>
12:09 pm - Monday April 19, 2021

ከካርታዉ በስተጀርባ ያሉ እንቅስቃሴዎች (ሚኪ ኣምሃራ)

ሰሜን ጎንደርን ከሶስት እከፍላለዉ ብሎ የሚንደፋደፈዉ ወያኔ ትናንት ህልሙን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አማካኝነት ነግሮናል፡፡ የአማራ ክልል ከሱዳን ጋር እንዳይገኛኝ አድርጎ እየሰራ መሆኑን ትናንት በብሄራዊ ቴሌቪዥን የቀረበዉ የኢትዮጵያ ካርታ ያሳያል፡፡ በተለየም ምእራብ ጎንደር ብሎ የመተማና ቋራ አካባቢን በመክፈል በሁመራ በኩል ከትግራይ ጋር በማገናኘት ትግራይን አስከቤንሻንጉል ክልል ድረስ ለማስፋት የታቀደ ነዉ፡፡ ጠለምት፤ደባርቅ አካባቢን ይዞ እንዲሁም ጠገዴን ሰሜን ጎንደር በማለት ወደ ትግራይ ለመጠቅለል ዝግጅቱን ጨርሷል፡፡
ካርታዉ ብቻ ሳይሆን ዞኑን ከሶስት በመሰነጣጠቅና ከትግራይ ጋር እንዴት መያያዝ እንዳለበት ህዝቡ ብዙም ሳያዉቅ ወያኔ የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራትን እየሰራ ይገኛል፡፡

1. የአስፓልት መንገድ ከመቀሌ ተነስቶ ራስ ደጀን ተራራ ድረስ እየሰራ መሆኑ፡፡ ከቅርብ ጊዜ በኋላ ራስ ደጀን ተራራ/ሰሜን ፓርክ ለመሄድ በመቀሌ በኩል እንደሚሆን፡፡ ከጎንደር/ደባርቅ በኩል ወደ ጃናሞራ፤በየዳና አጠቃላይ ወደ ፓርኩ የሚወስድ የረባ መንገድ የለዉም፡፡ ህወሃት ይሄን አካባቢ ለመጠቅለል እንዲያመቸዉ ከመቀሌ ሰሜን ፓርክ ደረጃዉን የጠበቀ መንገድ እየገነባ ይገኛል፡፡ ከአመታት በኋላ ወደፓርኩ ለመሄድ የሚፈልግ ሰዉ በመቀሌ በኩል ይሆናል ማለት ነዉ፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነዉ የሁመራ ሰሊጥ ባብዛኛዉ ወደ ጎንደር ይመጣ የነበረ መሆኑና እየቆዩ ግን ወደጎንደር ሙሉ ለሙሉ እንዲያቆም በማድረግ እንዲሁም ወደ ጎንደር ሲጭን የተገኘ ባለሃብት ተጨማሪ ታክስ እንዲከፍል በማደረግ ገቢያዉ ወደ መቀሌ እንዲዞር አድርገዋል፡፡

2. ምእራብ ጎንደር ብለዉ ሊወስዱት ያቀዱት የመተማና ታች አርማጭሆ ወረዳ አካባቢ ደግሞ የትግራይ ደረቅ ወደብ መተማ ላይ ለመገንባት ከ2500 በላይ አማራ ያለምንም ካሳ አፈናቅለዉ እያዘጋጁ ይገኛሉ (የትናንት የትግራይ ቴሌቪዥን ዜና ማየት ይቻላል)፡፡ ትግራይ ራሷን ስትችል በጅቡቲ በኩል መነገድ እንደማይችሉ ስላወቁት ሰሞኑን ወደ ሱዳን በመሄድ ከሱዳን መንግስት ለወደብ የሚሆን መሬት ቀይ ባህር አካባቢ ተሰቷቸዋል፡፡ስለዚህም ምእራብ ጎንደር ያሉት የመተማና ገንዳዉሃ አካባቢዎች ከትቂት ጊዚያት በሁዋላ የምእራብ ትግራይ ዞን አንድ አካል ናቸዉ፡፡ደረቅ ወደቡም ለትግራይ የወጪና የገቢ ንግድ ማከማቻና ማሳለጫ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡

3. የመተማና ምእራብ አርማጭሆ አካባቢዎችን አሁን ምእራብ ትግራይ ከሚባለዉ አካባቢ ጋር ለማገናኘት በህወሃት ወጪ ሱር በተባለዉ የህወሃት ድርጅት አማካኝነት በ1.5 ቢሊየን ብር በላይ ተበጅቶለት መንገድ እየሰራ ይገኛል፡፡ የመተማ አካባቢ ከሌላዉ አማራ አካባቢ ጋር የሚያገናኝ መንገድ ሳይኖረዉ ከምእራባዊ ትግራይ ጋር እንዲገናኝ የትግራይ ክልል በራሱ በጀት መንገድ እያሰራ ይገኛል፡፡መንገዱም ከመተማ ተነስቶ በአብራጅራ አድርጎ ሁመራ-ሽሬ መንገድ ጋር ይቀላቀላል፡፡

4. ለትግራይ አይሆንም የተባሉት አካባቢዎች አሁን የቅማንንት ልዩ ወረዳ አደርጋለዉ እያለዉ ያለዉን ላይ አርማጭሆንና ከፊል ጭልጋን ነዉ፡፡ እንዲሁም መሃል ጎንደር በማለት የሚሰይመዉ የጎንደር ከተማ አካባቢ ይዞ አስከ በለሳና ደንቢያ ያለዉ ብቻ የአማራ ሁኖ ይቀጥላል ማለት ነዉ፡፡

5. ሰሜን ፓርክ አካባቢ በቅርብ ለምርምር ስራ በሄድንበት አካባቢ የያዝነዉ የGPS መሳሪያ ከደባርቅ ከተማ ወደ ፓርኩ ታጥፈን 15 ደቂቃ ከነዳን በኋላ ገና የፓርኩ ጥግ ሳንደርስ የGPS መሳሪያችን አማራ የሚለዉ ጠፍቶ ትግራይ የሚል ጹሁፍ ያሳያል፡፡ይሄን ነገር ማንም ሰዉ ወደ ፓርኩ ሲሄድ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ በተለይ ከፈረንጆቹ ጋር ስትሄዱ እነሱ ይነግሯችዋል፡፡ ራሳቸዉ ትግራይ ገባን ይሏችዋል፡፡

6. ከደባርቅ ተነስቶ በፓርኩ በኩል አድርጎ ወደ በየዳና ሌሎች አካባቢዎች የሚዎስድ መንገድ ሊሰራ ሱር በተባለዉ የህወሃት ድርጅት ተጀምሮ የነበረ ሲሆን አሁን እሱ ተቋርጦ በመቀሌ በኩል እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

7. በደባርቅ፤ጃናሞራና፤በየዳ አካባቢ የሚኖሩ አማራወችን ለፓርኩ ደህንነት በሚል እያነሱ ወደ ማህል አማራ እያሰፈሩ ይገኛሉ፡፡ ይሄም ወደፊት ፓርኩና ተራራዉ ወደ ትግራይ ሲካለል አማራ የሚባል ኗሪ ባካባቢዉ አልነበረም ስለዚህም ለትግራይ ነዉ በማለት ነዉ፡፡

የሚቀጥለዉ ተግባራቸዉ የሚሆነዉ የተወሰኑ ትግሬወችን ከመሃል ትግራይ በማምጣት ፓርኩ አካባቢ ማስፈር ነዉ፡፡ ደባርቅና መተማ አካባቢ ማለት ሌላኛዉ የነገዉ ወልቃይት ነዉ፡፡
በቴሌቪዥን ትናነት ያየነዉ ካርታ ይሄን ያረጋግጣል፡፡ ከአመት በፊት ይቅርታ የተጠየቀበት ካርታ፡፡ በስህተት ነዉ ከዚህ በኋላ እንዲህ አይነት ካርታ አይኖርም በተባለ ማግስት ተለማመዱት ትግራይ ምእራብ ጎንደርን ጨምሮ እስከ ቤንሻንጉል ይደርሳል ተብለን ተነግሮናል፡፡እንግዲህ አይሆንም ያልነዉ ነገር ሁሉ በባለፉት 26 አመታት እየሆነ አይተነዋል፡፡ ተራዉ የመተማና የደባርቅ አማራ ነዉ፡፡ ነገ ትግሬነትን በጉልበት ለመጋት መዘጋጀት ወይም በአማራነት መሞት ብቻ ነዉ ያለዉ አማራጭ፡፡አማራነትህን ማትረፍ ካልቻልክ እንደ ኩርድ ህዝቦች በየአገሩ ተበታትነህ ስትንገላታና ስትሞት ያኔ ታዉቀዋለህ፡፡ ቀሪዉን የአማራ ክፍል ደግሞ ነገ የሆነ የብሄር ስም ይዞ ይመጣና አማራ አይደለህም ይልሃል፡፡ የበለሳ ብሄር ወይም የምስራቅ ጎጃም ብሄር የሚል ነገር በቅርብ መምጣቱ አይቀሬ ይመስላል፡፡የወልቃይት አማራ ትግሬ አንሆናለን ብሎ አስቦ አያዉቅም ነበር ግን በጉልበት ተጫነበት፡፡

ይመለከተኛል!!!
——————–
ጉዳዩ፦

ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት
ለብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ብአዴን)
ለአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት
እንዲሁም ጉዳየ ለሚመለከታችሁ ለአማራ ክልል ህዝቦችና ለመላው ኢትዮጵያውያን
ለ ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን(EBC)
እንደሚታወቀው፦
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከሱዳን ሀገር ጋር ይዋሰናል ይህን ደሞ ሀገር ያወቀው
ፅሀይ የሞቀው ጉዳይ ነው። በጣም አሳፋሪ የሆነ ነገርር ነሀሴ 18-12-2009 ሀሙስ እለት
በተላለፈው የኢቢሲ (ኢብኮ) (EBC) 7:00 ዜና ከ 7:14 እስከ 7:16 በጋዜጠኛ አበበ ባየ
በቀረበው ተጨማሪ ዜና ላይ የኢትዮጵያ ካርታ ላይ የአማራ ክልልን የማይወክል ካርታ
ታይቷል። የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና የቤንሻንጉል ጉምዝ ብሄራዊ ክልላዊ
መንግስት የአማራ ክልል ሉአላዊነትን በጣሰ መልኩ ተዋሳኝ ሆነዋል ይባስ ብሎ የአማራ
ክልል ከሱዳን ጋ ምንም አይነት ግንፕነት እንዳይኖረው ተደርጎ የተሰመረበት ካርታ ታይቷል።
ይህ በስህተት የቀረበ ሊሆን ይችላል ደሞም ስህተት ነው።
ስለሆነም ይህ ከላይ የሚታየው ካርታ ፍፁም ስህተትና የአማራ ክልልን ሉአላዊነት የጣሰ
በመሆኑ ተቃውሞየን አሰማለሁ ለጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ
ይፋዊ በሆነ ሁኔታ እንዲጣራና ይህን ካርታ እውቅና ሰጥቶ በሚዲያው ያስተላለፈው ኢቢሲ
(EBC) (ይህ ሚዲያ ካሁን በፊትም አሳይቶታል ከስህተቱም አልተማረም) ካርታውን
ያዘጋጁትየተጠቀሙት እውቅና የሰጡትና መሰል አካላት በሕግ እንዲጠየቁና ሕጋዊ እርምጃ
እንዲወሰድባቸው ምላሹም ባስቸኳይ እንዲነገረኝ ስል እጠይቃለሁ።
Inline image 1

Filed in: Amharic