>

አሰፋ ጫቦን ብርብር ማሪያም አሳርፉት !!!

assefa-chabo-canada1ዲልባቶ ደጎዬ ዋቆ

” ሁላችንም ተፈጥሮ ያዘጋጀልን ባቡር ተሳፋሪዎች ነን። መውረጃ ጣቢያችንን ነው የማናውቀው። በስደት ባይሆን ጥሩ ነበር ። ” ይሄን ያለው አሰፋ ጫቦ ነው ።

ለአመታት ደቡብ እና ኦሮሚያ አካባቢ ነግሶ የነበረውን የውሸት የታሪክ ክምር በብእር ደማሚት የደረመሰ እና የገለበጠ እንደ አሰፋ ጫቦ ማን አለ? ማንም ። አሴ ብእሩን አነጣጥሮ ብቅ ሲል የታሪክ ደላሎች ጥይት እንደሳተው ድኩላ በድንጋጤ ጆሯቸው ይቆም ነበር ።

ከደቡብ ኢትዮጵያ ከወጡ ልሂቃን አሰፋ ጫቦን የሚስተካከል የለም ።

ወደ ኋላ ሄጄ ማነፃፀር ካለብኝ ጋሼ አሰፋን ማወዳደር የምፈልገው ከእሱ ቀድሞ 500 አመታት በፊት ከኖረው የአገሩ ሰው የጋሞው የጨንቻው የብርብር ማሪያሙ ባለምጡቅ አእምሮ ምሁር ከአባ ባህሬይ ጋር ነው። የአባ ባህሬም ብእርም እንደ ማር እሸት ትኩስ ወተት አይጠገብም ። ዛሬ የአባ ባህሬን ስም ሳይጠቅስ የ16ኛው ክፍለ ዘመንን ታሪክ የሚፅፍ ምሁር በአለም ላይ አይገኝም ።

ታላቁ አባ ባህሬይ የቀመሳትን የብርብር ማሪያም ቅዱስ አፈር አሰፋም ይጋራው ።

Filed in: Amharic