>
5:19 am - Saturday January 16, 2021

ህውሃት እስካለ ድረስ የሙስና ድርና ማጉ ተስማምቶ ይኖራል

ቬሮኒካ መላኩ

የአባይ ፀሃዬ ሚስት የነበረችው ሳሌም ከበደ በሙስና ተያዘች ይባላል  እውነት ነው ብዬ   የሚከተለውን ልበል ።
እውነት ከሆነ አባይ ፀሃዬ ይኖር ዘንድ ሳሌም ከበደ የፖለቲካ ሞት መጋት አለባት ማለት ነው። ያውም አባይ ፀሃዬ ከሌላ ባል ቢነጥቃትም  ከሚስትነት ወደ   “ቀድሞ ሚስትነት ” Ex ” ከተለወጠች የቆየች ነች ተብሏል ። በህውሃት ቤት ሚስት መነጣጠቅና እንደ ሸሚዝ መቀያየር ባህል ስለሆነ ይሄኔ አባይ ከሌላኛዋ ሚስቱ ጋር ውስኪውን እየቀነደበ ሳቅ እያለ ዜናውን ይለበልብ ይሆናል። የመጀመሪያ ሚስቱ የነበረችውንና ሞንጆሪኖ እንደ አሮጌ ቁና ከወረወራት በኋላ ብዙ ሚስት ሳይቀያይር አይቀርም።

ይሄ የቶታሊቴሪያን የፖለቲካ ዘውግ ነው።
አባይ ፀሃዬ እንደ ጆሴፍ ስታሊን የቀድሞ ሚስቱን በድርድር መስዋእት አደረገ ማለት ነው ።
ጆሴፍ ስታሊን መጀመሪያ “አባቴ ! ጌታዬ ! ” እያለ ሲሽቆጠቆጥለት የነበረውን የሌኒን ሚስት  ገደለ ከዚያም የራሱንም ሚስት ገደለ። ግን ስታሊን በሙስና አልነበረም ።  ስታሊን የመግደል ሱስ ስለነበረበት እንጅ በሙስናና አገሩን በመከፋፈል አይታማም ።
የቶታሊቴሪያን ስርአት ድራማ የዚህ አይነት ነው። በዛ ላይ ፖለቲካ ” ክሩድ!” ነው።

abay-tsehaye-cartunእዚህ አገር ላይ የግርሃም ሀንኮክን አባባል ልዋስና “Lords of Poverty ” ከነገሰብን 25 አመታት እያለፈን ነው። እንኳን የሙስና ንጉሶች የሆኑት  አባይ ፀሃዬን ፣ ስብሃት ነጋ ፣አርከበ ፣ አዜብ፣ የመከላከያ ጄኔራሎችን  እና የመሳሰሉትን ሊነካ ቀርቶ አሁን እንኳን በቅርቡ 5 ቢሊዮን ብር ከልማት ባንክ ያጠፋው የህውሃቱ ኢሳያስ ባህረ ተዝናንቶ እየኖረ ነው።
ህውሃት በመንበሩ እስካለ ድረስ በድህነት እየገረጣና እያለቀ በሚሄድ አገር  የሙስና ድርና ማጉ ተስማምቶ ተረጋግቶ ይኖራል።

Filed in: Amharic