>

መድረክ የተሳካ የተቃውሞ ሰልፍ በኣዲስ ኣበባ ኣካሄደ። የሰማያዊ ፖርቲ ኣመራሮች ተካፍለውበታል

‘ሁሉም የፖለቲካ አና የህሊና እስረኞች ይፈቱ!”

”በፈጠራ ዶክሜንት ህዝብን ማጭበርበር ይቁም!”

”በየክልሉ ብሔረሰብን ከብሔረሰብ ማጋጨት ይቁም” 

ዛሬ መድረክ ባዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በብዙ  ሺዎች ወጥተው ያሰሙት ተቃውሞ ነው። ዜጎች በሃገሪቱዋ ውስጥ የመናገርና ሃሳባቸውን በጋራ ተሰብስበው እንዲገልጹ፣ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ላይ የተለየ ኣመለካከት ስላስተጋቡ  በተቀለቡ የስርዓቱ ታጣቂዎች በጥይት እንዳይደበደቡና፣ በሃገሪትዋ የዜጎች አኩልነት አንዲረጋገጥ በድምጽና ምስል ሲያስተጋቡ ውለዋል።በዚሁ ሰልፍ ላይ፣ በሃገሩቱዋ ውስጥ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲ ኣመራሮች ኣጋርነታቸውን ያሳዩ ሲሆን፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ሌሎች የኣመራር ኣባላቶችም ተቃውሞኣቸውን ከመድረክ ጋር ሲያሰሙ ውለዋል። የተቃዋሚ ፖርቲ መሪዎች ህዝቡን  በማስተባበር፣ መንግሰትን በማስጨነቅ፣ ከህገ-ወጥ ድሪጊቱ እንዲታቀብ ማድረግ፤ ኣለያም ከስልጣን ለማስለቀቅ ጫና መፍጠር የወቅቱና የሰልፉ ኣብይ መፈክር ነበር።  በተቃውሞ ስፍራ የነበሩ ወገኖች የፖለቲካ ፖርቲዎቹ የጋራ ኣቋምና ትብብር ይበል የሚያሰኝና የሚያበረታታ እንደነበርና፣ለሰልፉ ውጤታማነት የመድረክ ኣባላቶችና ኣመራሮች የተጫወቱት ሚና የሚያስመሰግን ብለውታል።

 

 


Filed in: Amharic