>

የዛሬው የአርበኞች ግንቦት ሰባት የድጋፍ ስብሰባ በኦስሎና የበቀለ ገርባ የፍርድ ቤት ውሎ

እንግዳ ታደሰ

G7 Oslo Norway 05062016 3ዛሬ ኦስሎ ከንጋቱ ጀምሮ በደማቅና ፈገግታዊ የፀሃይ ብርህን ታጅባ ነው ቀኗን ያስተናገደችው ፡፡ ከአዘጋጆቹ እንደሰማሁት ከሆነ ከወያኔ ኮካዎች ጋር ፥ ሌባና ፖሊስ ›. ጨዋታ እየተጫወቱ ነው ስብሰባውን በተቃና ሁኔታ የተወጡት ፡፡ ወያኔዎች ስብሰባ የተካሄደበትን የፈረንጅ ቤተክርስቲያን ቅጽር ለጦርነት ገንዘብ ማሰባሰቢያ ሊሆን ነወይ በማለት እስከመጨረሻዋ ሰዓት ድረስ ትግለ..ደደቢት ትግል አድርገው..እንዳልተሳካላቸው ነው የተረዳሁት ፡፡

የስዊድን ኢትዮጵያውያኖች በአውቶቡስ በጋራ በመሆን ስምንት ሰዓት ያህል ተጉዘው በመምጣት ለበዓሉ ድምቀት ሰጥተውታል ፡፡በጨረታ ፉክክር ውስጥም በኃይለኛ ተግዳሮት ውስጥ ኖርዌዮችን አላላውስ ብለው ነበር ፡፡

በዚህ ዝግጅት ላይ ከዶክተር ብርሃኑ ሌላ ሁለት ድንገቴ..እንግዶችም ተገኝተው ዝግጅቱን የበለጠ ድምቀት እንዲኖረው ችረውታል ፡፡ ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻውና ፥ የአቶ አንዳርጋቸው ታላቅ እህት ወይዘሮ ብዟየሁ ጽጌ ፡፡ ወይዘሮ ብዟየሁ በግጥም ስለአርበኛ አንዳርጋቸው ህይወት ግጥም ሲያነቡ ፣ በአዳራሹ ያለው ህዝብ ሁሉ በለቅሶ ነው ያጀባቸው ፡፡

ዶክተር ብርሃኑ ዛሬ በኢትዮጵያ ያለውን ስርአት እያነጻጸረ ያቀረበው ፣ ከቀድሞዋ ደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ስራት ጋር በማነጻጸር ነበር ፡፡ ዘረኞቹ የደቡብ አፍሪካ ነጮች ቢያንስ በግፈኛ ፍርድ ቤቶቻቸው ላይ ጥቁሮችን ሲያቀርቡ ፣ በካኒተራ ፥ በባዶ እግርና በሙታንታ ጥቁሮችን ፍርድ ቤት አላቀረቡም ነበር ፡፡ዛሬ ግን ተዋርደናል ፡፡እነ በቀለ ገርባን መለመላቸውን በባዶ እግር ፍርድ ቤት ያቆመ ዘረኛ ስርዓት ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው በማለት ሲናገር…ሁሉንም ተካፋይ ነበር እንደ ሰደቻ በንዴት ያጦዘው ፡፡ መፍትሄው በዘር ከረጢት ታጭቆ ትግል ማድረጉ ምንም ውጤት እንዳለመጣ ነው በነበቀለ ገርባ ላይ የተፈጸመው ግፍ የሚያሳየው ፡፡ ትግሉ መቀጣጠል ያለበት በኢትዮጵያውያን ዜግነት ላይ ሲመሰረት ብቻ ነው መፍትሄ የሚያመጣው ፣ አለበለዚያ በየተራ ከመሰልቀጥ አናመልጥም፡፡

ያም ሆነ ይህ ዛሬ በኦስሎ የተሰራው ድል…እስከአሁን…በአውሮጳም ሆነ አሜሪካ አልተሰራም ፡፡ በጠቅላላ ከሁለት ሚልዮን ብር በላይ ተሰብስቧል ..የስዊድን ኢትዮጵያውያኖችን ጨምሮ ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

Filed in: Amharic