>
5:13 pm - Sunday April 20, 2786

‹‹ህልምህ ቅዠቴ ነው›› [ህይወት እምሻው]

…ሲሆን ሲሆን፣ የዜጎቹ ህልም ለመንግስት ቅዠት ሊሆን አይገባም፡፡

Habtamu Ayalew30062016ይሁንና፣ ህልም በሚታሰርበት እንጂ በማይፈታበት ሀገር እንኳን፣ ‹‹ለሀገሬ ህልም አለኝ…ለህልሜ እሞታለሁ›› ብለው ያንቀላፋ በበዛበት የሚነቁ፣ የተኛ በበረከተበት የሚነሱ ጥቂቶች አሉ፡፡

ሐብታሙ አያሌው እንዲህ ያለ ሰው ነው፡፡
ህልሙ ጣመንም አልጣመንም፣
ሃሳቡ ከእኛ ሀሳብ ገጠመም አልገጠመም፣

ሐብታሙ እንዲህ ያለ ሰው ነው፡፡

አዎ …ፖለቲከኛ ነው፡፡
አዎ…ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ነው፡፡
ግን መጀመሪያ ሰው ነው፡፡
ሰው፡፡

እናም፣ ‹‹የአንተ አይነቱ ህልም ለእኔ ቅዠቴ ነው›› ብሎ ክፉኛ የታመመን ሰው ‹‹አትታከምም›› ማለት ፍርደ ገምድልነት ብቻ ሳይሆን የእጅ አዙር የሞት ፍርድም ነው፡፡

Filed in: Amharic