>

ትንሽ ገለጥለጥ [አሰፋ ጫቦ Dallas Texas USA]

Page 1 of 7
እንደመግቢያ
Ato Assefa Chaboይህ የማሕበራዊ ገጾች(Social Media)፣ በተለየም Facebook፣ የአንድ ስሞን ውሎ የቀነጫጨብኩት ነው። እስቲ እንየው! እስቲ እንታዘበው! ለማለት ያክል:
በዚህ ጉዳይ ላይ እጽፍበታለህ የሚል ሀሳብ የነበረኝ አይመስለኝም። ሆኖም በማሕበራዊ ገጾች አንዳንዶች ተንኮስ ሲደርጉኝ “ልበለው አልበለው !”የሚል ነገር ይመጣብኝ ነበር። ፈረንጅ Thinking Out Loud የሚለው ሳይሆን አይቀርም ። የThinking Out Loud ትርጉሙ ይኸውና:-
‘Thinking out Loud’. means that someone is verbalizing an internal monolog (or dialogue); thinking about something and, possibly inadvertently, saying it out loud. The phrase is mostly used when someone else hears it and thinks the person is talking to him or her. … I was just thinking out loud.”

ማብሰልሰ ል ልንለው እንችላለን?

መነሻው

ለዚህ መነሻ የሆነኝ ሌንጮ ባቲ Facebook ላይ ስለወንድሙ የሰጠው አስተያየት ነበር።”ወንድሙ፤የኦሮሞ ባንዲራ ካልተውለበለበ በስተቀር ከትምህርት ቤቱ አልመርቅ ብሎ ባንዲራውተሰፋለትና በዚያ ባንዲራ ጥላ ተመረቀ” የሚል ነው። የጻፈውን እዚህ እንዳለ ይኸውና ለጥፌዋለሁ። Lencho Bati · January 8 at 1:16am · Ambo Bati who was five times all American cross country champion refused to graduate unless the Oromo flag is
Page 2 of 7
lined with the flag of nations of the graduates. The college looked for all the companies around the world who produce world flags. Could not find it and order it. Spencer, who is Ambo’s track mates and a close friend, and now a Medical Doctor asked his mother to saw an Oromo flag from a picture presented to her over night. She put the pieces together and Ambo’s wish was fulfilled at Augustana College in Illinois on graduation day. It was 1996.
እስከሚገባኝ ድረስ ሌንጮ ባቲ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ድርጅት አባል፤መሪ( እርግጠኛ አይደለሁም) ነው/ነበረ።ከሁለት አመት በፊት ይሁን እንዲያ በMessenger ይመስለኛል ሰላምታና ምልእክት ልኮልኝ መልስ ሰጠሁት። ከዚያ በኋላ አልተመለሰም። መልሴን የወደደው አልመስለኝም።ስለ ኦነግ የማውቀውን ነግሬው “ብቻ በጣም በጥንቃቄ ብታየው ጥሩ ነው!” የሚል ምክር ነበር። ስለኦነግ ማወቅ ብቻ ሳይሆን ለአስር አመት ተኩል መታሰሬ ዋናው ምክንያት ኦነግና የኦሮሞ ጉዳይ ስለነበር ምክር መሰጠቴ ከዚህ ተመክሮ የሚመጣ ነበር። ከኔ በላይ ስለኦነግ በገለልተትኝነት ማውቅ “ላሳር ነው!” የሚባለው አይነት መሆኑ ነበር።አሳሩን ቀምሻለሁና!!

ይህ የኦሮሞ ባንዲራ ካለተውለበለበልኝ አልመረቅም ብሏል የተባለው የሌንጮ ባቲ ወንድም፤አምቦ ባቲ፣ ነገር ገርሞኝ እዚያው Facebook ላይ” ነገሩ ለካ እዚህም ደርሷል እንዴ!” በሚል ትንሽ አስተያየት ሰጠሁ። ይህ ዛሬ በሐይማኖትም ሆነ በሀገር፤በብሔረሰብ ሽፋን በመላው ዓለም የተፈለፈሉትን ጽንፈኞች፤በተለይም ፈንጅ ታጠቀው ራሳቸውንም ሌላውንም የሚያጠፉትን ወጣቶች አስታውሶኝ መሆን አለበት። ፖለቲካ ማለት “የመቻቻል ጥበብ ነው” The Art of Compromise የሚባለው ቀርቶ የመጥፊያ፤የማጥፊያና የመጠፋፊያ መሳሪያ መሆኑ እያሳዘነኝም እየደነቀኝም “ለመሆኑ እንዴትእዚህ ደርስን!?” ከሚልም ነበር።

ከዚያ ወረዱብኝ! ተራ ዘለፋና ስድብ ነው። እኔ ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ሰው የሆነ ሰው ሁሉ ጸያፍ ቃል ሲሰንዘር የሰቀጥጠኛል።እዚህ አሜሪካኖቹን እንኳን ስንት ጊዜ Mind Your Language እላለሁ። “ቃላቶችን ልብ በላቸው !”ለማለት ነው። እኛ ቤት እንኳን ጸያፍ ቃል ከአፋችን ሊወጣ ባለጌ ናቸው ከሚባሉ ልጆች ጋር ከታየን እንወገራታለን። ከማቱኬ አጆ ጋር ቀልድ የለም። “አሳዳጊ የበደለው ታሰኙኛላችህ!” ነው ዋናው መልእክትዋ።ይህንኑ ይኸው ከልጆችዋ ለልጅ ልጆችዋ አድርሰናል። ታዲያ ይህንን መሕበራዊ ገጽ ላይ የማየውን ጸያፍ ቃላት ስታዘብ ያ “አሳዳጊ የበደለው!”ዛሬ ጥዋት የተባለ መስሎ ብልጭ ይልብኛል።ይልልኛል!

ቢቸግረው መሰለኝ ወዳጄ፤አቶ ፈቃደ ሸዋቀና መልስ ሰጠ ።ያ መልስም ይኸው:- Fekade Shewakena Why do we employ so much vitriol even if the issue may be contentious and emotional. It doesn’t help anybody. Let’s read what Ato Assefa Chabo is going to write. We will all read and judge his views and write back to him if we don’t agree with him. Some of you like Macaaf Tuulema and Tolessa Gosomssa above should be ashamed of yourselves for the kind of language you use in

Page 3 of 7
this discussion. Even the most sacred of your beliefs can be questioned. You may have to respond calmly so that the rest of us who have no knowledge could learn ገባ ተብሎ ሲታይ
Facebook ላይ መልስና አስተያየት ከሰጡት ሰዎች ውስጥ አንዱ በፈቃዱ ሞረዳ ነበር። በፈቃዱን በስም አውቀዋለሁ። የሚጽፈውንም የሚገጥመውንም አነበላህ። በፈቃዱ የጻፈውን እንዳለ እዚሁ ልለጥፍ:- Befekadu Moroda አቶ አሰፋ…እንዴትም ይሁን ለምን ፣ስለኦሮሞ ማሰብዎ/መጠበብዎ ለእኔ ችግር የለዉም፡፡ እንዲያዉም ከዚህ የበለጠ እንዲያሳስብዎትና እንዲያናግርዎት ነዉ ፀሎቴ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ በቅጡ የሚጠቀምበት ከሆነ የወዳጁም ሆነ የጠላቱ ሐሳብ ያስፈልገዋል፡፡ይጠቅመዋልም፡፡እርስዎ ኦሮሞን እንዴትም ይጥሩት ዋናዉ ቁምነገር ‹‹ እንደዚያ›› የሚባል የራሱ ታሪክ፣ ባሕል፣እምነት፣ ቋንቋ፣ ማኅበራዊ ስነልቦና በአጠቃላይ እርሱን ከሌሎች የሚለዩት፣ እንዱሁም የሚያመሳስሉት የተከበረ ማንነት ያለዉ ሕዝብ መኖሩን ማወቁ ላይ ነዉ፡፡ ተወደደም፣ ተጠላም፡፡ ስለእርስዎ ሳስብ ሁሌም ወደአእምሮዬ የሚመጣዉ ጥያቄ ‹‹ አቶ አሰፋ ስለኦሮሞ ያሰቡትን፣የተናገሩትን፣የፃፉትን ያህል ስለጋሞ ግድ ብሏቸዉ ያዉቃል? ›› የሚል ነዉ፡፡ ጋሞ ዛሬ በአደባባይ ልነገርለት የሚገባ ችግር የለዉ ይሆን? ይህን ችግሩን የሚናገርለትስ ልጅ አልወለደ ይሆን;? ተስፋ አደርጋለሁ፤ እግዜር ከሰጠዎት ዕድሜ በቀረዎት ጊዜ ስለጋሞ ሕዝብ ብዙ የማናዉቃቸዉን ሀቆች ፅፈዉ ለታሪክ ትተዉ ያልፉ ይሆናል፡፡

የበፈቃዱ አስተያየት ብዙ አንድምታ ያለው ይመስለኛል። አንድምታው “ኦሮሞን ለቀቅ አድርገህ ለምን ስለጋሞ አትጽጥፍም!” የሚል ነው። የዚህ አይነት አስተያየት በመጠኑ በየጊዘው ይደረሰኛል። ባለፈው ሰሞን አንድ “ግዕዝን ለቀቅ አድርገህ ጨንቻ ላይ ብታቶኩር አይሻልም!??” የሚል ሁለት የጥያቄ ምልክት ያለበት ነበር። ከኦሮሞዎች አካባቢ ከዘለፋው ሌላ “ስለኦሮሞ አንተ ምን አገባህ ?”የሚል ተደጋጋሚ አገኛለህ። አንድ ሌላ የማውቀው ሰው “አሁንማ ሙሴ ሆንክላቸው!” አለኝ። “ለማን?” ብለው” አማራና ነፍጠኛና ባህሩን አሸገርካቸው!” አለኝ። “ወደተስፋይቱ፣ ቃል ወደተገባላቸው አገር አሻግሬ ከሆነ ጥሩ ነው!” ብዬ አለፍኩት። የአማራና የነፍጠኛ ደጋፊ ነህ ለማለት መሆኑ ነው።

እዚህ ግልጽ እንዲሆን የሚያስፈልግ መሠረታዊ ነጥብ ያለ ይመስለኛል።እኔ ስለማን ፣ስለምን እንደምጽፍ፤መጻፍ እንደሚገባኝ ፤እንደማይገባኝ ሊነገረኝ ፣ሊያዘኝ የሚችል ሰው በዚህ ምድር ላይ የለም። ይህ መሠረታዊ ፤ሰበአዊ መብቴ ነው። የኔ ብቻ ሳይሆን የማንኛችንም፤የሁላችንም መሠረታዊና ሰብአዊ መብት ነው። ስለዚህ ያ ለውይይት የሚቀርብ አይደለም!

ሌላው፣ በኦሮሞ፤በአማራ በጋሞ፤ብሎም በማንኛቸውም የሰው ዘር ላይ የተለይ የግል መብት(Monopoly) ያለው፤”እዚህ ድርሽ እንዳትል!” የሚል የለም!ሊኖርም አይገባም!! ብዙ ጊዜ እንዳልኩት፣ “ማንም ሰው ደሴት አይደለም!” ተያይዘን፤ተቆላልፈን ፤ተነባብርን የምንኖርና የምንጓዝም ነን ። የትም ይኑር የትም የአንድ ሰው ደስታው ደስታዬ ነው፤ሕመሙም ህመሜ ነው። ፈረንጅ We’re in This Together”የሚል ዘፈንም አለ።በዚህ መለኪያ ነው የምኖረው! የምጽፈውም!

ይህን ካልኩ በኋላ በፈቃዱ ሞረዳ ስለአነሳውና ስለሰጠሁት መልስ ሊህድበት። ”መጽሐፌን “የትዝታ ፈለግ” አላነበብክ እንደሁ እባክህ አንብበው።ምእራፍ አስር” የዶርዜ ማርያም”፤ምእራፍ አስራ ሰባት

Page 4 of 7
“የፈሩት ይደርሳል”፤ምእራፍ ሀያ ስምንት ፤”እንደዶርዜ እህቶቼ”፤”የትዝታ ፈለገ ፱” ስለቀኛዝማች ኢልታሞ ኢቻ የተጻፈው ስለጋሞ ነው።
አውስትራሊያ፤ካሳሁን ሰቦቃ በሚያዘጋጀው SBS የራዲዮ ቃለ መጠየቅ ስለጋሞ ሰፋ ያለ አስተያየት ሰጥቼ ነበር።እዚያ ውስጥ” እንደኔ እንደኔ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደጋሞ ቢሆንልኝ ደስታውን አልቸለውም ነበር!” የሚልም አለበት። ከያሬድ ጥበቡ ጋር “መወያየትመልካም”ፕሮግራሙባደርኩት ቃለ መጠየቅ ስለጨንቻ በሰፍፊው አውግቼ ነበር። በኢትዮጵያ ውስጥ ጨንቻን የሚስተካከል ከተማ ቢኖር አዲስ አበባ ናዝሬት ብቻ ይመስለኛልም ብያለህ። “ዜናሁ ለጋላ “ስለተጻፈበት ብርብር ማርያም በዩሱፍ ያሲን “ማንነት .. “መጽሐፍ ግምገማ በሰፊው ጽፌ ነበር። ይህ ሁሉ Facebook በድረገጾችም በ አዲስ አድማስም ወቷል” የሚል ነው።

ሁለት ነገር! አንደኛ ይህ ስለእኔ አስተያየት ለምን ተሰጠ የሚል አይደለም። ወድጄ ፈቅጅ “ የአደባባይ ሰው” ሆኛለሁና ያ “የሕዝብ ንብረት” ያደርግኛልና፣ ማንም ሰው ሊተቸኝ፣ ሊያርመኝ፣ ሊነቅፈኝ፤ ሊያስተካክለኝ መብቱ ነው።
ሁለተኛው ግን” መረጃ ሙሉ ሰው ያደርጋል!” የሚሉት ነው። ስለእኔ ለመጻፍ፤ የጻፍኩትም፤ የተጻፈልኝም፤የተጻፈብኝም፤የተገጠመልኝም እዚያው አደባባይ ላይ ሞልቶ ተርፏል። Google የማድርግ ጉዳይ ብቻ ይመስለኛል። በዚህ፤ አደባባይ ያለ ማስረጃ ሳያዩ ወይም ሳያስተውሉ ቀርተው ለምሳሌ ያክል ስለጋሞ አትናገርም ማለት ከጭብጡ ወጭ ይመስለኛል። እውነት አይደለምና! እውነቱ ተመዝግቦ ተቀምጧልና!
“ እገሌ፣እነእገሌ መንደራቸው የት ነው!”ብዬ አይደለም የምጽፈው። ለዚህ ማስረጃ እዚያዉ “የ ትዝታ ፈ ለ ግ ውስጥ ይገኛል።ምእራፍ ሁለት “በግ ካራጁ ጋር..” ስለጎንደሬው ዶክተር ካሳሁን መከተ፤ምእራፍ ስድስት “የኔይቱ ጀግና” ስለዘውዲቱ አስማረ ነው። ዘውዲቱ ዎሎዬ ነች።ምእራፍ አስራ ስድስት “በማተቡ ይዳኝ “ ወዳጄና ጓደኛዬም ስለነበረው ሰለኮሎኔል ደበላ ዲናሳ ነው።፣ ደበላ ደግሞ ኦሮሞ ነው።ምእራፍ ሶሰት “ልብ ያለው ልብ ይበለው” ስለረዘነ ወልዱና ስለወይናይ ነው።ኤርትራዊያን ናቸው። ብቻ ከተነሳ አይቀር ብዬ እንጅ በምጽፈው “ከየት መንደር መጣ!?” የሚል መመዘኛ የለኝም። ሰው መሆኑና፤በኔ ግምት ሊነገር የሚገባው ነገር አለ ብሎ ማመን በቂየ ነው። እንዲያ የሚያዩ ደግሞእኔን ወደዚያ ለመጎተት መሞሩ ጥሩ አይመስለኝም። በዚህ ዕድሜዬ “አዲስ አሰፋ!” አልሆን ነገር!

ወደ ባንዲራው
ሶስት ነጥቦች አንስቼ ባጠቃልል የሚሻል ይመስለኛል
flag_of_the_oromo_liberation_front-svgአንደኛው የኦሮሞ ባንዲራ የተባለው የኦነግ ባንዲራ ነው። “ከፍተን ብናየው!ሻአቢያና የኦነግ መስተፋቅር” በሚል የጻፍኩት በየድረገጾች ላይ ከመውጣቱም ሌላ በFacebookና በአዲስ አድማስም ላይ አዲስ አበባ ታትሟል። የወጣው በNovember 26,2016ነበር። አንድ ሰው በራዲዮ አንብቦትና በUtube ሆኖ
Page 5 of 7
ድረገጾች ላይ ተለጥፏል። ይህንን በራዲዩ የተነበበውን ዛሬ ጥዋት ድረስ 154,000ህ ሰው አድምጦታል።ይህ አዲስ አድማስ ፤Facebookና በየድረገጾች ላይ ያነበቡትን ሳይጨምር ማለት ነው።
በዚህ “ከፍተን ብናየው..”ጽሁፍ ላይ ኦነግን ከውልደቱ ጀምሮ አንስቻለሁ። ሳጠቃልልም” ያንን ታላቁንና ገራገሩን የኦሮሞ ሕዝብ ሥም ተሸከመው ሕዝቡን የሻንጫ ተሸካሚ ተምሳሌት ማድረግ የለባቸውም!” የሚል ነበር። የሚያሳፍርና ሊያፍሩበትም ይገባልም ብያለህው።
የኦነግ መሪዎች ወንጀለኞችም ናቸው ብያለሁ። ለማስረጃ ያቀርብኩት ሁለት ብቻ ነበር።አንደኛው ከሻአቢያ ጋር ሆነው አሶሳ በሰፋራ ሰፈር የነበሩትን ኢትዮጵያውያን በጥይትና በእሳት ማጋየታቸው ነበር። ሌላው የኦነግ ተዋጊ ወታደር ነው ያሉትን የወይኔ/የሻአቢያ ሽንጣ ተሸክመው አዲስ አበባ እንደገቡ ወያኔ “ወታደር ካምፕ አስገቡ!’ ብሎ ሲያዛቸው አስገቡ። “ድርሻችሁን ጨርሳችኋልን ከዚች ኢትዮጵያ ከምትባለው አገር ልቀቁ ወይም ወህኒ ውረዱ!” ብሎ ለኦነግ መሪዎች ትእዛዝ ሲሰጥ ከአገር ወጡ። እነዚህ ወታደር ካምፕ የገቡ የኦሮሞ ልጆች ወደ ወህኒ ወረዱ። እስከዛሬ ስለነዚህም ሆነ በብዙ ሽህ ለሚቆጠሩ በኦነግ ሰበብ-አስባብ ለሚሰቃዩ ትንፍሽ ያለ የኦነግ መሪ፤ተከታይ ወይም ጭፍራ የለም።ከነዚህ ፤በኔ ላይ ዘለፋ በሚያወርዱትም ሆነ በሌንጮ ባቲ ወይም በበፈቃዱ ሞረዳ ለዚህ ጉዳይ የተሰጠ መልስ፤ማስተባቢያ፤መደገፊያ ነገር የለም።

ማንናቸውም ድርጀት፤የንግድ ሆነ የፖለቲካ ሲከስር ይዘጋል። ኦነግ በተግባር ከስሮ ከተዘጋ ቆይቷል። አሁን የተያዘው ሥራ በኦሮሞ ስም ንግድ ነው። እንግዲህ የሌንጮ ባቲ ወንድም፤አምቦ ባቲ፣ መመረቀ አለብኝ የሚለው በዚህ ባንዲራ ጥላ ነው። ጎበዝ! እይተስተዋለ ቢሆን የሚሻል ይመስለኛል።
ሁለተኛው “ራስን ፍለጋና ትዝብት!” በሚል ርእስ ጽፌ ነበር። ያም እላይ በገለጽኳቸው የመገናኛ ዘርፎች ሁሉ ወቷል። የዚያ ጽሁፍ ምክንያት የሆነው አንድ አንባቢ በድረ ገጾች በተለጠፈ ጽህፍ ጥያቄ አቅርቦልኝ ስለነበር ነው። አንደኛው ጥያቄ “ወያኔ እንደገባ በጎሳ ድርጀት ስም ምክር ቤት ገብተሀል” የሚልና ሌላው”ኦነግ እርሶ ቢሮ ነው የተፈለፈው!” የሚል። ለዚህ መልስ ሰፋ ባለ መልኩ ሰጥቼ ነበር።

በጎሳ ድርጀት ሽግግር ምክር ቤት ገበተሀል ለተባለው “በጎሳ አይደለም!ኦሞቲክ በሚል ድርጀት ስም ነው” ብዬ ኦሞቲክ ማለት ምን ማለት እንደሆነ አስረዳሁ። በዚያ ሳቢያ የጅማው አባጅፋር ከአጼ ምንሊክ ጦር ጋር 30,000 ወታደር ይዞ ከፋ ፤10,000 ይዞ ወላይታ ዘምቶ እንደነበር፤ጅማ ቤተ መንግስቱ ፤ሔርማታ የባሪያ መሸጫ ገበያ እንደነበረ፤በዚህም ምክንያት ከጋሞ ጭምር አባጅፋር ግማሽ ሚሊዮን ባሪያ እንደነገደ፤ ጅማና ወለጋ የባሪያ ንግዱ አካልና አምሳል መሆናቸውን የሚገልጽ ነበር።በባርነት የተሸጡት ደግሞ በጦርነቱ የተሸነፉት ኦሞቲኮች መሆናቸውንም ገልጫለህ::በዚያ ጽሁፍ ም ክ ን ያት ሆኖ ዛሬ Facebook ላይ ከየቦታው የተሰባሰቡ ታዳሚዎች ጅማ፣ሔርማታ ላይ ለነዚህ በ አባጅፋር ተፈንግለው ለተሸጡት መታሳቢያ ሐውልትና ቤተመዘክር ለማቋቋም በመነጋገር ላይ ናቸው።እኔንምሊቀመንበር ሁንልን ብለዋል።

ለዚህ በኦሮሞና ዛሬ የኦሮሞ ምድር በሆነው ለተፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት ከነዚህ ለኦሮሞ ነፃነት እንታገላለን ካሉት ውስጥ ትንፍሽ ያለም የለም። ኦሮሞ ሰው ነው! እነዚህ የተነቀሉትና የተፈነገሉት ም ሰዎች ነበሩ! የሰውን ዘር ሁሉ የማይጨምር ነጻነት የሚል ቃል ያለ አገባብና ያለቦታው የዋለ ፤በውስጡ የተደበቀ ሌላ ተልእኮ ያለው ይመስለኛል!
ሁለተኛው በዚሁ ጥያቀ ሳቢያ ኦነግ የነበረው ፤እኔአነው ለጋሞ ጎፋ ዋና አስተዳዳሪነት ያሾምኩት ፤መኮንንገላን፣ደምሴ ደሬሳ ከሚባል የደርግ አባልል ጋር ሆኖ ጋሞ ጎፋን ከጋሞ ጎፋ ተውወላጆች አጽድቶ

Page 6 of 7
በኦሮሞ ሲተካ እንደነበረም ገልጫለህ።ከዚህም ሌላ ኦነግን እኔንና ትንሽ ወንድሜን ለ እስራት ፤ታላቅ ወንድማችንን ወደጦር ሜዳ በማመላክ ቤታችንን ያለተጠሪና ጧሪ አስቀርቶ አንደነበር ገልጫለህ። ከመንግስቱ ኃይለማርያም ጋር ለመጨረሻ ጊዜ ፊት ለፊት እንድንቆራረጥ ያደርገው አብዩ ገለታ ፤ዶክተር ታደስ ቀነዓ የሚባል ሰው እንዳስፈታ ለጠየቀኝ መንግስቱ ጋር ቀርቤ በነበረበት ጊዜ ነበር።

የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ይመስለለኛናል ዋሽንግተን ዲሲ በኢሳት ተለቨዥን ቃለ መጠይቅ ሳደርግ ይህንኑ አንስቼ ነበር። ከዚህም በላይ ለጋዜጠኛው ሲሳይ አጌና እባክህን እነዚህ የኦነግ መሪዎች የሚባሉት እዚሁ አሜሪካ ስለሚገኙ ጛጋብዘህ እ ኔ የልኩትን እአንዲያምኑ ወይም እንዲያስተባብሉ አድርግም ብዬ ነበር። የኢብሳ ጉተማ ስልክ ቁጥር ስለነበረኝር ለሲሳይ አጌና የስልክ ቁጥሩንም ሰጠተሁኝ። ሲሳይደውሎ ለመቅረብ ፈቃደኛ አልሆንምብሎ።
ዛሬም የኦነግ መሥራችና መሪዎች ነን የሚሉ፤ አብዩ ገለታ፤ኢብሳ ጉተማ፤ መኮንን ገላንና ሌንጮ ባቲ ከጨለማ ተገን ወጥተው በአደባባይ ቢያስተባብሉኝ ወይም አምነው ቢቀበሉ በብርቱ የምንማማርበት ይመስለኛል።
ዘለፋዎችን በመሠረቱ የቀሰቀሰው መነሻ ምክንያት ምን እንደሆነ የገልጽኩ አልመስለኝም። ዛሬ በኢትዮጵያ ላይ አንዣቦ በሚታየው ፖለቲካ ላይ የተለያዩ መጻጽፎች ላለፈው ሶስት ወራቶች ለማቀረብ እየሞከርኩ ነው። ሁለት ይቀሩኛል። አንደኛው “ያጋር ቤታችን !ቅርሳችንና ውርሳችን!” የሚለና ሌላው “ዝም ብንል ብናደባ ..”በሚል ረስ ይሆናል።” የጋራ ቤታችን…” የሚለው አሁን ቢያንስ በማሕበራዊ ገጾች በተለየም ዲያስፖራ በሚባለው መድርኩን ያጣበበውን በ አማራና ኦሮሞ ስም የሚደረገውን የተዘጋ ዶሴ (Dead File)ለመክፈት የሚደረገውን መራወጥ ለመዳሰስ ነው።”ዝም ብንል..” ደግሞ “እንዲያው በዚህ ሁሉ መራኮት ውስጥ የደቡቡ ኢትዮጵያዊው ኢትዮጵያን እንዴት ሲረዳት ኖረ? አሁንስ እንዴት ያያታል?” የሚለውን ለመቃኘት ነው። የጥሬቴ ነገር-ዓለሙ ይህን ካደረኩ፤በኔ አስተያየት፣መሐል መንገድ ላይ ያተኮረ ፤ኢትዮጵያን ያማከለ ውይይት ይፈጥራል የሚል እምነትና ተስፋ ነው።”እኔም የድርሻዬን!” ለማለት ነው። ሁላችንም ድርሻ ድርሻ አለንና!
“የጋራ ቤታችንን” ጨርሼ በ10 ቀን ውስጥ አደባባይ አዋጣለሁ። አማራና ኦሮሞ የሚመለከት ነው የሚል Facebook ላይና ሌላም ቦታ ጠቃቀስኮ። ይህ እርግማንና ዘለፋ የተጀመረው ገና ባልታየ፤ባልተነበበ ጹሁፍና አስተያየት ላይ ነበር።ያ ነው ይበልጥ የገረመኝ። ከማንውቀው ይሰውረን ማለት ይሆን ? ከምናውቀው ግን ከሸሸነው እውነት ሰውረን ነው? አውቀን የካንደነውን እውነት አታስታውሰን ማለት ይሆን? ይህንን ደህና ያጧጧፍነውን ሥራና ገበያ ይሻማብናል ማለት ይሆን? ሥራ ያሰኘን በተለየ አንዳንድ ዲያስፖራው ኗዋሪዎች መተደዳደሪያም ወደመሆን የተቃረበ የሚያስመስል ፍንጭ ስለሚታይ ነው። በተፈጠረው የሕዝብ አመጽ ሳቢያ ታዋውቂ ሆነን፤አገር አውቆን ፣ፀሐይ ሞቆን፤ አንቱ የተባልንበትን ልታፈርስብም ነው የሚል ስጋት ፈጥሮ ይሆን? የሚል መላ ምት ይፈጥራል።
ለማጠቃለል
እኔ የምለውን የምለው “ እገሌ፤እንእገሌ እንዳሉት ብዬ መጽሐፍት ጠቅሼ ነው።መጽሐፍ ካልጠቅስኩ ደግሞ እዚያው አገሪቱ፤ምድሪቱ፤ኢትዮጵያ ላይ የተነጠፈውን ፣ድፍን አገር የሚያውቀውን፣ ፀሐይ ሲሞቀው የኖረውን ማስረጃ ጠቅሼ ነው።በከፊል ልክ ላልሆን እችላለህ! ሙሉ ለሙሉም ልክ ላልሆን እችላለሁ። ያንን ደግሞ እንዲሁ ታሪክም፤የአይን ምስክርም ፤ምድርቱን ጠይቆና ጠቅሶ
Page 7 of 7
ማስተባባል፤ማስተማር ነው።ያ ያባት ነው! ያ ሲሆን ነው ወደኋላ ሳይሆንወደፊት የምንጓዘው! ሁለት እርምጃ ወደኋላ ሳይሆን አንድ እርምጃ ወደፊት ይሆናል!
ህግ ውስጥ “ያልተካደ/ያልተስተባባለ ሁሉ እንደታመን ይቆጠራል!” ይላል Silence ammounts to acceptance። ይህም ወደፍትሐብሔር ሕግ ሥነስረዓት ገብቶ “በክሱ ማመልክቻ ላይ የተነሳውን ጭብጥ እያንዳንዱን በግልጥ እመን ወይም አስተባባል “ይላል። ይህ ካለሆነ ዳኛው ወይ እንዳለተካደ/እንደታመነ ቆጥሮ ይፍርዳል። ወይም ኪሳራ ቆርጦ እንዲያስተካክል እድል ይስጣል። ይህን ያነሳሁት እላይ ለጠቀስኳቸው ሳያገለግላል አይቀርም በሚል ነው።

ካህኑ እንደሚለው “አውቆ በድፍረት ሳይውቁ በስህተት ከማሳሳት ይሰውረን!”
January 12, 2017

Filed in: Amharic