>
4:18 pm - Saturday April 16, 1301

በጌድዮ ዞን ፖሊስ አዛዥ በአጋዚ ተገደለ - የቧንቧ ውሃ ተመርዟል [ክንፉ አሰፋ]

Street_scene_in_Dilla-Ethiopia-150x150በጌድዮ ዞን የምትገኘው ዲላ ወረዳ ፖሊስ ዋና አዛዥ በአጋዚ ተገደለሲሉ በስልክ ያነጋገርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸውልናል።

ከሶስት ቀናት ቃጠሎ፣ ዘረፋ እና ውድመት በኋላ አጋዚ በትላንትናው እለት ዲላ እንደገባ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። አጋዚ የጦር ቀጠና ምትመስለው ዲላ ከተማ እንደገባ አቶ ከበደ የተባሉትን የዞኑን ፖሊስ አዛዥ በጥይት ደብድቦ ገድሏቸዋል።

ላለፉት ሶስት ቀናት በዲላ፣ ይርጋጨፌ፣ ወናጎ እና ፍሰሀ-ገነት የተነሳው አመጽ ያነጣጠረው በጉራጌ እና አማሮች ላይ ነበር። የጌዲዮ ተወላጆች ከአካባቢው ካድሬዎች እየታዘዙ አብያተ-ክርስትያናትን እና መስጊዶችን ጨምሮ 60 የሚሆኑ መኖርያ ቤቶችን አቃጥለዋል። ህወሃት ሕዝባዊ አመጹን  መቛቛም ስላልቻለ ከ10 አመታት በፊት የነበረውን ቁርሾ በመቀስቀስ የጌዲዮ ተወላጆች በአማራ እና በስልጤ ተወላጆች ላይ ዘመቻ እንዳስነሳ ነው የአካባቢው ሕዝብ የሚናገረው።

በስልክ ያነጋገርናቸው አንዲት የአማራ አዛውንት ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ እንደወደመና የሚያርፉበት መጠለያ እንኳን እንደሌላቸው ተናግረዋል።ልጆቻቸው በሙሉ ጥቃቱን በመሸሽ ወደ ጫካ እንደገቡም ተናግረዋል::   የአካባቢው የስልጤ ተወላጆች ለግዜው በመስጊድ ውስጥ ተጠልለዋል ብለዋል።

በይርጋጨፌ፣ ዲላ፣ ወናጎ፣ ፍሰሀ-ገነትና በአቅራቢያው የሚኖሩ ሰዎች የቧንቧ ውሃ እንዳይጠጡ ውስጥ ምስጢሩን የሚያውቁ ዜጎች ለሕዝቡ ተናግረዋል።በጌዴኦ ዞን የከተማው ነዋሪ ለመጨረስ የመጠጥ ውሃውን ዴፖ መርዘዋል እየተባለ ነው።

ዲላ ነዋሪ ሕዝብ ላለፉት ለሶስት ቀናት የከፋ መከራ ውስጥ ነው ያለው። የአካባቢው ፖሊስ ሕዝቡ ከቤት  እንዳይወጣ ሲያዝዝ አጋዚ ደግሞ ከቤት ወጡ የሚል ትእዛዝ እየሰጡ ነው።

ትናንት ከተማው ውስጥ የገባው አጋዚ አስታራቂ በመምሰል የሚፈልገውን እያሰረ እና እየገደለ እንደሚገኝ ነው የተነገረው።

በአካባቢው ያሉ የመንግስት ባለስልጣናት እና ካድሬዎች በሙሉ አዋሳ ገብተው እንዳበቁ ወደ አዋሳ የሚወስደው መንገድ ዝግ ሆኗል።

በትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት ሆን ተብሎ እንዲህ ያለው የዘር ግጭት በጊዴዮ እንዲባባስ ሕጻናትን ጭምር ማስታጠቁን የግጭቱ ሰለባዎች ይናገራሉ።

Filed in: Amharic