>
5:13 pm - Friday April 18, 2442

በመታሰሬ አልገረመኝም! [ኣብርሃ ደስታ]

Abrha Desta 30.07.2016ፌስቡኬን እንደከፈትኩ “ኢህአዴግ እንደገና እንዳያስርህ ረጋ በል” የሚል የወዳጅ ምክር አገኘሁ። አልገረመኝም። ምክንያቱም ወዳጄ አዲስ ነገር አልነገረኝም። ምክንያቱም ኢህአዴግ በፅሑፍ የሚሸበር፣ ነፃነትን የሚያፍን ጨቋኝ ስርዓት መሆኑ አውቃለሁ። አዎ! ስንፅፍ ኢህአዴግ ያስረናል። ምክንያቱም በነፃነት ለመፃፍ የሚሞክሩ ግለሰቦች ያስራል። በኢህአዴግ ዘመን እስር አዲስ ግኝት አይደለም። ይታወቃል፣ ይጠበቃል። ግን ኢህአዴግን የምንተችበት አንዱ ምክንያትኮ ስንፅፍ ስለሚያስረን ነው። በነፃነት ፅፈን ባንታሰር ኖሮ እንዴት ኢህአዴግን በዓፋኝነት እንተች ነበር? (ሌላ እንዳለ ሁኖ)። ኢህአዴግን የምንወቅሰውኮ ስለሚያፍነን ነው። ስለሚያስረን ነው። ባያስረንማ አንቃወመውም ነበር። ምክንያቱም የፈለግነውን ፅፈን ካልታሰርን ኢህአዴግ ጥሩ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ኢህአዴግ ጥሩ አለመሆኑ አውቀን እየተቸን ፅፈን መታሰራችን ሊደንቀን አይገባም። አዎ! ኢህአዴግ ዓፋኝ ነው፤ ስንተቸው ያስረናል። ምክንያቱም ማሰርና ማሳሰር የኢህአዴግ ባህሪ ነው። ለነፃነት በነፃነት መፃፍ፣ የሚመጣውን መቀበል፣ ለራስ ተግባር በራስ ሓላፊነት መውሰድ ደግሞ የኛ ባህሪ ነው። እናም በመታሰሬ አልገረመኝም። ኢህአዴግ ባህሪውን ያንፀባርቃል፣ እኛም የነፃነት ጉዟችን እንቀጥላለን። ለትግል ከሚያነሳሱኝ ምክንያቶች አንዱ የኢህአዴግ ዓፋኝ ባህሪ ነው። ነፃነት ግን በራስ ሓላፊነት መውሰድ ያጠቃልላል። ስለዚህ ለሚደርስብኝ ነገር እኔው ራሴ ሓላፊነት እወስዳለሁ። በዓፈና ወቅትም ነፃነት እፈልጋለሁ። ምክንያቱም ነፃነት ከሌለኝ ህይወት እንዳለኝ አልቆጥርም። ያለ ነፃነት ህይወት ከሌለኝ ምን እንዳላጣ እፈራለሁ? ነፃነት ከሌለ የሚያስፈራ ነገር የለም። በነፃነትም ፍርሓት የለም። እናም ነፃ ነኝ። It is so!!!

Filed in: Amharic