>
5:13 pm - Sunday April 19, 3316

በመላው ኦሮሚያ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ (ጁሃር መሃመድ)

ቡድን በማሰማራት በሃረርጌ በቦረና እንዲሁም በባሌ አካባቢ ያሉትን የኦሮሚያ ድንበሮች አቋርጥ በመግባት ከመቶ በላይ የኦሮሚያ ነዋሪዎችን ገሏል። ጥቃቱ ከጎረቤት ሃገር ሶማሊያ ጭምር ቅጥረኛ ወታደሮችን ያሳተፈ ስለመሆኑ በተጨባጭ ሰነዶች ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን እስካሁንም እንደቀጠለ ነው። ስለሆነም ይሄንን በወያኔዎች መሪነት ከጎረቤት ሶማሊያ ጭምር በተውጣጡ ቅጥረኛ ነፍሰ-ገዳዮች የኦሮሞ ህዝብ ላይ በሶስት አቅጣጫዎች እየተካሄደ ያለውን ወረራ ለመቃወም በመላው ኦሮሚያ በመጭው ሃሙስ መስከረም 4, 2010 የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል። ሰላማዊ ሰልፉ የሚከተሉት ዓላማዎች ያለው ነው:-

1) በወያኔዎች መሪነትና ልዩ ፖሊስ በተባለው ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ ወታደሮች ኦሮሚያ ላይ እየተካሄደ ያለው ወረራና ግድያ በአስቸኳይ እንዲቆም ለማሳሰብ፤

2) ወያኔዎች ወንድማማች የሆኑትን የኦሮሞና የሶማሊ ህዝቦችን ለማጋጨት የሚያደርገውን እኩይ ተግባር ለመቃወምና የሁለቱ ህዝቦች ወንድማማችንነት እና አንድነት በዚህ ዓይነቱ እኩይ የወያኔዎች ተግባር ፈጽሞ ሊስተጋጋል እንደማይችል ግልጽ መልዕክት ለማስተላለፍ፤ ብሎም የኦሮሞ ህዝብ ለሶማሊ ህዝብ ያለውን ፍቅር፣ ወንድማማችነትና አጋርነት በዛውም ለማሳየት፤

3) ወያኔ ከኋላ ሆኖ ህዝብን ለማጋጨት ከሚያደርገው ከዚህ ዓይነቱ አደገኛ ድርጊት እንዲቆጠብ ለማስጠቀቅ ይሆናል።

ሰልፉ ፍጹም ሰላማዊ ይሆናል። ሰልፉን በሁሉም የኦሮሚያ አካባቢዎች ያሉ ቄሮዎች በግንባር ቀደምትነት የሚያስተባብሩት ሲሆን የየአካባቢዎቹ የሃገር ሽማግለውዎች ይመሩታል።
ስለሆነም በዚህ በመላው ኦሮሚያ ከላይ የተጠቀሱትን ሶስት ዓላማዎች አንግቦ ሊደረግ በታቀደው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በመጪው ሃሙስ ተሳትፎና ድጋፍ እንድታደርጉ ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች አስተባባሪዎቹ በታላቅ አቅብሮት ጥሪ አስተላልፈዋል።

Filed in: Amharic