
ምን አለው ለሬሳ ፤ መቀበር ነው ትርፉ፡፡

የትግሬ ህዝብ ሆይ! ፡-
ወያኔ ይሄንን ሁሉ ግፍ የሚሠራው ለአንተ ጥቅም ሲል እንደሆነ ሲነግርህ ቆይቷል አንተም ታውቃለህ፡፡ ወያኔ በሚሠራው ሥራ ሁሉ ያንተ ብርቱና የማያወላዳ ድጋፍና ይሁንታ እንዳለው በአጽንኦት ይገልጣል ይሄንንም ታውቃለህ፡፡ ወያኔ በቻለው መጠን ሁሉ መተለየና ፍጹም ኢፍትሐዊ በሆነ መንገድ አንተን ተጠቃሚ ለማድረግ ሲጣጣር “አይ! ይሄማ ሕገ ወጥ ተግባር ነው ከሌላው ሕዝብ ጋራም ያቃቅረኛልና አይሆንም አልፈልግም!” አላልክም፡፡ ይልቁንም “በረሀ እያለ አደርግላቹሀለው ብሎ ቃል የገባልንን እስከዛሬ ድረስ አላደረገም ተከድተናል!” የሚል ቅሬታ እንዳለህ ይነገራል ይሰማል፡፡ እጅግ በሚገርምና በሚያሳዝን መልኩ ይሄ ምን ማለት እንደሆነ ግን ጨርሶ አልገባህም፡፡ ይህ አንተን መከታ ያደረገ ግፈኛ አገዛዝ ያንተን ክንድ ተደግፎ ለሚሠራው ወንጀል ሁሉ ኃላፊ መሆንህን አልገባህም አልተረዳህም፡፡ ወይም ይሄ መሆኑን አምነህ ተቀብለሀል፣ ኃላፊነቱን ለመውሰድም ተዘጋጅተሀል ማለት ነው፡፡

ወያኔ እስከአሁን ያንተን ውክልና ይዞ በሠራው ግፍ ያልወደድከው ኖሮ በግልጽ “አይ! በስማችን እየተጠቀምክማ ይሄንን ልታደርግ አትችልም!” ስትል ታይተህ ተሰምተህ አታውቅም፡፡ ይልቁንም የሞቀ ድጋፍህ እየተቸረው ይገኛል፡፡ አሁንም ይሄ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ጨርሶ አልገባህም፡፡ ወያኔ በሚያሴረው ሰይጣናዊ ሴራ ዛሬ ዓለም አንድ መንደር ሆና ዜጎች ባሕር ተሻግረው ሁሉ በባዕዳን ሀገራት ሠርተው በሚኖሩበት ዘመን የአማራ ተወላጆችን እናት አባቶቹ ለነጻነቷና ለህልውናዋ በሞቱላት አጥንታቸውን በከሰከሱ ደማቸውን ባፈሰሱላት በገዛ እናት ሀገሩ ከተለያዩ አካባቢዎች ውጡ እያሰኘ ወልደው ከብደው ከየኖሩበት ቀየ እያፈናቀለና እየገደለ እንደቆየ ታውቃለህ፡፡ ይሄም ምን ማለት እንደሆነ ፈጽሞ አልገባህም፡፡

ወያኔ በአንተ ስም ይሄንን በማድረጉ ግን፤ መቸም የታሪክ እውነታ ነውና ከታሪክ እውነታ ውጭ ደሞ ለአንተ ተብሎ የተለየ ነገር ሊሆንልህ አይችልምና ነገ ቀን ሲለወጥ ወያኔ ክፉኛ እንዲያቄምብህ ባደረገው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህ “ውጡልን!” የሚለውና የሌላውም ጥቃት እጣ ባንተ ላይ ቢደርስ ልትለው የምትችለውን አንድም ነገር እያሳጣህ እንደሆነ ከቶውንም ሊገባህ አልቻለም፡፡ የሰው ጭንቅላት የያዝክ እስከማይመስል ድረስ ተደፍነሀል፡፡ ገብቶህም ከሆነ ከወዲሁ ልትወስደው የሚገባህን እርምጃ ስትወስድ ጨርሶ ታይተህ ተሰምተህ አታውቅም፡፡ እናም ብዙ ሊገቡህ ያልቻሉ የከፋ ዋጋ የሚያስከፍሉህ ነገሮች አሉ፡፡ ገብቶህም ከሆነ የማስተካከያ የማረሚያ እርምጃዎችን አለመውሰድህ ዕዳው ያንተ መሆኑን አላወክም ወይም ኃላፊነቱን ለመውሰድ ወስነሀል ማለት ነው፡፡ ይህም ምን ማለት እንደሆነ ፈጽሞ አልገባህም እጅግ እጅግ እናዝናለን፡፡ አንድ እውነት ግን እወቅ ሰው የዘራውን ያንኑ ደግሞ ያጭዳል!
“ነጻነቱ ስለሌለኝ እንጅ ሳይሰማኝ ቀርቶ አይደለም፡፡ እኔም እኮ ችግር አለብኝ እንዴት ብየ የተቃውሞ ድምፅ አሰማለሁ?” የሚል ምክንያት ቢኖርህ ተቀባይነት ሊኖረው የማይችልበት ምክንያት ቢያንስ እንደሌላው ብሔረሰብ ሁሉ በተለያየ መንገድ ቅሬታህን ማሰማት አልቻልክም፡፡ ሌላው ሕዝብ እየሞተ እየወደቀ አይደለም ወይ ተቃውሞውን እያሰማ ያለው? የወያኔ አኪያሔድ ከገባህ አደጋው የሚከፋው ላንተ መሆኑን ተረድተህ ከሌላው ሕዝብ በላቀ ጽናትና ቁርጠኝነት እየሞትክ ተቃውሞህን ልታሰማ የሚገባህ አንተ አልነበርክም ወይ? አሁንም እንደሌላው ብሔረሰብ ሁሉ ከሀገር ውጪ ባሉ ልጆችህ እንኳ የተቃውሞ ድምፅህን ማሰማት የምትችል ሆኖ እያለ ይሄንን ዕድልም ልትጠቀምበት አልቻልክም፡፡ እዚያ ያሉ ልጆችህም እንዳንተ ሁሉ አግባብነት በሌለውና እግጅ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ፍጹም ጭፍን ድጋፋቸውን ለዚህ ደንቁሮ ላደነቆረህ አገዛዝ፣ ከአህያ የተሻለ ማሰብ ለማይችል የጎጥ ቡድን የሚሰጡ ብቻ ናቸው፡፡ ይሄ ምን ማለት እንደሆነ እነሱም አልገባቸውም፡፡ እናዝናለን ምን ማድረግ ይቻላል? ብቻ እንዳወቅንህ እንድታውቅ፡፡ ህልውናህን ከወያኔ ህልውና ጋር ማጣበቅህ ማቆራኘትህ እንዴት ብስለት መስሎ እንደታየህ እጅግ እግጅ የሚገርምና ከአንድ ሕዝብ ሊጠበቅ ሊታይ የማይችል የደነቆረና ያልተለመደም አስተሳሰብ ነው፡፡

ወያኔ የሠራልህ የጠቀመህ የበጀህ መስሎሀል፡፡ ነገር ግን ሠርቶልህ ሳይሆን ሠርቶብህ፣ ጠቅሞህ ሳይሆን አሲሮብህ እንደሚሔድና እንዲህ የተንሰፈሰፍክለትን ያህል ወያኔን አምርረህ የምትረግምበት ዘመን እንደሚመጣ ልትጠራጠር አይገባም፡፡ አርቆ ማሰብ ከቻልክ ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ልታደርገው የምትችለውን ነገር አድርገህ የማይቀረውንና ደስ የማይለውን ክፉ ቀንህን ለማስቀረት እንድትችል ስመክርህ ከልብ እያዘንኩልህ ነው፡፡ ልብ አድርግ! ይሄንን ማድረግ የምትችለው ዛሬ እንጅ ነገ አይደለም፡፡ ነገማ ሌላ ቀን ነው……

ይህ ጽሑፍ ከሦስት ዓመታት በፊት ወያኔ በአማራ ተወላጆች ላይ ከመዠንግር ተወላጆች የተቃጣ የተፈጸመ ጥቃት አስመስሎ በፈጸመው ጭፍጨፋ ወይም የጅምላ ግድያ ወይም የዘር ማጥፋት ወንጀል ከ540 በላይ ወገኖቻችን በተጨፍጭፉ፣ ከ25 ባለይ ቤቶች በኗሪዎቹ ላያቸው ላይ እንደተዘጉ እሳት ተለቆባቸው እንዲቃጠሉ በተደረጉ፣ ከዚህ የተረፉት ሕፃናት እናቶች አረጋውያን ዕድሜ ልክ የለፉበት ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተፈናቅለው እንዲሰደዱ በተደረገ ጊዜ “አርማጌዶን የፍጻሜያችን ፍጻሜ!” በሚል ርእስ ከጻፍኩት ጽሑፍ ላይ የተወሰደ ነው፡፡ ሰሞኑንም ወያኔ ኦሮሚያ ብሎ በሚጠራው የሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ቁጥራቸው ያልታወቁ ወገኖቻችን አማራ ስለሆኑ ብቻ በወያኔ በኦነግና በኦሕዴድ በተሸረበ ሴራ ተገድለዋል፣ ሕፃናት ነፍሰጡር እናቶች አረጋውያን ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፣ ተሰደዋል፣ እንደአውሬ በየጫካው እንዲወሸቁ ተደርገዋል፡፡ በመሆኑም ጥሪውን በድጋሜ ማሰማት አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘሁት በድጋሜ ለጠፍኩት፡፡ በየ ክፍሉ ጥሪው የቀረበልን ወገኖች ሆይ! እባካቹህ ዘግይተን መቀልበስ የማንችለው የምንፈራው ችግር ከመፈጠሩ በፊት ማድረግ የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ፈጥነን እንነሣ!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

Filed in: Amharic