>

የማለዳ ወግ ... " አንተ መግባት አልተፈቀደልህም !" የቆንስሉ ምላሽ! [ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ]

* እናንተ ትክክለኛውን መረጃ ስጡና ከመረጃ ቅበላው ልታቀብ

Nebiyu Sirak (2006 -2007 )በማለዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ የተመራው የልዑካን ቡድን በጅዳ ቆንስል አንደሚመክር መረጃው ሌሊት ደርሶኝ ነበር ። ይህንኑ ለማረጋገጥና ዜጎች የሚያቀርቧቸውን ጥያቄዎች ለማቅረብ በጅዳ ቆንስል ተገኝቸ ነበር ፣ ነገር ግን እንዳልገባ ተክልክያለሁ ! በር ላይ ደርሸ ወደ አዳራሹ ለመግባት ፈቃድ ስጠይቅ በቀድሞው የህወሃት ታጋይ የጸጥታ ሰራተኛ ተጋይ ገሬ እያጉረጠረጡ ከቆንስሉ ሃላፊ ታግደሃል ካሉ በኋላ ደጋግሜ ለምን ስላቸው እንዲህ አሉኝ ” አንተ መግባት አልተደቀደልህም !” … አራት ነጥብ !

በስጨት ብየና አዝኘ ከመመለሴ በፊት ማን እገዳውን እንደጣለብኝ ለማጣራት ሞከርኩ ፣ አረጋገጥኩም ! … በአካል አልተገኘሁም ፣ ዳሩ ግን መረጃው ከቦታው እየደረሰኝ ነው ! ልዩነቱ ገብቸ መጠየቅ አለመቻሌ ብቻ ነው ፣ እገዳው ግን እንደ ዜጋ አያስከፋኝም 🙁 በስብሰባው ብዙ የሚጠይቁ ይኖራሉና ፣ ልቱነቱ መረጃውን አለቅረባቸው ነው ! አዝኘ ተመለስኩ ስል ያሳዘነኝ መረጃ የማግኘት መብቴ እንደ ዜጋ መገደቡ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዊነት ክብሬ በመገፈፉ አዝኛለሁ ! ያዘንኩት ከዋናው የቆንስል ኃላፊ ይልቅ የበታች ረድፍ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ሆነው በሚታዩበት ቤት በማንነቴ ላይ በጥላቻ ለመሳለቅ ” ተክልክለሃል ” በማለት አንገቴብ ሊያስደፉኝ መሞከራቸው ነው ! ይህ በፍጹም አይሆንም ፣ ስለ እወነት ቀና አድርጌ የምናገርበት አንገቴ በክፉዎች የማሸማቀቅ ድርጊት በጭራሽ አንገቴን አልደፋም ! የማይፈልጉኝን ለክልታማው ስደተኛ ስትሉ ይልቅስ ስለ እውነት ኑሩ እላቸዋለሁ !

በተረፈ የእኔ መረጃ ከእናንተ መረጃ እውነት ነው ይሻላል ፣ የእናንተ ውሸት ነው ፣ አይሻልም እያልኩ አይደለም … ትክክለኛውን መረጃ ካደረሳችሁት ደስተኛ ነኝ ፣ እኔም የተደበቀውን ፣ የተሸፈነውን ከማውጣቱ አድካሚ ስራ ትታደጉኛላችሁ ! ገጼም ከመረጃ አቅርቦቱ ያርፋል ፣ በልጆቸና በቤተሰቤ ፎቶ እያፈራረቅኩ ያሻኝን መረጃ አቀርብበታለሁ ! ስለእኔ አታስቡ ስለተቸገረው መብት ከቆማችሁ መብት አክብሩ ብየ አልጨቃጨቃችሁም ! እናም ለቀቅ ላድርጋችሁ ትክክለኛውን መረጃ ለስደተኛው አሳውቁት ! … እኔ ቤተሰብ አስተዳዳሪ ነኝ ፣ ስራ አለብኝ … እናንተ ትክክለኛውን መረጃ ስጡና ከመረጃ ቅበላው ልታቀብ ፣ ይህን ነው የምለው …

አበቃሁ !

ነቢዩ ሲራክ
ግንቦት 18 ቀን 2009 ዓም

Filed in: Amharic