>

"የናቁት ወንድ ያስረግዛል - ሊያውም መንታ መንታ" (ቬሮኒካ መላኩ)

1~ ለግማሽ ሚሊዮን የኦሮሞ ተወላጆች መፈናቀል ምክንያት የሆነው የአሁኑ የሱማሌና የኦሮሞ ክልል ግጭት ከመከሰቱ ወራት በፊት አንድ የኦሮሞ ብሄርተኛ ዋና አክቲቪስት የፃፈው ፅሁፍ እስካሁን ይገርመኛል ። ይሄው አክቲቪስት ” እኛ ኦሮሞዎች ከፈለግን ሱማሌን በአንድ ቀን እስከ ህንድ ውቅያኖስ ድረስ ጨምረን መምጣት እንችላለን ።” አለ ።
“የናቁት ወንድ ያስረግዛል – ሊያውም መንታ መንታ” ሆነና የተናቀው ሱማሌ በአብዲ ኢሌ አ የተመራ የኦሮሚያ ወረዳወችን በብርሃን ፍጥነት ተቆጣጥሮ ህዝቡን እያፈናቀለ ባንድራውን ይቸክለው ጀመረ። ይሄ የሱማሌና የኦሮሞ ግጭት የ6 ቱን ቀን የአረብ እስራኤል ጦርነት ያስታውሰኛል።
ይሄው አክቲቪስት ጉራውን ትቶ ማልቀስ ጀመረ ።

2~አሁን የሱማሌ ክልል በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከማንም በላይ ዋና ተዋናይና የሀይል ሚዛን መለኪያ እየሆነ ነው።

ዛሬ የሱማሌ ክልል ያወጣው መግለጫ ትንሽ ያስፈራል ። ነገሮች እየተባባሱ እንጅ እየቀለሉ እንዳልሆነ መገንዘብ ይቻላል።
አብድ ኢሌ እና ክልሉ ገና ከኦሮሚያ Claim የሚያደርገውን መሬት ካልተሰጠው ጦርነት እንደሚያውጅ ሁሉ ፍንጭ ሰጥቷል። የዚህን ውጤቱን ወደፊት የምንመለከተው ይሆናል።

3~ ዛሬ አንድ የጃጄ ሽማግሌ አገሩን ሁሉ የአማራ ህዝብ መሰረት እስከሆነችው እስከ ወሎ ያካለለ የኦሮሚያ ካርታ ተሸክሞ ተመለከትኩኝ። ሰዎቹ በግራ በቀኝ እየተገረፉም የሰው መሬት የማግበስበስ ፍላጎታቸው ይገርማል።
መለስ ዜናዊ ከ 1983 በፊት አማራን የጎዳሁ ብሎ ከአማራውም ፣ ከሱማሌውም ፣ ከደቡቡም ከአፋሩም መሬት ቆንጥሮ ቆንጥሮ ለሌንጮ ለታ አስረከበው ።በዚህም የተነሳ የአገሪቱን 1/3ኛ መሬት ካለአግባብ ኦሮሚያ በሚል ስም ተረከቡ። ከ25 አመታት በኋላ ወያኔ ኦሮሚያ የሚባለው ክልል የማይገባውን የህዝብ መሬት እንዳግበሰበሰ ገባትና ለሱማሌውም ፣ለደቡቡም ለአፋሩም ከኦሮሚያ የተወሰደበት መሬት እንድያስመልስ የሞራልና የመሳሪያ ድጋፍ እየሰጠች ክልሉን ወጥራ ይዛዋለች። ኦሮሞም ይሄን መቋቋም የሚችል አይመስልም።

Filed in: Amharic