>

ጥቂት ነገሮች [ፕሮፌሰር ደጀኔ ኣ. ላቀው]

Prof. Dejenie Alemayehu Lakewወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ያለው የሰሜን ጎንደር ህዝብ የትግራይ ወያኔን መንደራችን ዉስጥ ማየት አንፈልግም ወልቃይት ጠገዴ አማራ ነው ብሎ ታሪካዊና ኢትዮጵያዊ ጀግንነቱን በተግባር እየገለጸ ነው፤ ለዚህም የወያኔን አስተዳደር አንቀበልም ፤ በወያኔ በተሾሙ ሌቦችም አንተዳደርም በማለት ሌት ተቀን ወየኔንና ሆድ አደር የሆኑ ሃገር ያፈራቸውን እንክርዳዶች እየተዋጋ ነው፤ ይህ ትግሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጣሊያን ጋር ያደረገውን የነጻነት ትግልን በትክክል የሚያንጸባርቅና ማንም ኢትዮጵያዊ ትግላቸውን ሊደግፍና ሊቀላቀላቸው ይገባል። ጀግናው የጎንደር ህዝብ እንኳን ከብብቱ ስር እንደአይጥ አፈር እየቆፈረ ያደገንና በመሰሪ ተንኮል አጭበርብሮ ለጊዜው በጠበንጃ ሃይል በማናልበኝነት እኩይ ተግባሩ ቢያብድም ወያኔን የማይቀጡ ቅጣት በመስጠት ልክ እንደሚያስገባዉና ከመጣበት ጉድጓድ ተመልሶ እንዲገባ እንደሚያደርገው በሙሉ ልብ መናገር ይቻላል፤ ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል ነው የወያኔ በጎንደር ላይ የሚያሳየው እብሪት። ሁሉንም ጊዜና ታሪክ በመዝገብ ዪዞ ለወደፊት ትውልዶች ትምህርታዊ እዉነታወችን ይመሰክራሉ ። ለዚህም ተግባራዊነት የጎንደርና የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ ላይ የሚያደርገዉን የተባበረ ትግል ማጠናከር አለበት። የወያኔ ስልት በሆነው ከአማራ ይልቅ እኔ እሰራልሃለሁ እቀርብሃለሁ በሚለው አስመሳይ ጸባዩ አሁንም የአማራ ክልል አስተዳደር የቅማንትን ህዝብ ይቅርታ ይጠይቅ የሚል የልጆች ጨዋታ መሰል የድለላ ሃሳብ ይዞ መጥቷል ፤ የትግራይ ወያኔ ግን የጎንደር አካል የሆነዉን የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ ይቅርታ ዪጠይቅ እንዴት እንዳልተባለ የሚገርም ነው፤ ይሀን ሁሉ በደልና የዘር ማጽዳት ወንጀል ለሁለት አስርተ አማታት እየፈጸመ።

ባለፉት ጊዜአት የጎንደር ህዝብ በተለይ የጋይንት የደብረታቦር የባህር ዳር ሌላዉም አማራ የሆነ ሁሉ ስለወልቃይት ጠገዴ ጥያቄ አለን መወያየት እንፈልጋለን ጉዳዩ ያገባናል ቦታው ታሪካዊ የሆነ የኛ የአማራው ታላቅ እርስት አካል ነው ብለው ጥያቄ ሲያነሱ የወያኔ የዉስጥ ተወካዮች ስለወልቃይትጠገዴ ሳይሆን ስለአለንበት አካባቢ ብቻ ነው መወያያት የምንችለው እየተባሉ ጥያቄዉንም ማንሳት እንደወንጀል እያስቆጠረ እያለ፤ የጎንደር መሬት ለሱዳን መሰጠቱን ሲቃወሙ ፤ ባጠቃላይ ስለሃገር ጉዳይ ማዉራት መጠየቅና ህዝብ ያገባኛል ሲል አያገባህም ከተባለ እንዴት ነው የወያኔ መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ ሃገርህ ተወራለች ብሎ ማስነሳትና ታሪካዊው በሆነው ኢትዮጵያዊ ጅግንነት ማዋጋት የሚችለው? ሃገር ማለትስ በዚህ መሰረት የቱ ነው እሱ ከማይኖርበት አካባቢ ከሆነ? ወያኔ ዪጠቅመኛል ያለዉን ፤ ሃገር ሊሆነኝ ይችላል ብሎ የወሰነውን ቦታ ለመከላልከል ነው ህዝቡ ለጦርነት የሚሄደው ማለት ነው? ወያኔ እጅግ በሚያሳዝን መልኩ ሃገርን እያፈረሰና የህዝብን ሃገራዊ ወኔ እያንኮላሸ ፤ ግን በዉጭ የእርዳታ ወይም በቀጥታ በሚገኝ የገንዘብ ሃይል በመጠቀም የሰውን ሆድ ብቻ በመግዛት፤ የፖሊስ ሰራዊትና እስር ቤትን በማስፋፋት ደግሞ አስተሳሰብን ነጻነትና እዉነትን በማፈን የኢትዮጵያን ህዝብ እንደ የግኡዝ ወይም ለሆዳቸው የሚያስቡ እንስሦች ስብስብ አድርጎ ለመግዛት የሚያደርገው ጥረት የበለጠ የዋህነቱን፤ የበሰለና ምክንያታዊ የሆነ የፖለቲካ ርእዮተ አለም እንደለለዉና የሚያገኘው የአፍ ማዘጊያና የሆድ መያዣ የሆነው የዉጭ ገንዘብ ሲያቆም ህልዉናዉም አብሮ እንደሚያቆም አላወቀም ። ቁሳዊ ነገሮችን ለስሜት ፍጆታ ብቻ በማቅረብ የሰወችን ድጋፍ ለማግኘት ጥረት ማድረግ ላጭር ጊዜ ሊሰራ ዪችላል ፤ ማሰብን፣ ነጻነትንና እዉነትን ለማፈን ግን ምንም ቁሳዊ ነገር አያስቀራቸዉም። ለዚህም ነው ሁልጊዜም አምባገነኖች ባላቸው የሃብት ብዛት መጥፋታቸዉን መከላከል የማይችሉትና በእዉነትና ነጻነት ፈላጊው ህዝብ የሚጠፉት። ይህ ነው የትግራይ ወያኔም የመጨረሻ የእጣ ፋንታው ።

ኢትዮጵያን እያስተደደርኩ ነው የሚለው የትግራይ ወያኔ ቡዱን በንጹህ ኢትዮጵያዉን ሂወት አህጉር አቀፍ የነፍስ ዋጋ ሽያጭ እያደረገ ነው፡ የኢትዮጵያ ወጣቶችን ሃገራቸው ባልሆነው የሶማሊያ በርሃ ዉስጥ ደማቸው እንዲፈስና ለዚያም እኩይ ተግባር ወንጀሉን የሚመሩት የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የቁጭበሉ ጀነራሎች ከምእራባዉያን ሃገሮች የሚሰጣቸዉን የዉጭ ምንዛሬ ዶላር በመሰብሰብ ህንጻን መገንባት ንግድ ማስፋፋትና የተንደላቀቀ ህይወት መኖር ዪዘዋል ። የሞቱት ኢትዮጵያዉያን ግን ለምን እንደሚሞቱና መሞታቸዉም እንኳን በስነስርአት ለቤተሰ ሳይነገርና ሃገራዊ ክብር ሳይስጣቸው በየበረሃው ደማቸው ፈሶ እንደ እንስሳ ተረስተውና ሃገራቸው መስጠት የሚገባትን ክብር ሳያገኙ በከንቱ ዪጠፋሉ፣ ወላጅም ሃገርም እርሙን እንኳን ሳያወጣ እንደ እንስሳ ምንም ነገር እንዳልተለየው አስመስሎ በወያኔ ተገዶ ይኖራል፤ ይህ በዉነት ለኢትዮጵዉያን ሃገር ነው ወይስ የፍዳ ቦታ? ሁሉም ሃገሮች ዜጎቻቸው በጦርነት ሲሞቱ መጀመሪያ ለቤተሰቦቻቸው ማሳወቅ መንግስታዊ ሃላፊነትና ሃገራዊ ግዴታ ነው፤ ከዚያም ለሃገራቸው በከፈሉት የሂወት መስዋእትነት በወታደራዊ ክብር የሃገሪቱ መንግስት ባዘጋጀው የቀብራቸው ስነስርአት ይካሀዳል። ይህ ግን በትግራይ ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ እስካሁን አልታየም፣ ወያኔ ኢትዮጵያዉያንን ምንም አይነት ሃገራዊ ስሜት በሌለው ሁኔታ ተጥቅሞ እንደሚጣል የሸቀት እቃ ለገንዘብ ማግኛ እየተጠቀመባቸው ነው። የሚገርመዉ ነገር ደግሞ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ግለሰብ የትግራይ ተወላጅ እንዳለሆኑ ማንም እያወቀ ግን ተመሳሳይ ወንጀልና በደል የትግራይ ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በመለስ ዜናዊ ጊዜ የሚፈጸመዉን ያህል በበለጠ ሁኔታ እየፈጸመ እያለ እኔ ነን ጠቅላይ ሚኒስቴር ብለው በየመድረኩ ወያኔ የሰጣቸዉን የይስሙላ የስልጣን ማህተማቸዉን ይዘው መንከራተታቸው ነው።

በየትም ሃገር መሪወች ሲለዋወጡ ተተኪው መሪ ሙሉ ስልጣን ዪረከባል፤ ለቀደሙት መሪወች የተደረጉት ነገር ሁሉ ለአዲሱ መሪም ዪደረጋል፤ የመሪወች ስእል የሚለጠፈበት ቦታ ሁሉ የአዲሱ መሪም ስእል ይለጠፋል፤ አሜሪካን ሃገር አንድ ፕሬዘደንት የስራ ጊዜዉን ጨርሶ ሌላ ፕሬዘደንት ሲተካ ያለፈዉን መሪ ሃሳብና ያለዉን የወደፊት እይታ ሙሉ በሙሉ ተግባር ላይ ለማዋል ቃል እገባለሁ ብሎ ሳይሆን እኔ እንደዚህ ያለ የተሻለ ራእይና አድማሳዊ እይታ አለኝ ለተግባራዊነቱም በሃቀኝነት እሰራለሁ ብሎ ነው ቃል የሚገባው። ኢትዮጵያ ዉስጥ ግን የሚታየው ሌላ ነው፡ መለስን አመልካለሁ፤እሱ ያለዉን ቃል በቃል ምንም ሳልሸራርፍና ሳልጨማምር አቅሜ እስከፈቀደ ድረስ ተግባራዊ ለማድረግ የወያኔ አምላክ ይርዳኝ ማለት ብቻ ነው። ለዚህም ምስክር የሚሆነው ፣ በየክልል መንግስታት ቢሮወች፤ በየመሰብሰቢያ አዳራሹ፤ በጠቅላይ ሚኒቴር ቢሮ ዉስጥ ሁሉ የመለስ ስእል አሁንም ብቸኛው ተንጠልጣይ ስእል ነው ። አሁን ጠቅላይ ሚኒስቴር የሁኑትም ግለሰብ የኢትዮጵያ ህዝብ የሰጣቸው ስልጣን ሳይሆን ወያኔ እንደሰጣቸውና ለዚያም መለስን እያመልኩ መሞት እንዳለባቸው ከዚያ ዉጭ ማሰብም ማለምም እዳይችሉ የተወገዙ ይመስላል: የሳቸው ስእል በመሪነት የትም ቦታ እንደ መለስ መታየት የሚገባው ሆኖም የሚያስቡት አይመስልም ።

በመጨረሻም ለኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት፤ የፖሊስ ሃይል አባላትና ኢትዮጵያ ሃገሩን ለሚወድ ዜጋ ሁሉ ፡ በአለም ላይ ህዝብን ከህዝብ ያናከሱ የሰዉን ህልዉና የተፈታተኑና የሰዉን ዘር ለማጥፋት እጅግ እርኩስ የሆኑ በአእምሮ ብልሽት ተሰቃይተው ህዝብን የፈጁና ያፋጁ አምባገነኖች ነበሩ ፤ ነገር ግን እነሱን በህሊና እጦት በሙሉ ታዛዥነት ካገለገሉትና ከነሱም ከተጠቀሙት ሚሊዮኖች በበለጠ መልኩ እነሱን ለማጥፋት ወይም ያጠፉት ጥቂት ግለሰቦች በታሪክ መዛግብት ዉስጥ በህብረተሰባቸው ክብር መዝግብ ላይ የዘላለም ጀግና ሆነው ይኖራሉ፤ የዚያ የወንጀል ስርአት አገልጋዮችና ተጠቃሚወች ግን አምባገነኖች ሲጠፉ አብረው ዪጠፋሉ። በሞያችሁና በህሊናችሁ ህዝባዊና የወታደራዊ ሞያ ተልእኮን ያነገባችሁ ለእዉነት ብላችሁ ብትሞቱና የኢትዮጵያን ህዝብ ጠላት የሆኑትን የጥፋት መሪዎችና የወንጀል ተባባሪወቻቸዉን ለይታችሁ በማጥፋት ሃገራችሁን ኢትዮጵያን ከጥፋት ማዳንና ስማችሁን በኢትዮጵያ ታሪክ የዘላለም መዝገብ ዉስጥ ማስመዝገብ ሙያዊና የቁርጥ ቀን ዜጋዊ ግዳጃችሁ ነው።

Filed in: Amharic