>

የጨንቻ ዝግባ ስንብት [ታሪኩ ደሳለኝ]

ማርከሻው ጥበሉ!
እንደጠፋ ቀረ …? እንደተሰወረ??!

assefa-chabo-canada1ጋሽ አሰፋ ጫቦ በትዝታው ፈለግ መፅሀፋችው ይህን ሲሉን ምናልባት እንዲህ እያሉን ይሆናል አላለሁ ፣

ኢትዮጲያዬ ናፍቆትሽ ዳርቻ አልባ ነው፣ናፍቆትሽ ምህረት የለውም ፣ካንቺ ስርቅ አይደለም ኢትዮጲያነትሽን የተረዳሁት፣ ካንቺ ስርቅም አልነበረም ናፍቆትሽ ያመመኝ ፣የናቺ ናፍቆት ባወቅሁሽ ቁጥር በገባሽኝ ልክ በቀረበኩሽ መጠንም አየርሽ እየሸተተኝ፣ አፈርሽ እያወደኝ፣ህብርሽ እያጓጓኝ እግርሽ ሰር ሆኜ ነው። ኢትዮጲያዬ ናፍቆትሽ ያሳወረኝ።

አሁን አሁንማ ኢትዮጲያዬ እንዲህ እርቄ ውሃና ተራራ መሀላችን ገብቶ፣ አድማስሽን ጋርዶኝ ፣ሳላይሽ፣ ሳልነካሽ፣ በእለት በእለት ሳይሆን የሰከንድ ግማሽ ሳይሞላ፣ አይኔ በአንቺ ይከለላል።ኢትዮጲያዬ ትናፍቂኛለሽ።ድክ ድክ ያልኩት ጨንቻ፣ የኔ የጨረቃ ጉዞ፣ የኔ ለንፋስ የማይታዘዝ ደመና፣የኔ ነጭ ሰማይ፣ ከኢተየጲያዬ ስር ይታየኛል። ከጨነቻ ጀምሬ መሬትሽን አካልያለሁ፣ ባስተማርሽኝ ልክ አገልግዬሻለሁ፣አጉድዬብሽ እንጂ አጉድለሽብኝ አታውቂም። ኢትዮጲያዬ ሃያ ምናምን አመቴ ሰዎችሽ ጀርባሽን ሰጡኝ፣በቤቴ በቤታችን ደጅሽን መለስ አረጉብኝ፣ይኸው ይህን ሁሉ ግዜ እንደራብሽኝ ከናፍቆትሽ ማማ ቆሜ አንቺን አስባለሁ። ኢትዮጵያዬ ያቆየኝ ያኖረኝ ናፍቆትሽ ነው። ናፍቆትሽ ሲያገረሽብኝ፣በእርጅናዬ ሳላይሽ፣ በሽምግልናዬ ሳላዳኝሽ፣ዳርና እና ዳር እንድቆምኩ እንደምቀር ሲሰማኝ ሆዴ ይባባል። ህግሽን ተምሬለሁ።ህግሽ ከፍቅርሽ በታች እንደሆነ ተረድቻለሁ።ለዚህ ነው ለፍቅርሽ ይግባኝ የሌለው።

ኢትዮጵያዬ “ለጋራ ቤታችን” ስል ስላንቺ ከፍ ዝቅ ተደርጌለሁ።ስላንቺ የመሰለኝን ከትቤያለሁ።ከጋሞ እስከ አሜሪካ ባንቺ ጉዳይ ተሳቅያለሁ። ኢትዮጵያዬ ባንቺ የመጡብኝን ሁሉንም በሃሳብ ሞግቻለሁ። ያንቺ ክብር እንዳይጓደል እኔ እስክጓደል ስላንቺ የማውቀውን ሁሉ ከትቤለሁ። አድሜዬ ያሳየኝን “ለጋራ ቤታችን” የሚሆነው ሁሉ እንዲሆን ስጥር ወዳጅ ዘመድ ቢከፋ ካንቺ ስለማይበልጡ አላስበለጥኳቸውም። ለዚህም መሰለኝ “ከሀገሬ ከወጣሁ 25 አመት አለፈ፣11 የአሜሪካ ግዛቶች ኖሬለሁ ያልኖርኩባቸውን ወይ ነድቼ ወይም ከአየር አይቻለሁ።ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ህልም ባየሁ ቁጥር ሰመመን ውስጥ በገባሁ ቁጥር የኢትዮጵያ መሬት የኢትዬጲያዊያን ፊት ብቻ ነው የሚታየኝ” ።

በእውኑም በህልሙም ሀገሩ በቻ የታየችው ጋሽ አሰፋ ጫቦ የሀገሩን ናፍቆት ሳይወጣ ሳይወጣ ከሀገሩ በግሩ እንደወጣ ዛሬ በሳጥን መጥቶል። እንግዲህ አገሬ ሀዘንሽን ቻዬው።

ጋሽ አሰፋ ጫቦ ጨንቻ አመት ሙሉ ይዘባል እዛ ደመና ነው እንዳሉት ይህው በዝናብ እየቀበርናቸው ነው።

እባካቹሁ ዘመዶቼ በሳቅ ጉዞ ፍታት ፍቱኝ
በሙሾ ዋይታ አታጅሉኝ
እናቴም ፌትሽ አይከስል
በዕልልታ በብርሃን ይንበልበል።
በእረፍቴ እንዳታፌዥብኝ
በሠርጌ እንዳታለቅሽብኝ።
ገጽሽ በጭንቅ አይወረስ
ልብሽ በኀዘን አይለበስ
በሆድሽ ሞት አይፀነስ
ዕንባ ባይንሽ አይቋጠር
የሞት ቅስሙ እንዲሰበር።
አዎን አደራ አደራችሁ የሙት ውሌን ተቀበሉኝ
ደስታዬን ተካፈሉኝ
ለንሰሃ ሞት አደለም ለፍሥሐ እረፍት አብቁኝ
በዶርዜ እስክስታ አስቀብሩኝ
በዕልልታው ጎዙ አሳጅቡኝ
በጦሩ ችቦ አሳጥሩኝ
ጭብጨባችሁ በስልቱ ይውረድ
ዛፍ ቅጠሉም አብሮ እስኪረግድ
ሀገር ምድሩ ያቅራራ
ሀሴት ነው ይበል ጀቢራ
ሠርጌ ነው የምታ ደንኪራ።

ባለቅኔ ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድን

ሚያዚያ 27/09ዓም
ቅድስት ስላሴ ካቴድራል

Filed in: Amharic