>

ለመላው ኢትዮጵያዉያን: ጉዳዩ ስለ ሃብታሙ አያሌው ሕክምና

Habtamu Ayalew Medical Fundበወገኖቹ ላይ የሚደርሰውን ግፍና ኢፍትሃዊነት እያየ ዝም ማለት ሳላልቻለ ፣ መታሰር፣ መገደል፣ እንግልትና መከራ እንደሚያጋጥመው ቢያወቅም፣ ለአገርና ለሕዝብ መቆሙን መረጠ። በአደባባይ የአገዛዙን ግፍ ማጋለጥ ጀመረ። የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ እና የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቀ ሰብሳቢ ሆኖ በአገሪቷ በሙሉ ኢትዮጵያዉያንን ማደራጀት ጀመረ። ጠንካራና አልበገር መሪ መሆኑን ሲያውቁ ወደ ወህኒ ወሰዱት። ከፍተኛ ቶርቸር አደረጉበት። ጤነኛ ሆኖ እሥር  ቤት ገብቶ በሽተኛ ሆኖ ወጣ።  ሃብታሙ አያሌው፣ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው የዘመኑ አንጋፋ የሰብአአዊ መብት ተሟጋቾችና ፖለቲከኞች አንዱ።

“በሃብታሙ ላይ የደረሰው ስቃይ የኛም ስቃይ ነው” በሚል፣  ለሕክምና ይሆነው ዘንድ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ከጎኑ ቆሙ። ወደ ዉጭ ሄዶ እንዳይታከም ግን እገዳ ተደረገበት። እነርሱና ልጆቻቸው ጉንፋን ሲይዛቸው ወደ ዉጭ ሄደው እየተካሙ ሃብታሙ ራሱን ስቶ፣ ሐኪሞች “እኛ ምንም ማድረግ አንችልም፤ ዉጭ ሄዶ ይታከም”  ብለው ቢያስጠነቅቁም፣  ጭካኔ ባህሪያቸው ነዉና፣ ወጥቶ እንዳይታከም ጨከኑ።

ሆኖም ኢትዮጵያዊያን ካደረጉት የገንዘብ ድጋፍ የተነሳ፣  ምንም እንኳን መሳሪያው ስለሌላቸው አገር ቤት ያሉ ሐኪሞች ሊያድኑት ባይችሉም፣ በተለያዩ  ጊዜያት በድንገትኛ ሆስፒታል ሲገባ ከፍተኛ እርዳታ  እያደረጉለት፣  በቀጣይነት ለወራት የዘለቀ ክትትላቸው ሳይለየው ፣ ፣የሕመም ማስታገሻ ከባባድ መድሃኒቶች እየወሰደ፣  በስቃይም ሆኖ ሕይወቱ ተጠብቃ ቆየች።

በፈጣሪ ቸርነት ፣ የቀረበበት የሽብርተኝነት ክስ ውድቅ ስለተደረገ፣  ዉጭ የመዉጣት እግዱ ተነሳ። ለሕክምና አሜሪካ መጣ። ላለፉት በርካታ ወራት የደረሰበት ስቃይ ልብን የሚሰበር ቢሆንም፣ ወንድማችን ሕይወቱ ተርፋ ጥሩ ሕክምና ለማግኘት አሜሪካ መምጣቱ ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያን ሁሉ አስደሳች ዜና ነው።

ሃብታሙ በአሜሪካ ቆይታው የሕክምናውን ጨመሮ ሌሎች ወጭዎች ስለሚኖሩት፣ አሁንም ኢትዮጵያዉያን በያለንበት ከጎኑ እንቆም በአክብሮት እንጠይቃለን።
እነርሱ አላማቸው ሌላ ነበር። ግን እግዚአብሄር ቀደማቸው። እነርሱ ከጨዋታ ዉጭ ሊያደርጉትና ቅስሙን ሊሰብሩ ሊገድሉት ነበር አላማቸው። አልተሳካላቸዉም። ወንድማችን ሕይወቱ ተርፎልናል። ሙሉ ለሙሉ ደግሞ ድኖ፣ በጎንደር፣ በደሴ፣ በባህር ዳርና በተለያዩ ከተሞች በሺሆች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉይን ፊት፣ በወኔና በጀግንነት፣ የዴሞክራሲን፣ የፍትህና የኢትዮጵያዊነትን ድምጽ ሲያሰማ የነበረበት ጊዜ የነበረዉን ጤና አግኘቶ በቅርብ እናየዋለን።

ሃብታሙን  ለመደገፍ በሚከተለውን በራሱ ስም የተከፈተ አካዉንት  በመጠቀም በቀጥታ መደገፍ የምንችል ሲሆን፣ ለዚሁ አላማም የተዘጋጀ የ ጎ ፈንድ ሚ  ድህረ ገጽ ( gofundme) ተዘጋጅቷል።

https://www.gofundme.com/habtamu-ayalews-medical-fund

If you choose to direct deposit to Habitamu Ayalew’s  checking account , please use the Bank Account Information belowHabtamu Ayalew Teshome

Bank of America
Account #   2260 0057 6350
ACH Routing# 054001204

If you need help, please call 503- 449 7777

With Appreciation Gratitude and Love,

ስለሁሉ የከበረ ምስጋናችን ይቀድማል !!

ጒደኞቹ

https://www.gofundme.com/habtamu-ayalews-medical-fund

Filed in: Amharic