>

የአበበ ቢቂላ ልጅ አሁንም በጎዳና ላይ እንደወደቀ አለ [ኤርሚያስ ቶኩማ]

Ye Abebe Bikila Lij begodana lay - Ke Erimias Tukumaከዚህ ቀደም የዛሬ አመት ገደማ ስለአበበ ቢቂላ ልጅ የጎዳና ህይወት አስመልክቼ የተወሰነ ፅሁፍ ፅፌ ነበር። በትላንትናው እለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታን ለመመልከት አዲስ አበባ ስታድየም የገቡ አብሮ አደግ ጓደኞቼ ስታድየም ለመግባት ወደሥፍራው ሲደርሱ አሁንም የአበበ ቢቂላን ልጅ በጎዳና እንደተመለከቱት አጫወቱኝ በጣምም አዘንኩኝ ስንቱ ድምፅ አልባ አዝማሪ በሚረዳበት ዘመን አይዞህ ባይ ያጣው የጀግናው የአበበ ቢቂላ ልጅ አዲስ አበባ ስታዲየም ደጃፍ ላይ ወድቆ ሲለምን መመልከትን የመሰለ አሣዛኝ ነገር አይኖርም አባቱ በባዶ እግሩ ሩጦ የሀገሩን ሰንደቅ አላማ ሲያውለበልብ ልጁ የሚያግዘው አጥቶ በባዶ እግሩ ጎዳና ላይ ወድቆ ይለምናል… አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ዘወትር ማለዳ ለልምምድ የሚወጡና የሚገቡ ሯጮችን ማየት የተለመደ ነው፡፡ ከትንሽ እስከ አንጋፋ፤ ከጀማሪ እስከ ታዋቂ፤ ከእግረኛ እስከ ባለመኪና አትሌቶች ይመላለሱበታል፡፡ ሁሉም አንድ ህልም አላቸው፦በአለም አደባባይ ስኬታማ አትሌት መሆን፡፡ ህልማቸውን እንደሚደርሱበት ደግሞ እርግጠኞች ናቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ መነሻ አላቸው፡፡ እውነት አላቸው! ታሪክ አላቸው! አበበ ቢቂላ…የእነሱ እውነትና እምነት፡፡ የእነሱኩራትና ተስፋ! የዚህ ጀግና አትሌት ልጅ… ኢትዮጵያ አበበ… ግን እንደ ብዙዎች አትሌቶች በአባቱ ኩራትና ተስፋ ከልቡ ውስጥ የለም፡፡ ጀግንነቱን አልወረሰም፡፡
Abebe Bikilaታሪኩንም የሚያካፍለው አላገኘም፡፡ መኖር የፈተነው ህይወት፣ ማንነት ያሰቃየው ሰውነት ይዞ ጎዳና ላይ ወጥቷል፡፡ ከእድሜያቸው በላይ በላይ ገርጅፈዋል፡፡ አዲስ አበባ ስታዲየም ሲወጡና ሲገቡ የሚታዩ አትሌቶች፣ የአበበ ቢቂላን ታሪክ ለአለም እያወሩ ኩራታቸውን የሚገልጹቱ፣ እርሱን ተስፋቸው ያደረጉ፣ ድልንም የተጎናጸፉቱ፣ አዲስ አበባ ስታዲየም ዋና መውጫያና መግቢያ በር ፊት ለፊት ተቀምጦ የሚውለውን ልጁን ማየት አልቻሉም፣ ወይም አልፈለጉም፡፡ ወይም… ወይም….ወዘተ… የጀግናው ልጅ ግን ያያሉ፡፡ ያያሉ… ሊያውም በአንክሮ ያያሉ፡፡ ግን አይናገሩም፡፡ በዝምታ ያያሉ፡፡ ይታዘባሉም፡፡ ‘የአበበ ቢቂላ ልጅ ነኝና እባካቹ እርዱኝ፣ ርቦኛልና አጉርሱኝ’ ማለት ያሳፍራቸዋል፡፡ ብቻ ዝም ብለው ስታዲየሙ እያዩ ይተክዛሉ፡፡ አይናቸው እንባ እያቀረረ ወደ ፈጣሪያቸው ይማጸናሉ፡፡ “ፈጣሪ ሆይ አንተ ለኔ መሆን ከቃተህና ሰው ፊት የምታቆመኝ? እኔስ ምን በደልኩህ? አባቴን ፍቅርና ክብር ሳላጣጥም በስቃይ እንድኖር ስለምን ፈረድክብኝ? ብቻ ግን ተመስገን! ተመስገን!” ……………አሁን ኢትዮጵያ አበበ እድሜያቸው ገፍቷል፡፡ ኑሮ አድክሟቸዋል፡፡ ከአስር አመት በላይ የቆዩበት የጎዳና ህይወት አንገሽግሿቸዋል፡፡ ፍላጎታቸው ብዙዎች እንደሚያስቡት የአበበን ሀብትና ንብረት መውረስ ወይም እውቅና መፈለግ አይደለም፡፡ ማረፍ ነው የሚፈልጉት፡፡
“እኔ የአባቴን ሀብት ንብረት ስጡኝ፣ አካፍሉኝ ብዬ አልሟገትም፡፡ የአበበ ቢቂላ ስለሆንኩም እርዱኝ አልልም፡፡ በዚህ እድሜዬ የአዲስ አበባን ጎዳናዎች እየዞርኩ መለመን አቅቶኛል፡፡ ማረፍ ነው የምፈልገው”
ይሁን እንግዲህ መገፋት መልካም ነው ክፉውን ነገር ሳይሆን፤ ክፉ ያልነው ነገር የሚያጎናጽፈንን ቅን ነገር እናስብ፡፡ መገፋት መልካም ነው፡፡ ከገፉን ነገሮችም ሆነ ግለሰቦች ብዙ ርቀን እንድንሄድ ያደርገናል፡፡ መገፋት ሀይል ነው፡፡ ወደፊት እንድንስነፈጠር የሚረዳን፡፡ መገፋት ከፊታችን ያለውን ፍላጎታችንን በፍጥነት እንድንቀዳጅ የሚያግዘን ጤነኛ እልህ ነው፡፡ ደጉን ጊዜ አሻግረን ማየት እንድንጀምር ሰበብ የሚሆነን፡፡ ከኋላችን የሚገፋን ነገር ከሌለ ከፍተኛው ለመድረስ የምናደርገው እርምጃችን አዝጋሚ ይሆናል፡፡ ሁላችንም በሕይወት ጉዞአችን አሯሯጭ ያስፈልገናል፡፡ አሯሯጮቻችን ደግሞ የግድ ሰዎች መሆን የለባቸውም፡፡ በቀላሉ ኑሮአችንን ራዕያችንን የለውጥ ነሻጮቻችን ማድረግ እንችላለን፡፡
‪#‎ኤርሚያስ_ቶኩማ‬

Filed in: Amharic