>

‹‹ነጻነት ይሰማኛል›› ዮናታን ተስፋየ

ፍ/ቤቱ በአቶ ዮናታን ተስፋየ ላይ ለ2ኛ ጊዜ 28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሰጠ

*‹‹ነጻነት ይሰማኛል›› ዮናታን ተስፋየ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

Yonatan Tesfaye Semayawi Party PRበሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ማዕከል በእስር ላይ የሚገኘው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለ2ኛ ጊዜ የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶበታል፡፡

ዛሬ ጥር 17/2008 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት የቀረበው አቶ ዮናታን ፖሊስ ምርመራየን አልጨረስኩም በሚል የጠየቀበትን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለየካቲት 15/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ አቶ ዮናታን ተስፋየ የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡

ፖሊስ በአቶ ዮናታን ላይ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ሲጠይቅ ‹‹የቴክኒክ መረጃዎችን መሰብሰብ ይቀረናል፤ ያልተያዙ ግብረ አበሮችንም አሉ›› የሚል ምክንያት ማቅረቡን የተጠርጣሪ ጠበቃ ገልጸዋል፡፡

አቶ ዮናታን ተስፋየ በጠበቃ እና በቤተሰቦቹ እንዳይጎበኝ እንደተከለከለና ከታሰረበት ክፍል መታፈን የተነሳ የጤና እከል ቢገጥመውም ህክምና እንዳላገኘ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም አቤቱታውን አድምጦ በጠበቃውም ሆነ በቤተሰቦቹ እንዲጎበኝ እንዲፈቀድለትና ህክምናም እንዲያገኝ ትዕዛዝ መስጠቱን ከጠበቃው ለማወቅ ተችሏል፡፡

አቶ ዮናታን ከችሎት ሲወጣ በስፍራው ለነበሩት ቤተሰቦቹና ወዳጆቹ ያለውን ፍቅር ገልጾ ‹‹ነጻነት ይሰማኛል›› በማለት ጮክ ብሎ ሲናገር ተደምጧል፡፡

Filed in: Amharic