>

ከሬሳ በታች ሰው!

Keresa betach sewአክሊሉ ምንተስኖት

የወስላታ ጊዜ፥ ያድር ባይ ምናምን፤
አስከሬን ላይ ቁሞ፥ ይታያል ሲለምን።

እያሞዳሞደ ዛሬን ቢመቸው፤
ከሰው መፈጠሩን እንዴት እረሳው?

ከዚህ ሰውየ ላይ አንድ እውነት ተገኘ፤
ከበድኑ አንሶ፣በፎቶ አስደግፎ፣ በአለም ተናኘ።

ይሄ ጋዜጠኛ
ለማን ፃፍክ ቢሉት ለማን ነው የሚለው?
ስብዕናን አርክሶ፤ ኢትዮጲያዊነትን፤
ምንስ ተጠቃሚ፣ ምንስ አትራፊ ነው?
እኔ ልንገራችሁ
ሃቁም፣ትርፉም፣ጥቅሙም ይሄ ሰው ከርሱ ነው።
ሃይማኖቱ ጣኦት፤ ሆዱን አምላኪ ነው!!

Filed in: Amharic