>

በሕወሃት የፕሮፓጋንዳ ማሽን ....(ስዩም ተሾመ)

የዘር_አፓርታይድ እ.አ.አ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ከደ.አፍሪካ ሲነቀል በስደት ወደ ኢትዮጲያ መጣ፡፡ ስሙን ከዘር_ወደ_ብሔር ቀይሮ በሰላም መኖር ጀመረ፡፡ ቀስ እያለ በስደት በመጣበት ሀገር ስር ሰደደ፡፡ በመጀመሪያ ብሔርተኝነት የሚሉት ሽፋን አበጀ፡፡ ከዚያ ቀጥሎ የብሔር_አፓርታይድ ስርዓትን ዘረጋ፡፡

የአፓርታይድ ስርዓት በአለም የመጨረሻው መጥፎ ፖለቲካዊ ስርዓት ነው፡፡ አንዴ ከተተከለ በኋላ እሱን መንቀል እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም፣ በደልና ጭቆና የሚፈፅመው የራሱን ርዕዮተ-አለም ወይም መርህ ተከትሎ ሳይሆን ከህዝብ በስተጀርባ ተደብቆ ነው፡፡ የደ.አፍሪካው ነጭ_ሰፋሪዎችን  ሲጠቀም የኢትዮጲያው   ደግሞ የትግራይ_ህዝብን እየተጠቀመ ይገኛል፡፡

በመጀመሪያ “ሕወሃት ከሌለ የትግራይ ህዝብ የለም፣ የትግራይ ህዝብ ከሌለ ሕወሃት የለም” በሚል መፈክር የራሱን ህልውና ከህዝቡ ህልውና ጋር ፕሮፓጋንዳ አቆራኘ፡፡ ከዚያ በኋላ የደ.አፍሪካው አፓርታይድ ስርዓት በጥቁሮች ላይ ሲፈፅም የነበረውን በደልና ጭቆና በብዙሃኑ ኢትዮጲያዊን ላይ መፈፀም ጀመረ፡፡ የመብትና ነፃነት ጥያቄ የሚያነሱ ወገኖች በፓርቲ ወይም መንግስት ላይ ሳይሆን በህዝብ ላይ የተቃጣ ጥቃት እንደሆነ በመግለፅ ራሱን ከህዝቡ በስተጀርባ መደበቅ ጀመረ፡፡ በመንግስታዊ ስርዓቱ ላይ የሚነሳ አመፅና ተቃውሞ በፖለቲካዊ ስርዓቱ ላይ ሳይሆን በትግራይ ህዝብ ላይ እንደሆነ በመግለፅ የሚወክለውን ህዝብ በፍርሃት ማራድና ከሌላው የኢትዮጲያ ህዝብ ይነጥላል፡፡ ይህ ህዝብን ከህዝብ ያቃቅራል፣ ገዢው ቡድን ደግሞ የስልጣን ዘመኑን ያራዝማል፡፡

ይሄን ሁሉ የፃፍኩት ለምንድነው?  አዎ… #ቴዲ_አፍሮ እና #ኤደን ገ/ስላሴ ሁለቱም ኢትዮጲያዊ ሙዚቀኞች መሆናቸውን፣ ሄለን በ2008 ዓ.ም፥ ቴዲ ደግሞ በ2009 ዓ.ም የሙዚቃ አልበም ለማስመረቅ ጥረት ማድረጋቸውን፣ ቴዲ አፍሮ ትግራዋይ ባለመሆኑና ኤደን ደግሞ #ትግራዋት በመሆኗ እሷ አልበሟን በታላቅ ድምቀት ስታስመርቅ እሱ ግን መከራና ፍዳ እያየ መሆኑን… ይህ ደግሞ ሕወሃት/ኢህአዴግ በግልፅ አፓርታይድ ስለመሆኑ ማሳያ እንደሆነ ለመጠቆም ነው!

(ከዚህ ሁሉ በኋላ፣ “ይህ ፅሁፍ ለትግራይ ህዝብ ያለህን ጥላቻ ወይም ዘረኝነት ያሳያል” የሚለኝ ሰው ካለ፣ እሱ በተፈጥሮ የተሰጠውን አስተዋይ አዕምሮ #በሕወሃት_የፕሮፓጋንዳ_ማሽን የተተካለት ግዕዙ ፍጥረት ስለመሆኑ በራሱ ላይ እንደመሰከረ ይቆጠራል!! እኔም ሆንኩ ወዳጆቼ ለግዑዝ ፍጥረታት ቦታና ክብር የለንም!!)

Filed in: Amharic