>

የመስቀሉ ስር ቁማርተኛው ህወሀት (ቬሮኒካ መላኩ)

ሜቴክ ከምስረታው ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከሰራቸው የተሳካ ፕሮጀክቶች ብቸኛው አድግራት ተራራ ላይ በአለፈው አመት የተከለው አርቲፊሻል የብረት መስቀል ነው ። ዘንድሮ ደሞ መቀሌ ላይ የብረት መስቀል እየሰራ ነው አሉ።
የአድግራቱ መስቀል የተሰራው በጦርነት የተቃጠሉ ታንክ ብረቶችን አቅልጦ ሲሆን የመቀሌው መስቀል ደሞ የሚሰራው ለስኳር ፋብሪካ የተገዛውን አርማታ ብረት በመውሰድ ነው። ከታንክ ብረትና በተሰረቀ አርማታ በተሰራ መስቀል መዳን ካለ ልናይ ነው ። ዛሬ ስለመስቀሉ ስር አጭበርባሪዎች አጠር አድርጌ ልፃፍ ። መንፈሳዊና ታሪካዊ ሀብቶቻችን እየተዘረፉ ስለሆነ መጠንቀቁ አይከፋም

ይች ፎቶው ላይ የምትመለከቷት ቤተክርስቲያን የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት የቀኙ ሙሉ ግማደ መስቀል የሚገኝባት ግሸን ደብረ ከርቤ ማሪያም ቤተክርስቲያን ናት ።ይች ታሪካዊና መንፈሳዊ ቤተክርስቲያን በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ተራራ ላይ ትገኛለች።
የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል በአለም ላይ አራት አገሮች ተከፋፍለውት የነበረ ሲሆን የቀኙ ግማደ መስቀል ለኢትዮጵያ ደርሷት ግሼን ደብረ ከርቤ ቤተክርስቲያን ይገኛል ።

ይሄ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ የመጣው በአፄ ዳዊት ዘመነ መንግስት ነው።አፄ ዳዊት ከ1365ዓ.ም እስከ 1395 ዓ.ም ለ 30 አመታት ኢትዬጺያን ያስተዳደሩ ንጉስ ነበሩ ።
ይሄ መስቀል ከ615 አመት ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ዐፄ ዳዊት በታላቅ አጀብ መስቀሉን እጅግ ብዙ ካህናትን አስከትለው በታላቅ አጀብ በጸሎት፣በወረብ፣በዝማሬ ግሸን ማሪያም አሳርፈውታል።

ዛሬ ስለግሼንም ሆነ ስለጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ መስቀል ልፅፍ አልተነሳሁም። ስለመስቀሉና ስለቤተክርስቲያኗ ለማውራት ያለኝ እውቀት እጅግ ውስን ነው ።
የዛሬው አላማዬ የአማራ ክልላዊ መንግስት እና Amhara Mass Media Agency የመስቀል በአልን ትኩረት በመስጠት በአማራ ክልል የምትገኜውን የጌታችን መስቀል በሚገኝባት ግሼን ማሪያምን በሰፊው በሚዲያ እንድያስተዋውቅ እና የመንፈሳዊ ቱሪስት ማእከል እንድያደርጋት ለማስገንዘብ ነው ። ይሄን በማድረጉም ህዝቡን አሁን እየተነሱ ያሉ “የመስቀሉ ስር አጭበርባሪዎች ” ለመታደግም ነው።

የዚህ ሁሉ አላማ ታሪካዊና መንፈሳዊ እሴቶችን ዝርፊያና ሽሚያ ነው ። በአለፉት አመታት የአማራውን “ሻዴይ” ቀስ በቀስ “አሸንዳ ” በሚል በመውሰድ የራሳቸው ብቻ እንደሆነ ለአለም ሲያስተዋውቁ ቆይተዋል። ከባለፈው አመት ጀምሮም የመስቀልን በአል EBC ቴሌቪዥን ቀጥታ ከአድግራት እንድተላለፍ በማድረግ የታንክ ብረት ቀልጦ የተሰራ አርቲፊሻል መስቀል በማሳየት ህዝቡን ሲያጭበረብሩ ነበር። አሁን የተያዘው የመንግስት ሚዲያን በመጠቀም በፕሮፓጋንዳ በታገዘ መልኩ የታሪክና የመንፈሳዊ ሽሚያ በማድረግ ማጭበርበር ነው ።
ባለፈው እዚህ ፌስቡክ ላይ አንድ ትልቅ ቁምነገር ያለው ቀልድ ሲነገር ነበር ። ቀልዱ “ትልቅ ሀይቅና ቄጤማ ሳር ቢኖራቸው ኖሮ ኢሬቻም የእኛ ባህል ነው ከማለት አይመለሱም ።” የሚል ነበር። ይሄ ቁምነገር አዘል ቀልድ የሚያመለክተን እየተዘረፍን ያለነው ቁሳዊ ሀብታችንን ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊና ታሪካዊ ሀብታችንንም ጭምር መሆኑ ነው ።
ይሄ ፈፅሞ መወገዝ ያለበትና ሁላችንም “የመስቀሉ ስር አጭበርባሪዎችን ” በማጋለጥ መታገል የሁላችንም የውደታ ግደታ ነው።

Filed in: Amharic