>
4:18 pm - Sunday April 15, 6035

የእኛ ፖለቲካ [ምንሊክ ሳልሳዊ]

በወያኔ ላይ የምናሰማው ጩኸትና ተቃውሞ እየተላተመ በመመለስ ዲያስፖራውን ፖለቲከኛ ነኝ ባይ ለፖለቲካ እብደት ከመዳረጉም በላይ ወያኔ በቀደደው የጎሳ ፖለቲካ ቦይ እንዲፈስ አድርጎታል።

Image may contain: text
#Ethiopia ምስጋናዬ የላቀ ነው።በማህበራዊ ድረገጽ የሚደረገውን ተራና የወረደ ክርክር የስም ማጥፋትና አስጠሊታ የፖለቲካ እብደትን ላለማየት ፕሮፋይሌን የመዝጋት እቅዴን ተከትላቹ በኢንቦክስ በኢሜይል በስልክና በስካይፒ ጥያቄና ምክር ያጎረፋ ወዳጆቼ እያመሰገንኩ ተዘግቷል ሲባል አረፍት ላይ መሆንን እንጂ ከሃገር ጉዳይ ራስን ማግለልን ኣይገልጽም።መልእክታቹ ብርታት ሆኖኛል።ራስን ማግለል ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን ብስለት ነው።ድሮም ገለልተኛ ነኝ በነፈሰበት እየነፈስኩ አላቦካም ሲለኝ ወደ አንዱ ሳይለኝ ወደ ሌላው እላሽካልልም።ኣቋሜ ኣንድ ነው አምባገነንነትን ማስወገድ ፤ይህንንም ላለፉት የማህበራዊ ድረገጽ ቆይታዬ ሳልደፈርስ አረጋግጫለሁ አስር አመት ካለእረፍት ቆይቻለሁ አሁን ግን የማይረቡ አጀንዳዎችን ከማየት ይልቅ ማረፉ ይመረጣል።በማህበራዊ ድረገጽ ጥቂት ኢትዮጵያውያን ከነበሩበትና ፖለቲካ መጻፍ እንደ ብርቅ ከሚታይበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት አስር አመታት በተለያየ መልኩ በማህበራዊ ድረገጽ በኢትዮጵያ የተንሰራፋው አገዛዝ ለመታገል በሳይበር አርበኝነት በጋራ ያሳለፍነው ጊዜ እጅግ መልካምና የተሳካ ነበር። የተሳኩ የፖለቲካ ድሎችን ከማግኘት አልፎ ሃገር ወዳድ የሆኑ አክቲቭስቶችን ማፍራት ተችሏል።በፓርቲ አፍቃሪ ቀፋይ ሰዎች ታጥረንም ቢሆን ለወያኔ ኃይሎች ክፍተት ሳንሰጥ ዘልቀን ተጉዘን ነበር።ዛሬ ላይ ባልበሰሉ ሰዎች ኣካሔድ ደፈረሰ።

ወያኔም ይሁን የለውጥ ሃይሉ ወደ ማህበራዊ ድረገጽ መጉረፍ የጀመረው ከ2010 በኋላ ነው። የተረጋጉና ከፍተኛ እውቀታቸውን ሲያፈሱ የነበሩ የማህበራዊ ድረገጽ ወዳጆቻችን ባሁን ወቅት የሉም። በሩቅ ሆነው እየታዘቡ ነው።በወያኔ ላይ የማናሰማው ጩኸትና ተቃውሞ እየተላተመ በመመለስ ዲያስፖራውን ፖለቲከኛ ነኝ ባይ ለፖለቲካ እብደት ከመዳረጉም በላይ ወያኔ በቀደደው የጎሳ ፖለቲካ ቦይ እንዲፈስ አድርጎታል።ይህንንም በተግባር እያየነው ነው። ለዚች ሃገር ችግር ተጠያቂው ወያኔ ብቻ ሳይሆን ከወያኔ ጋር በኣንድ ትቦ የሚፈሰ በፖለቲካ እብደት የናወዘው ዲያስፖራውም መሆኑ የግድ ሊታወቅ ይገባል።ከኛ በላይ አዋቂ የለም እኛን ብቻ ስሙ የሚሉ በተለይ በአሜሪካ የተወተፉ ድፍንና ጭፍን ዲያስፖራዎች በሚሰሩት ሕገወጥ ጥርጊያ የወያኔን እድሜ እያስረዘሙት ይገኛሉ። በማህበራዊ ድረገጽ የበሰሉ ምሁራን ማግኘት ዘበት ሆኗል። አሉ የሚባሉትም ምሁራንም ያልበሰሉ ጋጥወጦችን በመደገፍ በስድብ ፖለቲካ ላይ ተሰማርተዋል።

ትግሉ በስም አጥፊዎች በኣሉባልተኞች በውሸታሞች በቀፋዮች በሓሜተኞች ወዘተ ተወሯል።ይህንን ማጽዳት ደግሞ ወያኔን ከመታገል የማይተናነስ ጊዜ ይወስዳል። ለማጽዳትም አስቸጋሪ ሲሆን ይህን ወረራ ተጠቅሞ ወያኔ ራሱ ከባድ የሆነ የቤት ስራ ለለውጥ ሃይሉ በማሸከም የማህበራዊ ድረገጽ አብላጫ ድምጹን ተቆጣጥሮታል።በተለያየ ጊዜ እርምጃ እንዲወሰድበት በመምከራችን ተሰድበናል ተዋርደናል።የተያዘው መስመር ያሳዝናል ያሳፍራል ከዚህና በስፋት ከሚታዩት ከማይረቡ አጀንዳዎችና መንገዶች በመነሳት ለጊዜው ክማህብራዊ ድረገጽ አረፍት ላይ መሆን አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።አረፍት ላይ መሆን ተስፋ መቁረጥ አይደለም።እንግዲህ በቀጣይነትም አለሁ።#MinilikSalsawi

Filed in: Amharic