>
5:13 pm - Monday April 18, 5403

ከሳምንቱ ቅሌቶች በጭልፋ [አሰፋ ጫቦ]

Ato Assefa Chabo1. Amazon ላይ ይህንን አዲሱን ቫፖር የሚሉትን ሲጋራማጨሻ በ$4.99 ለመላኪያ የሚሆን ክፍልን ውስድ የሚል አነበብኩን እንደተባለው አዘዝኩ።ለማዘዝዘ ሁሌ እንደሚደርገው የክርዲትካርድ(Credit Card) ቁጥር ሰጠሁ። ከሁለት ቀን በኋላ ለመላኪያ 2.99 እንደገና እንጨምራለን አሉ። ገርሞኝ ለሁለት ብር አልሟገትም ብዬ አለፍኩት።
ትላንትና ከባንኬ email አገኘሁ። “አንድ Ecigarር የሚባል ከሒሳብህ ላይ$99.99 ቆርጧልና ታውቀዋለህ ወይ?” የሚል። “አውቀዋለሁ ግን የህንን ገንዘብ ውስድ አላልኩትም” ስል “እኛም ጠርጥረን ክፍያውን አግደናል!” አሉ።ያ ሳይያነስ ዛሬ ገና በቅጡ ሳይነጋ ስልክ ተደውሎ ከ Fraud Investigation Department ነን አለኝ። Fraudትርጉሙ አጭበርባሪ ን፤ አውናባጅና ሌላም ሌላም ማለት ይሆን?” ምነው?” ስላት ሰሞኖኑን የተገበያየኸውን እስቲ አብረን እንደናይ ነው” ብላ የአንድ ሳምንቱን ግብየቴን ቆጠረችልኝና “ይህ ሁሉ ያንተ ነው ወይ?” ስትለኝ ፤ የEcigareሩ ልክ አለመሆኑን ነግሬ “እኛም አውቀናል ጎድጓድ ምሰናል!” ብላ ገንዘቤ እንዳልተነካ ነገረችኝ
ከተጀመረ አይቅር ብዬ ዛሬ ባንኩ ሔጄ ያንን ሁለት$ ከምናምኑንም አሰረዝኩ። “አንዴ ቁጥርህን ስለሚያቁ ሊጠቀሙበት ይችላሉና አዲስ ካርድ ይሻላሐል!’ ብላኝ ነባሩን በመቀስ ቆራርጣ ጣለችው። በቋፍ እንድንሔድ እያደርርጉን እኮ ነው!!

2. ሌላው ቅለቴ የዚህ የጋምቢያ ፕሬዝዳንት ጉዳይ ነው። ቢሊዮን አመት እነግሳለሁ ብሎም ነበር አሉ። ብቻ ቢሊዮኑ ሲመነዘር ወደ 20 ምናምን አመት ሆነ። ምርጫ ተደርገና መሸነፌን ተቀብያለህ አለ።በማግስቱ አልተቀበልኩምና እንደገና ይቆጠርልኝ አለ። በዚያ ማግስት ይሁን እንዲያ ፓርላማ የሚለውን ጠርና “ነገሩ እስኪታጣራ 3 ወር ተጨማሪ ጊዜ ስጥተነዋል!” አለ ፣ፓርላማው።
ነገሩ እንዲህ ሲጠነዛ የምእራብ አፍርቃ ትብብር የሚባለው “ወይ ወርድ ወይ ወዮልህ!” አለና ወታደር ላከበት።እወርዳለሁ ግን ቀን ስጡኝ ብሎ ሶስት ቀን አገኝቶ አሁን ተሳፍሮ አገር ለቆ ወጣ። ሶስቱን ተጨማሪ ቀን የፈለገው ወርቅ ፤ዶላላርና ሌላም ያከማቸውን ከየተደበቀበት አውጥቶ ለመጫን ነበር።
“አፍሪቃዊ መሆኔያሳፍረኛል!”ለማለት ትንሽ ዳድቶኝ ነበር። ከዚያ ኢትዮጵያዊ መሆኔ፤ ኢትዮጵያም ዲሞክራሲያው ረፑብሊክ መሆንዋ ትዝ አለኝ። “ምነው የዚህ እንደምእራብ አፍርቃው በምስርቃ አፍሪቃም ባለጠመንጃ ትብብር ቢኖር?” አሰኘኝ።

3. ሌላው የዶናልድ ትራምፕ ቅለቴ ነበር። ሰውዬው ቅሌታም መሆኑን አንድም ቀን ክዶና አስተባብሎ አያውቅም። ባይሆን በላይ በላዩ ይጨምርበታል እንጅ። የትራምፕ ቃለ አቀባይ በመጀመሪያ በሰጠው ጋዜጣታው መግለጫ የትራምፕን መመረቅ ለማየት የወጣው ሕዝብ ብዛት እስከዛሬ ተሰምቶም ታይቶም አያቅም አለ። ጋዜጦችና መገናኛ ዜደዎች ሁሉ የሕዝቡን ብዛት ከኦቦማ ጋር በማነጣጠተር በምስል የተደገፍ አውጥተውት የነበረውን አውገዘ። ውሸት ነው አለ።
በነጋታው የትራምፕ አዲስ ሹም የሆነች ሴት አንድ ጋዜጠኛ ተለቪዥን ላይ አፈጠጣት። “ይህንን በማስረጃ የተደገፈ እውነት ት እንዴት ትክዳላችህ?” ሲላት “እናንነት የምታዩት እውነትና እኛ የምናየው እውነት ይለያያል!” አለኝ። ሲተትረጎም እውነት የሚባል ነገር የለምና እንደተርጓሚው ነው ማለትዋ ነው መሰለኝ።
ሌላው በምስል የተደገፈ ቅሌቴ የትራፕምና የሚስቱ ሊረከቡ ሲመጡ፤አቦማና ሚሼል ደረጃ ላይ ሆነው ሲጠብቋቸው የሆነው ነው። ትራምፕ ከመኪና ይወርድና ሚስቱን ዞር ብሎ እንኳን ሳያያት ደርጃውን ይወጣታል። ቆይታ ተከትላው ትወጣለች።ያኔም አልተቀበላትም። ከዚያ ለሚሼል ያመጣችውን ስጦታ ስተሰጥ አቦማ ይረዳታል።ሰውየው የሚዘረጠጥው ሴት በጠቅላላው ብቻ ሳይሆን የገዛ ሚስቱንም የሚየከብር አይመስልም።
ከዚያ ትራምፕና ባለቤቱ ግብዣ ላይ ሲደንሱ የሚያሳይ ፊልም አየሁ። ተዋደው ተጋብተው ሳይሆን ፖሊስ አዘገድዷቸው የመጡ የሚመስል ነገር አለው።
ከቤትም ከአደባባይም ቅሌትና አወናብጅ ይሠውረን

Filed in: Amharic